ወያኔ እግሩ አዲስ አበባን ከረገጠበት ግዜ ጀምሮ የጭቆና ተቋሞቹን በየቦታዉ ተክሎና ተደላድሎ ህዝብን እንዳሰኘዉ መርገጥ እስከጀመረበት ግዜ ድረስ አንዴ ሰዉ በላዉን የደርግ ስርዐት አስወገድኩላችሁ እያለ ሌላ ግዜ ደግሞ ፌዴራል ስርዐት መስርቼ ብሄር ብሄረሰቦችን ነፃ አወጣሁ እያለ ለተወስነ ግዜም ቢሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ቀልብ መሳብ ችሎ ነበር። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ያ በፌዴራሊዝም፤ በዲሞክራሲና በይስሙላ ምርጫ የተሸፈነዉ የወያኔ አስቀያሚ ገበና ይፋ እየሆነ መጥቶ ወያኔ አርግጫዉንና ግድያዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ትግሉን፤ እስሩንና ስደቱን ተያያዙት።
BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Monday, 30 June 2014
እያበበ የመጣዉ ህዝባዊ ትግል
ጊዜ የማይሠጥ ሀገራዊ ጥሪ አለብን!
ራሱን “የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር” ብሎ የሰየመው ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት (ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት)፤ ሀገራችንን ዕለት ከዕለት ወደ ባሰ አዘቅት እንድትገባ እየጎተታት ነው። የፖለቲካ ፍልስፍናውና የአስተዳደር መመሪያው የሀገራችንን ሕልውና በንጥልጥል ላይ እንዲቀመጥ ሌት ከቀን እየጣረ ነው። በአንፃሩ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ በመቆም፤ በተለያዩ ድርጅቶች ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል፤ ከዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተዋደቁ ያሉ ታጋዮች አሉ። ይህ በዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥትና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል እየተደረገ ያለው ግብግብ፤ ለረጅም ዘመን እንዳለ ሆኖ፤ ፀረ-ኢትዮጵያዊው መንግሥት የፈለገውን እያደረገ ያለበትና፤ በታጋዩ ወገን ያለው ክፍል ደግሞ ላለፉት ፳ ፫ ዓመታት ባለበት የሚረግጥበት ሁኔታ አልተለወጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት የሚጠናወተው ክፍል እየበዛ፤ በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ ይኼው ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ሊቆጣጠረው በማይችልበት ቀውስ ውስጥ ልትገባ አዝምማለች። ከዚህ እንድታቀና ሁላችን እንፈልጋለን። ይኼን ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ማስወገድ ሁላችን እንፈልጋለን።
Sunday, 29 June 2014
ከምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ፍትህ አሁንም ድረስ አለማግኘታቸውን ገለጹ
ኢሳት ካነጋገራቸው የተፈናቃዮች ተወካዮች መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት የአማራ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ አንገባም በሚል ምክንያት ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች አልሆኑም።
ከመንግስት የሚሰጠው መልስ ተስፋ እንዳስቆረጣቸውም ተፈናቃዮች ገልጸዋል
የተፈናቃይ ተወካዮች እንደሚሉት ከፍተኛ ችግር ከነበረበት ከሚያዚያ 22 እስከ ግንቦት2 በነበረው ጊዜ ለደረሰው የሰው ህይወት እንዲሁም ለጠፋው ከፍተኛ ንብረት የአካባቢው ባለስልጣናት እና በክልሉ ተሰማርቶ የሚገኘው ልዩ ሃይል እጅ አለበት። ባለስልጣናቱ የችግሩ አሳሳቢነት ሲነገራቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን የተፈናቃዮች ተወካዮች ተናግረዋል።
በተለይም ጉዳዩን እንዲያጣራ በቅርቡ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ማስረጃዎችን አስቀድሞ ይፋ እያደረገና የምስክሮችንና የጠቁዋሚዎችን ስሞች አስቀድሞ ይፋ እያደረገ ህዝቡ በድጋሚ እንዲጋጭ ጥረት እያደረገ ነው በማለት ተወካዮች ገልጸዋል።
በጊምቢና በቄለም ያሉ ዘመዶቻቸውን በስልክ ለማግኘት መቻላቸውን የሚናገሩት ተፈናቃዮች፣ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራራቱ እንደቀጠለ መሆኑን እንደነገሩዋቸው አስረድተዋል።
ከኦሮምያና ከፌደራል የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ማክሰኞ ወደ ጊምቢ በማቅናት ነዋሪውን እያነጋገሩ ነው። እስካሁን ድረስ በመንግስት በኩል ተፈናቃዮችን በተመለከተ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።
በጊምቢ ተነስቶ በነበረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲወድም፣ አንድ ፎቅና ሁለት መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በርካታ ቤቶችም ተዘርፈዋል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31736
ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ”ሞት ሊበየንበት ይችላል” -በሽብርተኝነት ክስ ሞት ተፈርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ 127 ሰዎች ኣሉ

”ባለፈው ሳምንት ለማወቅ እንደተቻለው ዕድሜው 52 የሆነና ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ የተባለ ኖርዌጂያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል።” tiltalt for terror በማለት የጀመረው የኖርዌዩ ዳግብላደት ሲቀጥልም…”የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ ኣቀባይ እንደሚለው ገንዘብ ኣሰባስቦና ኣጥቂ ቡድን መልምሎ ኣደጋ ለማድረስ ሲሞክር ያዝነው በማለት መከሰሱን ያትትና በበኩላቸው የኖርዌዩ የሰብኣዊ መብት ጥበቃም ሆኑ የዓለም ኣቀፉ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጥብቅ ያወገዙት ሲሆን፣ ኣያይዘውም ለዚሁ ድረ-ገጽ ታሳሪው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ከወትሮው የከፋ እንደሆነም ስጋታቸውን እንደገለጹለት ያወሳል።
ኢትዮጵያንም ሆነ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት፣ በኣሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ የሚገኙትን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ ”በሚገባ ያውቃሉ” ያሉዋቸውን የሰብኣዊ መብት ተሟጋችና ኖርዌጂያን ፈሊክስ ሆርነ ን ኣነጋግሮ ድረ-ገጹ ያገኘው መልስ ”ኖርዌጂያኑን ኦኬሎ በሚቀጥለው ሳምንት የሚሰየመው ችሎት ሞት ሊበይንበት ይችላል” በማለት የገለጹ ሲሆን ኣክለውም፣
”በሃገሪቷ ውስጥ በሽብር ወንጀል የሚከሰሱት ዜጎች የሚገጥማቸው የሞት ፍርድ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሞት የሚፈረድባቸው ዜጎች ምንም ማስረጃ ያልቀረበባቸው ናቸው።
መዝገቦቹ መልሰው ተቀራረቡ የእምነት ክህደት ቃል በኃይል አስፈርመዋቸዋል
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በስድስቱ ጦማሪያንና በሦስቱን ጋዜጠኞች ላይ የፌደራል ፖሊስ የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቀጠሮ የሚያራዝመውን ሁለት መዝገብ አንዴ ሲያቀራርበው መልሶ ደግሞ ሲያራርቀው ቆይቶ አሁን ደግሞ መዝገቦቹን መልሶ አቀራርቧቸዋል፡፡እስረኞቹ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ኹኔታ ፖሊስ ያረቀቀውን የእምነት ክህድት ቃል ተገደው እንዲፈርሙ አድርጓቸዋል፡፡
የሦስቱ ብሎገሮች አቤል ዋበላ፣በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን ቀጠሮ ለዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ የሚል የነበረ ሲኾን ከጠዋት ጀምሮ ችሎቱን ለመታደም የመጣውን ቤተሰብ፣ጓደኞቻቸው፣ጋዜጠኞች፣ዲፕሎማቶችና የወጣቶች ደጋፊዎች በአጠቃላይ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጋ ሰው ከችሎት ውስጥ የሚሰማውን አዲስ ነገር ለመጠበቅ በግቢው ውስጥ ቆመው ነበር፡፡ ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢ የእስረኞቹ ጠበቃ አቶ አመኃ መኮንን ተጠርተው የመዝግብ ቤት ጸሐፊዋ ስለሌለች ችሎቱ ለከሰዓት በኋላ እንደተዛወረ ይነገራቸዋል፡፡ እርሳቸውም ችሎቱን ለመከታተል ለቆመው ሰው መልዕክቱን ያስተላልፋሉ፡፡ ጥቂት ሰዎችም ይህን መልዕክት ሰምተው ግቢውን ለቀው ይወጣሉ ብዙኃኑ ግን እዛው እንደቆሙ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ይጀምራሉ፡፡
