.png)
ጥያቄዎቹ በተለይ በግንባሩ አባላትና በካድሬዎች ጭምር የሚነሱ መሆናቸው ግንባሩን ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደጣለው የጠቀሱት ምንጮቻችን የበላይ አመራሩ በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የወሰደው አቋም የለም፡፡
በተለይ ሰሞኑን በዋቢሸበሌ ሆቴል እና በፌዴራል ፖሊስ እየተካሄደ ባለው የመንግስት መገናኛ ብዙሃንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ስብሰባ ላይ የመንግስት ጋዜጠኞች እያነሱት ያሉት ጥያቄዎች ትምህርት ለመስጠት ከተመደቡ የኢህአዴግ ሰዎች አቅም በላይ መሆኑ ትዝብት ላይ ከመጣሉም በላይ ጠንካራ ጥያቄዎቹ እንዳስደነገጣቸው ታውቋል፡፡
በተለይ የፕሬስ ነጻነትና የጋዜጠኞች የጅምላ እስርና ስደት ጉዳይ የተነሱ ጥያቄዎች ተድበስብሰው መታለፋቸው በርካታ ጋዜጠኞችን አሳዝኖአል፡፡ አንዳንዶቹም መግባባትና መተማመን ለማይገኝበት ስብሰባ ለምን የህዝብ ሐብትና ገንዘብ እንደሚባክን በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment