BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 26 November 2013

ጠጉረ ልውጥ የተባለው ያው አንዱ ሕዝብ አይደል?

ኢትዮጵያውያን ለተለያዩ ጉዳዮች በአገሪቱ ማለትም በሃገራቸው ይዘዋወራሉ፡፡ 

በተለይ በአዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መነሃሪያ ነች፡፡ ኢትዮጵያም ሆነች 

አዲስ አበባ ትንሽ መንደር አይደሉም፡፡ 

በሽብርተኝነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!


ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡ አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም የሚያወጡት ሕግ የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ነው ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደ የተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ ነው የሚባለው፡፡ ይህንን ያልኩበት አብይ ጉዳይ ዛሬ ሃገራችንንና ህዝቧን እያስጨነቀ ያለው የወያኔ አገዛዝ የፀረ ሽብርተኝነት ህግን ከለላ በማድረግ በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፤ እጅግ የከፋ ደረጃ በመድረሱ ነው።
በሰላማዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ የመንግስት ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ሰላማዊ ዜጎችን አግባብ ባልሆነና ባልተጨበጠ ክስና ዉንጀላ ማሰር፣ አፍኖ መሰወር፣ ንብረትን ማዉደምና መዉረስ እንዲሁም የአደባባይ ግድያ ባለፉት 22 የወያኔ የአገዛዝ ዘመናት የተለመዱ ተግባሮች ሆነዉ ቆይተዋል። 

Monday, 25 November 2013



Photo


የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ የፖለቲካ አመለካከትን መተቸት አይደለም፤ ከዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ወረድ ያሉ የጉልበታሙን ስርዓት የሥራ አፈፃፀሞችን ማብጠልጠልም አይደለም፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ስንክሳር መንቀስም… አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ (አል-ሀበሽ) መሆን ለፈተና፣ ለመከራ፣ ለሰቆቃ… መዳረጉ የወለደው ብሶት እንጂ፤ መመረር-ማምረር ነው፡፡ …ይህ የእኛ ዕጣ ፈንታ የሆነበትን ምስጢር መመርመር ነው፡፡
ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ታጣቂዎች እና በድጎማ የሚያድሩ የሀገሬው ተወላጆች በመሰረቱት የጥፋት ግንባር ጉልበታቸውን ገብረው፣ በላብ በወዛቸው በሚያድሩ ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ ወንጀል፣ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ በከባድ ሀዘን የሰበረ፣ በቁጭት ያንገበገበ አሳዛኝ ፍፃሜ ሆኗል፡፡


ፍትህ ያጣ ህዝብ ጭቆና በዛብኝ ብሎ ሃሳቡ መግለፅ እንዴት ወያኔ 

ሊያበሳጨው ይችላልን??????? እየተገረፍንና እይታሰርን ያለነው እኛ 

ወጣቶች ነን !!! 


ስንቶች ወንድማሞቻችን በኢህኣዴግ ጥይት እንደ ወጡ ቀርተዋል!!! ስለ 

መብታቸው ጥያቄ ስላቀረቡ ለምን በጥይት ወያኔ ይገድላቸዋል? ህገ 

መንግስቱ ይከበር እያለ የሚመፃደቅ ወያኔ ህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብቱ 

ለመጠቀም ሲሞክር መንግስት ለምን ዜጋ ለማሰር ይራራጣል? ህገ መንግስቱ 

ወያኔዎች የህዝብን ስሜት ለማንበብ የሚጠቀሙበት መሳርያ እንጂ ለህዝብ…      

Sunday, 24 November 2013




ሃገርና ሕዝብ በውጥረት በታመሰበት አምባገነን የህውሃት/ኢአዴግ/ ዘረኛ ስርዓት ከምስራቅ እስከ ምህራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ሃገሪቱን እንደ ብራና ወጥሮ የሕዝቡን ኑሮ ሲያከብድበት እያየንና እየተመለከትን ስርኣቱን ለመታገል በየትኛውም መልኩ የተዋቀርን ድርጅቶች ሳንጀምር እየጨረስን ወይም እራሳችን ስላዋቀርነው ፓርቲ፣ ድርጅት ወይም ሸንጎ ሳንመረምር ሌሎች ስለሚደክሙበትና ስለሚለፉበት ትግል መፃዪ እድል እየተነበይን እርስ በእርስ ስንናከስና ስንጣረዝ የዘረኛውን የህውሃት እድሜ አበርክተን እዚህ አድርሰነዋል፡፡
በዚህ እኩይ የህውሃት ስርዓት መጀመሪያ ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል በራስ ተነሳሺነት ተዋቅረው እየተንቀሳቀሱ ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች አላማና ግባቸውን ለማስፈፀም የሰላማዊ ትግል መርሆችን ተግባራዊ ለማደረግ አንድም በራሳቸው የውስጥ ችግር ምክንያት፣ በዋነኝነት ግን ስርዓቱ ካለው ተፈጥሮዊ ባህሪ አንፃር ከሕዝብ ጋር ያለው ትስስርና በሕዝብ ላይ የሚፈፅመው የመልካም አስተዳደር ችግርም ሆነ የሰብሃዊ መብት አያያዝ እንዲሁም ሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ስላሉበት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለተደራጁ  ፓርቲዎች  ነፃነት ሰጥቶ ሞቱን ማፋጠን አይፈልግም፡፡ ስለዚህም ነው በሰላማዊ መንገድ የመታገያ መንገዶችን ሁሉ ዘግቶ በጥቂት ቁርጠኛ ታጋዮች ላይ እርምጃ እየወሰደ ትግሉን እያሽመደመደ ያለው፡፡ በሰላማዊ መንገድ እታገላልሁ የሚል ድርጅት አባላቱን አሰባስቦ አላማውን ማስረፅ ካልቻለ፣ በህዝብ ላይ የሚፈፀመውን ማንኛውንም በደል በመቃወም የሕዝብን ድምፅ ለማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ካላካሄደ፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን የሚያዘጋጅበት ቦታ ማግኘት ካልቻለና ይህንንና ይህንን የመሳሰሉ ህገ-መንግስታዊ የሰላማዊ ትግል መብቶቹን በወያኔ ስርዓት ከተቀማ እንዴት ነው ትግሉን ጫፍ ማድረስ የሚቻለው የሚል ጥያቄ ማሰነሳቱ አይቀርም፡፡

Saturday, 23 November 2013

ሰው ለመምሰል የሚሞከርበትን ቀን ለመሆን ቢማርበት 

ያለጥርጥር መሆን ይችላል  

ለመሆን የሚደረግ ልምምድ ትምህርት ሲባል,


ለመምሰል የሚደረግ ጥረት ግን 


በራስ ካለመተማመን እና ከበታችነት ስሜት


 የሚመነጭ ክፉ በሽታ ነው ::

Friday, 22 November 2013

የማይታከም ሕመም...

ያልታየን አሟሟት- ባንተ አይቼ
ሞትህን በቁሜ ሞቼ
ሲገድሉህ የተሰበረ ቅስሜ
እስካሁን አልtጠገነም ህመሜ
ሲገሉሽ ሞቼ ነው የከረምኩ
ከስቃይሽ እኔም አልተረፍኩ
ይህንን የናንተን አበሳ
ልጽፈው ብዬ ብነሳ

ሰማያዊ ፓርቲ፣ የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል!!

ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የሳውዲ መንግስት እያደረሰ ያለውን እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ በመቃወም እና ህይወታቸው ላለፈ፣ ለተደበደቡ እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ህዝቡ ሃዘኑን እንዲገልጽ በመጪው እሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ፣ የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል!!

ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የሳውዲ መንግስት እያደረሰ ያለውን እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ በመቃወም እና ህይወታቸው ላለፈ፣ ለተደበደቡ እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ህዝቡ ሃዘኑን እንዲገልጽ በመጪው እሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡

www.zehabesha.com

ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ. የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ

 
በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡
ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

Monday, 18 November 2013

በዜጎች ሰቆቃ ፕሮፓጋንዳ ለምን?