የሦስቱ ብሎገሮች አቤል ዋበላ፣በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን ቀጠሮ ለዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ የሚል የነበረ ሲኾን ከጠዋት ጀምሮ ችሎቱን ለመታደም የመጣውን ቤተሰብ፣ጓደኞቻቸው፣ጋዜጠኞች፣ዲፕሎማቶችና የወጣቶች ደጋፊዎች በአጠቃላይ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጋ ሰው ከችሎት ውስጥ የሚሰማውን አዲስ ነገር ለመጠበቅ በግቢው ውስጥ ቆመው ነበር፡፡ ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢ የእስረኞቹ ጠበቃ አቶ አመኃ መኮንን ተጠርተው የመዝግብ ቤት ጸሐፊዋ ስለሌለች ችሎቱ ለከሰዓት በኋላ እንደተዛወረ ይነገራቸዋል፡፡ እርሳቸውም ችሎቱን ለመከታተል ለቆመው ሰው መልዕክቱን ያስተላልፋሉ፡፡ ጥቂት ሰዎችም ይህን መልዕክት ሰምተው ግቢውን ለቀው ይወጣሉ ብዙኃኑ ግን እዛው እንደቆሙ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ይጀምራሉ፡፡
የከፍተኛ 15 ቀይሽብር ተዋንያን ከፍያለኝ ዓለሙ 22 ዓመት እሥራት ተፈረደበት
ቀን ፡ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፮ ዓ.ም. (May 23, 2014)
ከ«ያ ትውልድ ተቋም» የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
የከበረ ሰላምታችንን በቅድሚያ አያቀረብን፤
May 23, 2014 (ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፮ ዓ.ም.) በሰሜን አሜሪካ
ዳንቨር ኮልራድ የአረመኔውን ከፍተኛ 15ቱ ቀይ ሽብር ተሳታፊ
ከፋለኝ ዓለሙን ጉዲይ የመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የፍርድ ቤቱ
ችሎት ከጠዋቱ 9፡30 ተሰየመ። ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩት ጠበቆችና
የሚመለከታቸው ተገኝተዋል። ከፋለኝ ዓለሙን ለመጀመሪያ ጊዜ
በዳንቨር ኮልራድ በመመልከት ወደ ፍርድ ይቀርብ ዘንድ ከፍተኛውን
ድርሻና ኃሊፊነት የተወጣው የዳንቨሩ ነዋሪ አቶ ክፍለ ከተማን ጨምሮ
በነሐሴ ፬ ቀን ፪ ሺህ ፭ ዓ.ም. በዳንቨር በተካሄደው የፍርድ ቤት ውሎ
በአካል በመገኘት በከፋለኝ ዓለሙ በከፍተኛ 15 እሥር ቤት በ1970/71
ዓ.ም. በጊዜው ወጣቶች፣ ሕፃናትና አዛውንቶች ላይ የፈጸመውን
አሰቃቂ ግርፋት፣ ግፍና ግድያ በመመስከር ተገኝተው የነበሩት ወ/ሮ
አበበች ደምሴ ከሳንሆዜ፣ አቶ ብርሃን ዳርጌ ከዋሽንግተን ዲሲ፣ ድር ሳሙኤል ከተማ
ከዳንቨር እና አቶ ነሲቡ ስብሐት ከቨርጂንያ ሲገኙ አቶ አሳየኸኝ ፈለቀ ከቦስተን በሥራ
ምክንያት አልተገኙም።
Thursday, 26 June 2014
አብዛኛው ህዝብ ለመንግስት ጥላቻ አለው” ሲል አንድ ከኢህአዴግ የወጣ ሰነድ አመለከተ

የብአዴን አመራር እና አባላቱ ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ አለመምጣቱን፣ ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ግድ እንደሌላቸው፣ እንዲሁም መንግስትን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ቀርቧል።
“የኢትዮጵያ ህዝቦችና አገራዊ ህዳሴያችን” በሚለው የማጠቃለያ ግምገማ ሰልጣኞቹ ” ስለአገራቸው ታሪክ ብዙ ትምህርት መቅሰማቸውን፣ የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት ድርጅቱ እየከፈለ ያለውን መስዋትነት፣ የኢትዮጵያ ገናና ስልጣኔ ለምን እንደወደቀ፣ የህዳሴ ጉዞውን ሊያሳካ የሚችል መንግስት ያለ መሆኑን፣ የብዝህነትና እኩልነት ሀገራዊ ጠቀሜታ ፣ የአማራ ገዢ መደብ ሌሎች ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ብቻ ሳይሆን አማራውን ጭምር እንደጨቆነ” የሚያሳይ ትምህርት መውሰዳቸውን ሰነዱ ያመለክታል።
እሥረኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ደሳለኝ ኃይለማርያም በምግብ ራሳችን ችለናል ማለቱ ከምኑ ላይ ነው ስህተቱ?!
