BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 4 November 2014

በሰሜን ጎንደር ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የቅማንት ተወላጆች ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ በተጠራ የስራ ማቆም አድማ በዞኑ የሚገኙ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ የተዘጉ ሲሆን፣ መንግስት እስከ መስከረም 30 መልስ የማይሰጥ ከሆነ፣ ተቃውሞው ግብር ባለመክፈል እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በርካታ አስተባባሪዎች ተይዘው የታሰሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው እስከ መስከረም መጨረሻ መልስ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።

እስካሁን ከ130 ሺ ያላናሱ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የቀሩ ሲሆን፣ ሌሎች ትምህርት ቤቶችና የመንግስት መስሪያ ቤቶችም  በአድማው ይቀጥላሉተብሎ ይጠበቃል። በተዘጉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚውለበለቡ ሰንደቃላማዎች እንዲወርዱ ተደርጓል። ሰንደቃላማዎች እንዲወርዱ የተደረገበት ምክንያት የህዝቦችን መብቶች የሚወክሉ አይደሉም በሚል ነው።

No comments:

Post a Comment