በፕሮፓጋንዳ የተለከፈ ፓርቲና መንግስት
ግርማ ሠይፉ ማሩበኢትዮጵያ ሀገራችን ፓርቲና መንግሰት መለያየት አሰቸጋሪ እንደሆነ ከተረዳን ውለን አድረናል፡፡ ለዚህም ነው መንግሰት የሚባለው አካል ሁል ጊዜ ግዴታውን በሚወጣበት ጊዜ አብሮ ፕሮፓጋዳ የሚጨምርበት፡፡ ሰሞኑን ግን ቅጥ ያጣ የፕሮፓጋዳ ርዕስ ሆኖ ያገኙሁት ደግሞ በሳውዲ ሀረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ በደረሰው ግፍ፣ ሰቃይ፣ መከራና ሞት ጎን ለጎን የኢትዮጵያ መንግሰት ችግሩን ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት የገዘፈ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻና ነውረኝነት የተሞላበት ዘገባ ነው፡፡ማፈሪያው የኢትዮጵያ ቴሌቪዝን እና ፕሮግራም ሰሪዎቹ (አሁን ደግሞ ዜና አንባቢዎቹ ጭምር ድምፀታቸው ሲሰማ የድል ብስራት የሚነግሩ ነው የሚመስሉት) በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው የሚያስተላልፉት ዘገባ ተጎጂዎቹ ህገ ወጥ ስለመሆናቸው እና በመንግሰት በጎ አድረጊነት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሚያብስሩ ናቸው፡፡ ይህን ፅሁፍ ሳዘጋጅ በስቃይ ላይ ከሚገኙት ኢትዮጵያዊያን አሰር ከመቶ እንኳን የሚሆኑት ወደ ሀገራቸው መግባት ባልቻሉበት ሁኔታ ዕድል አግኝተው መመለስ የቻሉት ዜጎች የመንግሰትን ሰኬታማ እንቅስቃሴና ችሮታ እንዲያወድሱ እየተደረገ ነው የሚገኘው፡፡ የሚያሳዝነው ከሳምንት በላይ የሚላስ የሚቀመስ አጥተው በስቃይ ላይ የሚገኙ ዜጎችን እሮሮ እየሰማን ባለንበት ወቅት በኤምባሲው ጥረት በአንድ ቀን ያለ ምንም ችግር መግባቱን የሚገልፅ ተጎጂ ማቅረብ ችግሩን ለማቅለልም ሆነ የኢትዮጵያ ኤምባሲን ትጋት ለማሳየት አይረዳም፡፡ ይልቁንም ይህ ተፈናቃይ የተሰራው ፍሪዝ ፀጉሩ ሳይበላሽ በአንድ ቀን ሊመለስ ከቻለ በእድል ወይም ከሹሞች የአንዱ ዘመድ ሆኖ መሆን ይኖርበታል፡፡
በጣም የሚያስገርመው ይህ ሚዲያ የኢትዮጵያ መሆኑን የሚያጠራጥር ነው፡፡ ይህ ፕሮግራም የሚቀርበው በአማርኛ ባይሆን ዝግጅቱ ባለቤት የሳውዲ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር መስሪያ ቤት ነው የሚመስለው፡፡ ዜናው ሲጀምር “በህገወጥ መንገድ ሳውዲ ገብተው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ….” ብሎ ይጀምራል፤ አነዚህን ዜጎች ወደ ህገወጥ ስደት የደራጋቸው መቼም ደርግ ወይም ንጉሡ አይደለም፡፡ ለእነዚህ ወጣቶች በማንኛውም ሁኔታ ሀገራቸውን ለቀው እንዲሄዱ በቀጥታም በተዘዋዋሪም የሚገፋው ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያለው መንግሰት እና መንግሰት የሚከተለውን ፖሊሲ የቀረፀው ፓርቲ ነው፡፡ ደርሶ ግፍ የደረሰባቸውን ዜጎች ጥፋተኛ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት በታሪክ ፊት ተጠያቂ ያደርጋል እንጂ አንድም ውሃ የሚቋጥር ውጤት አያመጣም፡፡