መግቢያ፦ ህወሃት/ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊ የሆነ አጀንዳ እንደሌለውና ሊኖረውም እንደማይችል ከተቋሙ መሠረታዊ ፕሮግራም በመነሳት ግንቦት 20/1983 በሚል ባቀርብኳት ጦማሬ አስረግጨ አሳውቄ ነበር። እነዚህን የምልበት ምክንያት ከባዶው ተነስቼ ሳይሆን ድርጅቱ ከፈጸማቸውና እየፈጸማቸው ካለው ፀረ-ሕዝብና አሰቃቂ ዘግናኝ ተግባሮቹ በመነሳት እንደሆነ እንዲታወቅልኝ እወዳለሁ።የዚህ ድርጅት መነሻውም ሆነ የመጨረሻ ግቡ ከተቻለ የህወሃት/ኢህአዴግ ትውልዶች ብቻ የሚኖሩባት ኢትዮጵያን መፍጠር አለዚያም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነውን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነገድ ተራ በተራ እያዘናጉ መጨረስና አገሪቱንም ለባእዳን እንዳወጣች ሸጦ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳልነበረች ማድረግ እንደሆነ ለማንም ስውር ሊሆንበት አይገባም።

ድርጅቱ ቀደም ሲል ጫካ ውስጥ በትግል በነበረበት ወቅትም ሆነ የመንግሥት ሥልጣን ከያዘ በኋላ የፈፀማቸውና እየፈፀማቸው ያሉት አፀያፊ ድርጊቶች ታይተው ያማያውቁ የኢትዮጵያዊነት ሞራልና ስብእና የጎደላቸው ስለመሆናቸው ብዙ የተባለ ሲሆን አንድ ግልጽና ቀላል አስረጅ መጥቀስ የበለጠ እውነታውን ያሳያል ብየ አስባለሁ።
ድርጅቱ ቀደም ሲል ጫካ ውስጥ በትግል በነበረበት ወቅትም ሆነ የመንግሥት ሥልጣን ከያዘ በኋላ የፈፀማቸውና እየፈፀማቸው ያሉት አፀያፊ ድርጊቶች ታይተው ያማያውቁ የኢትዮጵያዊነት ሞራልና ስብእና የጎደላቸው ስለመሆናቸው ብዙ የተባለ ሲሆን አንድ ግልጽና ቀላል አስረጅ መጥቀስ የበለጠ እውነታውን ያሳያል ብየ አስባለሁ።
በምስራቅ እዝ የመከላከያ መኮንኖች መካከል ውስጣዊ ውጥረት ሰፍኗል።
በወያኔ መኮንኖች እና በኢትዮጵያ የመከላከያ ስራዊት መኮንኖች መካከል በፖለቲካ እና በጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ዙሪያ ውስጥ ውስጡን እየተካረረ የመጣው አተካራ ከባድ ውጥረት መፍጠሩን በእዙ የሚገኙ መኮንኖች የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ሕገመንግስታዊ ጥያቀዎችንእና ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞችን የሚተይቁ መክንኖች ከየክምፑ ተለቅመው ወደ ሰሜን እዝ እና ወደ ሶማሊያ ከሄደው ጦር ጋር እንዲቀላቀሉ ከተደረገ በኋላ ውጥረቱ እየሰፋ መምጣቱ ታውቋል።
Tuesday, 24 June 2014
ከሕገ-መንግሥቱ በፊት (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)
በመጀመሪያ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ጉዳይ ‹‹ያገባኛል ባይነት እና ጋዜጠኝነት በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ›› በሚል ርዕሥ የውይይት መነሻ ሀሳብ ከሙያ አጋሮ ቼ ጋር እንዳቀርብ ስለጋበዘኝ በቅድሚያ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
፩
የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 29
ነሐሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት ሲጸድቅ የፈረሙበት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ነበሩ፡፡ ይህ ሕገ-መንግሥት በአንቀጽ 29 (1) እና (2) ላይ ሃሳብን በነጻነት የመገለጽ መብትን በተመለከተ እንዲህ ይላል፡:
ሰበር ዜና፡- ጅዳ ሳውዲ አረቢያ አንዲት ኢትየጵያዊት በጅዳ ቆንስል ግቢ ታንቃ ተገኘች

በሀዋሳ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ዛሬም የረሀብ አድማ ላይ ናቸው!! በሀዋሳ ሰ.መ.ጉ እስረኞችን እንዳይጎበኝ ተከለከለ – የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት

ጅቡ ሞቷል፡ ቀበሮው እየበላ ነው!
