በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላዕሎ ወረዳ “አይናለም” የተባለ ጣብያ (ንኡስ ወረዳ) አለ። በዛ አከባቢ ያለው ደን “የመለስ ፓርክ”ተብሎ ተከልሏል። ኗሪዎቹ “የመለስ ፓርክ” መባሉ አልተዋጠላቸውም፤ ተቃውመውታል።
ባለፈው ወር ነው። “ከመለስ ፓርክ” የተወሰነ ዛፍ ይቆረጣል። በዚህ ጉዳይ የተቆጡ ካድሬዎች የአይናለም ኗሪዎችን ሰብስበው ዛፉ የቆረጠው ማን እንደሆነይጠይቃሉ። አውጫጭ መሆኑ ነው። ህዝቡ ላለመናገር አደመ። ህዝቡ ስላልተናገረ ለስምንት ተከታታይ ቀናት ታሰረ፤ ቅጣት መሆኑ ነው። ህዝቡ የታሰረውፖሊስ ጣብያ አልነበረም፤ ፖሊስ ጣብያ አይበቃውማ። በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ (ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ እናቶች በቃ ሁሉም) በረኻ ላይ በፖሊሶች ተከቦታስሮ ይውላል። ዝናብ ይደበደባል፤ ፀሓይ ይመታል። ህዝቡ ግን ይህን ሁሉ ስቃይ ችሎ በቃሉ ፀና። ካድሬዎቹ ከስምንት ቀናት በኋላ ተስፋ ቆርጠው ተውት።ህዝቡ ግን ተቀይሟል።
ከተወሰነ ግዜ በኋላ የማዳበርያ ጉዳይ መጣ። መዳበርያ ዉሰዱ ተባሉ። አንወስድም አሉ፤ በአንድ ቃል። ህዝቡ ያቀረበው ምክንያት መዳበርያ ለመግዛትገንዘቡም ፍላጎቱም የለንም የሚል ነው። ካድሬዎች ህዝቡን ለማስፈራራት ሞከሩ፣ አሰሩ፣ አዋረዱ። አልተሳካላቸውም። የካድሬዎች የመጨረሻ ሓሳብ ህዝቡለማዳበርያ የሚሆን ገንዘብ ከሌለው ከቤተክርስያን ታቦት እንዲበደር ጠየቁት። ህዝቡ አሻፈረኝ አለ። ከታቦት ተበድረን ማዳበርያ አንገዛም፣ ከእግዚአብሄርቤት ተበድረን ለመንግስት አንሰጥም አሉ።
ካድሬዎችም ማዳበርያው በተሽከርካሪ ጭነው ጣብያው (ቀበሌው) ላይ አራገፉት። ህዝቡም የምንከፍለው ገንዘብ የለንም አለ። ካድሬዎቹ ደግሞ የአይናለምህዝብ ታቦት የሚገኝበት “መድሃኔዓለም ቤተክርስትያን” ጋ በመሄድ ለማዳበርያው ዋጋ የሚሆን ገንዘብ ይወስዳሉ። የታቦቱ ቄሶች ዝርፍያ ተፈፅሞብናል በሚልተግባሩን ይቃወማሉ። ቄሶቹ አርፈው እንዲቀመጡ ይነገራቸዋል። አሁን ለማዳበርያው የሚሆን ገንዘብ በቤተክርስትያኑ ተወስዷል። ህዝቡም ተቃውሟል።አሁን የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየሞከሩ ነው። ህወሓትም እያስፈራራቸው ነው። ቤተክርስትያን ተዘርፏል ብለው ተቃውሞ ያሰሙ ቄሶች ግንታስረው ይገኛሉ።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31200
No comments:
Post a Comment