የተሰጠ መግለጫ
ጥቅምት 25 ቀን 2007ዓ.ም
በስብሰባ ጋጋታ የተማረውን ሕብረተሰ የሸፈተ ልብ ምርኮኛ ማድረግ አይቻልም
በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ
በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያጋጠመውን ዙሪያ ገብ ችግር ፣ በመምህራን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል
ከዚህ አንፃር መምህራን የትምህርቱን ጥራት ለማስጠበቅና መብቶቻቸውን ለማስከበር ማድረግ ያለባቸውን
እንቅስቃሴና መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃ በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ መግለጫዎችን በማውጣት
በመላው ዓለም ላሉ ኢትዮጵያውያን ባጠቃላይና በተለይ ለጉዳዩ ባለቤቶች ለኢትዮያጵያ መምህራን ፣
ለተማሪዎችና ለወላጆች እንዲደርስ አድርጓል።
በዚህ መግለጫ ከላይ በርዕሱ እንደተመለከተው የኢትዮጵያን ሕዝብ በጠመንጃ ኃይል እየገዛ ያለው አምባገነኑ
የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በ2007ዓ.ም የምርጫ ዋዜማ ላይ ሆኖ ት/ቤቶችን የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃ
ማዕከል በማድረግ የምርጫ ማጭበርበሪያ ስልት ቀድመ ዝግጅት እያመቻቻ እንደሚገኝና የመምህራንና
የተማሪዎች ተሳትፎና ምላሽ ምን መልክ እንደነበረው ከደረሱን መረጃዎች ጋር አቅርበናል።
ሥርዓቱ ዳኞችን ፣ ፖሊሶችን የራሱን የድርጅት አባላት፣ የአንደኛና የሁለተኛ ድረጃ ት/ቤቶችና የዩኒቨርስቲ
መምህራንን በስብሰባ ጠምዶ ከ2007 ዓ.ም ምርጫ ጋር በተያየዘ ብዙ የትምርት ጊዚያቶችን በመባከንና
ከፍተኛ የሐገሪቱን ገንዘብ በማፍሰስ በሰጠው የፖለቲካ ስልጠና በተለይ ከት/ቤቶች በተነሳበት ጠንካራ
ጥያቄዎችና ተቃውሞ ዕቅዱ እንዳልሰራ፣ ይልቁንም ፍርሃትና ስጋቱ ጨምሮ በስብሰባ ጋጋታ የተማረውን
ሕብረሰብ የሽፈተ ልብ ምርኮኛ ማድረግ እንደማይችል መረዳት ተገዷል። ለዚህም ማስረጃ የሚሆነው
ወያኔ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጠና ወቅት ከሁለተኛ ደረጃና ከዩኒቨርስቲ ተሳታፊ ተማሪዎች ከተነሱ ጥያቄዎችና
አስተያየቶች መካከል የተወሰኑትን ከዚህ በታች እናቀርባለን፡-
አንድ ፓርቲ ብቻ በተቆጣጠረው ፓርላማ ስለመድለ ፓርቲ መናገር አይቻልም።
አሁን ባሉት ዩኒቨርስቲዎች ባልተሟሉት የትምህርት መሳሪያዎችና በአንዳንድ ብቃት በሚጎደላቸው
መምህራን የሚሰጠው ሥልጠና የተማሪዎችን ክህሎት አያዳብርም።
ኢትዮጵያ ከክፍፍል ተጠቃሚ ነች ወይ? ምንስ አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው ከ1993ዓ.ም ወዲህ አዲሲቱ
እየተባለች የምትጠራው?
ኢትዮጵያ ሊበራሊዝምን ብትከታል የበለጠ መጠቀም አትችልም ነበር ዎይ?
No comments:
Post a Comment