ህወሓትን ስንቃወም የደርግ ናፋቂዎች ይሉናል። ህወሓትን መቃወም ደርግን መደገፍ ነው እንዴ? ደርግን ሳንደግፍ ህወሓትን መቃወም አንችልም እንዴ?
ጅቡ ግን ሞቷል። በድን ሁኗል። ሬሳ ነው ያለው። በጎቹ ደግሞ ጅቡ በህይወት እያለ ከቀበሮ በላይ በግ-በሊታ መሆኑ ያውቁታል። ጅብ በአንዴ ብዙ በጎች (ቀበሮ ከሚበላው በላይ) ይበላ እንደነበር በደንብ ያውቃሉ።
Thursday, 19 June 2014
ህወሓት የቤተክርስቲያን ገንዘብ ዘረፈ
በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላዕሎ ወረዳ “አይናለም” የተባለ ጣብያ (ንኡስ ወረዳ) አለ። በዛ አከባቢ ያለው ደን “የመለስ ፓርክ”ተብሎ ተከልሏል። ኗሪዎቹ “የመለስ ፓርክ” መባሉ አልተዋጠላቸውም፤ ተቃውመውታል።
ባለፈው ወር ነው። “ከመለስ ፓርክ” የተወሰነ ዛፍ ይቆረጣል። በዚህ ጉዳይ የተቆጡ ካድሬዎች የአይናለም ኗሪዎችን ሰብስበው ዛፉ የቆረጠው ማን እንደሆነይጠይቃሉ። አውጫጭ መሆኑ ነው። ህዝቡ ላለመናገር አደመ። ህዝቡ ስላልተናገረ ለስምንት ተከታታይ ቀናት ታሰረ፤ ቅጣት መሆኑ ነው። ህዝቡ የታሰረውፖሊስ ጣብያ አልነበረም፤ ፖሊስ ጣብያ አይበቃውማ። በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ (ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ እናቶች በቃ ሁሉም) በረኻ ላይ በፖሊሶች ተከቦታስሮ ይውላል። ዝናብ ይደበደባል፤ ፀሓይ ይመታል። ህዝቡ ግን ይህን ሁሉ ስቃይ ችሎ በቃሉ ፀና። ካድሬዎቹ ከስምንት ቀናት በኋላ ተስፋ ቆርጠው ተውት።ህዝቡ ግን ተቀይሟል።
አሸባሪው አቃቤህግ በአሜሪካ !!

የእነ ሽመልስ ከማልን አርአያ እንዲከተሉ ተመልመለው እንደነ እስክንድር ነጋ፣ ርዮት አለሙ፣ ውብሸት ታየ አንዱዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣በቀለ ገርባ፣ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውያንን ለእስርና ለሰቆቃ ከዳረጉት አቀብያነ ሕግ መሃል ቴዎድሮስ በሃሩ፣ ዘርሰናይ ምስጋናው፣ብርሃኑ ወንድምአገኝ በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው።
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ኢትዮጵያን ከዓለማችን ደሃ ሀገራት ከመጨረሻው ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና ሌሎችንም በሃስት በመክሰስ እና በመመስከር ለዕስር ከዳረጉ ህሊና የሌላቸው ግለሰቦች በትቂቱ ይህን ይመሰላሉ ::
አሽባሪው አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ በታማኝነት ህውሃቶችን በማገልገል በርካታ ንጽሃን በሃስት ከሶ ለዕስር እና መከራ ዳርጎ በአሁኑ ግዜ ከቤተሰቡ ጋር በአሜሪካ ሃገር በሜሪላንድ ሲልበርስፕሪንግ በሰላም ኑሮውን እየመራ ይገኛል:: አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ እስክንድር ነጋን ጋዜጠኛ ርዮት አለሙን እንዲሁም በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊና ዋና ዋና በተባሉት ላይ ታላቅ ሚና የተጫወተ ግለሰብ ነው::
ጦማሪያኑን እና ጋዜጠኞቹን በተመለከተ ችሎቱ ለፖሊስ ጠንካራ ትዕዛዝ አስተላለፈ

Saturday, 14 June 2014
የሕዝብ ሃብቶች በመንግስት ወጪዎች ሰበብ ያለርሕራሔ በወያኔ ባለስልጣናት እየተዘረፉ ነው።
ሓገራችን በጥቂት አደገኛ የገዢው ፓርቲ ዘራፊዎች እጅ ወድቃለች።
ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ የወያኔ መራሹ ጁንታ ያዋቀራቸውና በተቋምነት የሚታወቁ መስሪያቤቶች ውስጥ እየተፈጸመ ያለው አግባብ ያልሆነ ስልጣንን መከታ በማድረግ በትእዛዝ ብቻ ካለማረጋገጫዎች እና ካለምንም ቅድመ ዝግጅት በመስፋፋቱ ከፍተኛ ዘረፋ እየተካሄደ ነው።በየተቋማቱ የሚደረጉ የበጀት ምደባዎች፤ኮንትራቶች ፤የንብረት ግዢዎች፤ ጨረታዎች ፡የውጪ ምንዛሬ እንቅስቃሲዎች እና የተለያዩ ወጪዎች አገሪቷ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት በማስከተል የኑሮ ውድነት እንዲስፋፋ እያደረጉ ነው።ይህ ዘረፋ ተቆጣጣሪ አካላት ማጣት የዘመድ አዝማድ የውስጥ አሰራር እና ግንኙነት በፓርቲ ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረ አለመተማመን እና መፈራራት አገሪቷ በጥቂት አደገኛ ዘራፊዎች እጅ እንድትወድቅ ሆኗል።
የወያኔው መንግስት በተለያዩ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር በማድረግ በግብር እና በቀረጥ ስም እየበዘበዛቸው ቢሆንም የመንግስት በጀት ተብሎ የተመደበ ሲባክን አገልግሎት ላይ ሳይውል ሲቀር አላስፈላጊ ግዢዎች ተደርገው ብክነት ሲታይ ዝምታን በመምረጥ በሃገሪቱ ከፍተኛ የሙስና ተግባራቶች እንዲስፋፉ እድል ከፍቷል። ሙሰኞችን ጸረ ሙሰኞችም የተወሰኑ ባለስልጣናት በሆኑባት ኢትዮጵያ የሚደረገውን ብዝበዛ ለመሸፋፈን በተለያዩ የፖለቲካ ስውር እጆች ብክነት እና ብዝበዛን በማስፋፋት ህዝብ በኑሮ ውድነት እንዲደናቆር አድርገዋል።
ከስራ አፈጻጸም ጋር የማይዋሃዱ የማይገናኙ እና የማይመጣጠኑ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚመደቡ በጀቶች ውጤት አልባ ለሆኑ ጉዳዮች ከፍተኛ ውጪ በመመደብ - ለስብሰባ- ለነዳጅ-ለሆቴል-ለመኪና ግዢ-ለአልተፈለገ ድግስ- ለፊልድ አበል -ወዘተ እየተባለ አላስፈላጊ እና የማይመጥን ወጪ በማውጣት የወያኔ ባለስልጣናት የህዝብን ሃብት ካለመራራት እየበዘበዙት ይገኛሉ። ባለስልጣናቱ ወደ ባንኮች በመሄድ በመደወል በጥቅም በመተሳሰር ከተለያዩ የንግድ ድርት ባለቤቶች እና ከባንክ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር የውጪ ምንዛሬ በማውጣት የሃገሪቷን ካዝና በባዶ ለማስቀረት ሌት ከቀን እየሰሩ ሲሆን እንዲሁን ይህንን የዶላር ምንዛሬ ለማግኘት ለሚፈልጉ ነጋዴዎች በአንዱ ዶላር ሁለት ብር ጉቦ በማስከፈል ስልታናቸውን ለከፍተኛ ብዝበዛ እየተተቀሙበት ነው።
ስልጣናቸውን ያለአግባብ የሚጠቀሙት የወያኔ ሰዎች ከውጪ ሃገር በግዢ እንዲመጡ የሚወሰንባቸውን የተቋማት የሕዝብ ንብረቶች ጨረታዎች በሙሉ በከፍተኛ የሙስና ትሥሥር የሚፈጸሙ ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ከውጪ የተገዙ የተቋማት ንብረቶች ከሙስና የጸዱ እንዳልሆኑ እና በጥቅማጥቅም ውህደት በኮሚሽን የተገዙ እንደሆነ ማረጋገጫዎች በገሃድ እያየናቸው ነው፤ጨረታ የሚለውን ቃል እንደ ህጋዊነት በመጠቀም በመጠኑ አስደንጋጭ የሆነ ኮሚሽን በመያዝ የሃገር እና የህዝብ እየተበዘበዘ ሲሆን በዚሁ የኮሚሽን እና የጉቦ ትሥሥር ከተለያዩ አገሮች የሚገዙ ንብረቶች የተበላሹ እና የሚቀላልጡ ውጤት አልባ በመሆናቸው ምንም ሳይሰራባቸው በየቦታው እንደቆሙ እና እንደወዳደቁ ሲቀሩ ባለስልጣናቱ ሙስናቸውን በመቀጠል ተቆጣጣሪ አልባ ስለሆኑ ወደ ሌላኛው ብዝበዛቸው ይሻገራሉ። ይህ አደገኛ ዘረፋ በብዙ መልኩ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ዘረፋዎች እየተካሄዱ ነው በሂደት እያየነው እንሄዳለን ።
የዞን 9 ጦማሪዎች እና ጋዜጠኛው ተጨማሪ 28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጠባቸው
የሕዳሴ አብዮት አተገባበር!
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ ባቀረብኳቸው ጽሑፎች ገዥው-ግንባር የመረጠው ስሁት መንገድ፣ ኢትዮጵያችንን ለሳልሳዊው አብዮት እያዘጋጃት መሆኑን ማውሳቴ ይታወሳል፡፡ ይህ የለወጥ መስመርም “የሕዳሴ አብዮት” የሚል ስያሜ ኖሮት፣ ሁሉን አሳታፊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ንቅናቄ በመፍጠር አገሪቱን በዳግም
ውልደት ለማንፃት ብቸኛ አመራጭ የመሆኑ ጉዳይ በስነ-አመክንዮ ተሰናስሎ ቀርቦበት ነበር፡፡ በዚህ ተጠየቅ ደግሞ አብዮቱን ከዳር ለማድረስ ሊተገበሩ የሚችሉ (በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ) ስልቶች እና በመጀመሪያው የንቅናቄው ምዕራፍ ሥርዓቱ ለመመለስ ሊገደድባቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን እንዳስሳለን፡፡
Friday, 13 June 2014
አስገዳጁ የፋይናንስ አዋጅ ጸደቀ
የኢህአዴግን የልማት ስኬት እንዲመሰክሩ የተጠሩ ሰዎች ያልተጠበቁ ችግሮችን አነሱ
ሰኔ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ምርጫ ለአሸናፊነት ያበቃኛል በማለት ኢህአዴግ በተለያዩ አካባቢዎች የተመረጡ ሰዎች በአምስት አመታት ውስጥ ስለተሰሩ ስራዎች እንዲመሰክሩ በማድረግ ላይ ቢሆንም፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ያልተጠበቁ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው።
በደብረብርሃን ሰሞኑን ተካሂዶ በነበረው ውይይት ህዝቡ የተለያዩ የማህበራዊ አግልግሎት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አንስቷል። ርዕሰ መምህር ከፈለኝ ዘውዴ እንደተናገሩት በከተማዋ ውስጥ ከ15 ሺ ያላነሱ ነዋሪዎች ለ7 ዓመታት መብራት ሳያገኙ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
የወያኔ ግፍ ለከቱን አልፏል!
የወያኔ ሹማምንትና በዘር ለዝርፊያ የተሰማራው ድርጅታቸው በቅርቡ ደግሞ ስዘርፍ አያችሁኝ በሚል ቁጣ ከአንደበታቸው በላይ ምንም ባልታጠቁ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ከአካሄደው ጅምላ ጭፍጨፋ አልፎ ግለሰብ ተማሪዎችን በማሳደድ ሰቆቃ መፈጸሙን ቀጥሎበታል። በዚህ ሰአት በርካታ ተማሪዎች በታወቁና ባልታወቁ እስር ቤቶች ታጉረዋል። ብዙዎቹ ከትምህርት ገበታ ካላንዳች ጥያቄ ተባረዋል እየተባረሩም ይገኛሉ።
ከወያኔ ግፎች ሁሉ በእጅጉ የሚዘገንነው ሌሎችን በመወንጀል ማሰቃየትና መግደል በፈለገ ቁጥር ራሱ ወንጀል ከፈጸመ በኋላ ወንጀሉን በሌሎች ላይ ለማመኻኘትና ለመቅጣት የሚጠቀሙበት የሃሳብ ዘዴ ነው።
በአለምያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተሰበሰቡበት አዳራሽ ውስጥ የደህንነት አባሎች ቦንብ አፈንድተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ የሚፈልጓቸውን ወጣቶች ቦንብ ሲያፈነዱና ሲጠምዱ ያዝናቸው በማለት ከዚህ በፊት በዊክሊክ መረጃ እንደተለቀቀው የተለመደ በሰው ልጆች ላይ ሰቆቃ ይፈጽማሉ። ሌላው ቀርቶ ቦምብ አፈነዱ ተብለው የተከሰሱት ተማሪዎች በገዛ ጓደኞቻቸው ላይ ቦምብን የሚወረውሩበት ምክንያት የላቸውም።
የመሬት ወረራን በመቃወሜ የተፈፀመብኝ በደል – አበበ ሆንጃ (ከሰበታ)

ከህወሀት/ኢህአዴግ ጓዳ በሀብታሙ አያሌው ላይ የተወረወረች ቀስት
ከዘላለም ደበበ

ይህን ፅሁፍ በሎሚ መፅሄት ላይ ባለፈው ሳምንት አወጣሁት፡፡ መፅሄቱ ላልደረሳችሁ ይኸው እዚህ ለጠፍኩት፡፡
በቅድሚያ እንኳን ወታደራዊ አምባገነኖች ተደምስሰው ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› አምባገነኖች ለተተኩበት የግምቦት 20 በአል አደረሳችሁ፡፡ ዛሬ ዝምታ ሲበዛ ፍርሀት፣ ውሸት ደግሞ ሲደጋገም እውነት ይሆናልና የማውቀውንና የተሰማኝን ለአምባቢም ግልፅ ሊሆንለት የሚገባ ጉዳይን በወፍ በረር ላስቃኝ ወደድኩ፡፡
ለፅሁፌ መነሻ የሆነኝ ሎሚ መፅሄት አቤል ኤፍሬም በተባለ ግለሰብ የቀረበውንና መፅሄቱ ይዞት የወጣው ፅሁፍ ነው፡፡ ፅሁፉም በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ላይ ያነጣጠረ ግልፅ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው፡፡ እኔም ይህንን ፅሁፍ ያዘጋጀሁት የአቶ ሀብታሙ ተሟጋች ሆኜ ሳይሆን እውነታው ግን በፅሁፉ ከቀረበው ጋር ፍፁም የተለያየ ስለሆነ እና የፅሁፉ ‹‹ሞቲቭ›› አላማ ስም በማጉደፍ አምባገነኑ ስርዓት እንዲቀጥል ማስቻል ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ከህወሃት/ ኢህአዴግ መንደር ወደ ወጣቱ ፖለቲከኛ የተወረወረች ትንሽ ቀስት መሆኗን መጠቆም ስለሚገባ ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ በሎሚ መፅሄት ላይ ባለፈው ሳምንት አወጣሁት፡፡ መፅሄቱ ላልደረሳችሁ ይኸው እዚህ ለጠፍኩት፡፡
በቅድሚያ እንኳን ወታደራዊ አምባገነኖች ተደምስሰው ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› አምባገነኖች ለተተኩበት የግምቦት 20 በአል አደረሳችሁ፡፡ ዛሬ ዝምታ ሲበዛ ፍርሀት፣ ውሸት ደግሞ ሲደጋገም እውነት ይሆናልና የማውቀውንና የተሰማኝን ለአምባቢም ግልፅ ሊሆንለት የሚገባ ጉዳይን በወፍ በረር ላስቃኝ ወደድኩ፡፡
ለፅሁፌ መነሻ የሆነኝ ሎሚ መፅሄት አቤል ኤፍሬም በተባለ ግለሰብ የቀረበውንና መፅሄቱ ይዞት የወጣው ፅሁፍ ነው፡፡ ፅሁፉም በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ላይ ያነጣጠረ ግልፅ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው፡፡ እኔም ይህንን ፅሁፍ ያዘጋጀሁት የአቶ ሀብታሙ ተሟጋች ሆኜ ሳይሆን እውነታው ግን በፅሁፉ ከቀረበው ጋር ፍፁም የተለያየ ስለሆነ እና የፅሁፉ ‹‹ሞቲቭ›› አላማ ስም በማጉደፍ አምባገነኑ ስርዓት እንዲቀጥል ማስቻል ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ከህወሃት/ ኢህአዴግ መንደር ወደ ወጣቱ ፖለቲከኛ የተወረወረች ትንሽ ቀስት መሆኗን መጠቆም ስለሚገባ ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)