ህዳር 9 የ ሚከበረውን የ ፀረ-ባርነ ት አመፅ ቀን አስመልክቶ  
ከኦሮሞ የ ወጣቶችን ነ ጻነ ት (ቄሮ) የ ተሰጠ መግለጫ  
ባለፈው አንድ አመት (ከህዳር 2012 እስከ ህዳር 2013) ውስጥ የ ታሰሩ፣ የ ተገ ደሉና የ ደረሱበት ያልታወቀ የ ኦሮሞ ልጆችን በተመለከተ፤
የ ኦሮሞ ህዝብ ለወያኔ አገ ዛዝ አንድም ቀን ፍቃደኛ ሆኖ አያውቅም፡ ፡ በመሆኑም ባለፉት 21 ዓመታት ይህን ጨቋኝ ስረዓት በመቃወም ብዙ መስዋትነ ትን ከፍሏል፡ ፡ በኦሮሚያ ውስጥ የ መብት ጥያቄ የ ሚያነ ሱትን በየ ጊዜው አድኖ ማሰርና ማፈን የ ወያኔ መንግስት የ አስተዳደር ስረዓት ባሕል እንደሆነ ይታወቃል፡ ፡
ከህዳር 9/2012 እስከ ህዳር 9 2013 የ ፀረ-ባርነ ት አመፅ እያካሄዳችሁ ነው ተብለው በርካታ ቁጥር ያላቸው ኦሮሞዎች እስር ቤት ውስጥ የ ታፈኑ ሲሆን ገ ሚሶቹ ደግሞ የ ተገ ደሉና የ ደረሱበት ያልታወቁ ናቸው፡፡ ባጠቃላይ በዚህ አንድ አመት ውስጥ በርካታ የ ፀረ-ባርነ ት አመፆች በመላው አገ ሪቷ ተካሂዷል፡ ፡ ወያኔም እስራትና ግድያ ሲፈፅም ነ በር፡ ፡ በዚህ አመት ውስጥ ለኦሮሞ ነ ጻነ ት ሲታገ ሉ የ ታሰሩ፣ የ ተገ ደሉና የት እንደደረሱ ያልታወቁትን ለማስታወስና በአለም ላይ የ ሚገ ኘው ብሔረሰባችን የ ታጋዮቻችንን መብት ለማስከበር በሁሉም ቦታ እንዲፋለም የ ኦሮሞ የ ወጣቶች ነ ጻነ ት ንቅናቄ የ ታሰሩትን፣ የ ተገ ደሉትንና የት እንደደረሱ የ ማይታወቁትን መችና የት እንደታሰሩ ችምር መዝግቦ እንደሚቀጥለው አቅርቧል፡፡
በህዳር 11 2012 ምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጄሬ ወረዳ ውስጥ የ ሀገ ር ባለቤትነ ትን የ ሚመለከቱ ጥያቄዎች ጠይቃችኋል ተብለው ከስራ የ ተባረሩ የ ኦሮሞ ልጆች፡ -
1. አቶ ግርማ አራርሳ - የ ኤጄሬ ወረዳ ረዳት የ እንሰሳት ሀኪም 2. አቶ አበበ ግዲራ - የ ኤጄሬ ወረዳ ረዳት የ እንሰሳት ሀኪም 3. አቶ ደቀባ ተፈራ - ረዳት የ እንሰሳት ሃኪም
በኢሉባቦር ዞን ጮራ ወረዳ የ ተጠየ ቁትን የ መብት ጥያቄዎች ከኦነ ግ ጋር በመሆን እያቀናጀ ነው ተብሎ መምህር አበበ ተካ ህዳር 14/2012 እ.አ.አ ወያኔዎች አፍነ ውት እስር ቤት ወስደውታል፡ ፡
ህዳር 15/2012 እ.አ.አ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተከታታይ ሲነ ሱ ከነ በሩት የ መብት ጥያቄዎች ጋር ተያይዞ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለወያኔ መንግስት ጥላቻ አላችሁ ተብለው ከዩኒቨርሲቲ የ ተባረሩ የ ኦሮሞ ልጆች፣ -

Thursday, 14 November 2013

የብአዴን ከፍተኛ ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ምክንያት 

ንትርክ እና ጭቅጭቅ ተከስቶ እንደነበር ተጋለጠ 

የብአዴን ከፍተኛ ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ምክንያት ንትርክ እና ጭቅጭቅ ተከስቶ እንደነበር ተጋለጠ  በሙስና ሰበብ ተለጥፎባቸው በእስር ላይ በሚገኙት የወያኔ ቱባ ባለስልጣናት ዙሪያ በተደረገ ውይይት ላይ በባለስልጣናት መሀከል ንትርክ ተፈጥሮ መሰንበቱን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ያገኘነው ጥቆማ ገለጸ፡፡ 

        የብአዴን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዳይሬክተር በሆነው በመላኩ ፈንታ ዙሪያ በተነሳ ውይይት አንዳንድ የብአዴን ከፍተኛ ካድሬዎች ሞራል እና ስነ ምግባርን ያልተከተለ ክስ ነው በሚል ባነሱት ጥያቄ ምክንያት ንትርክ እና ጭቅጭቅ ተከስቶ እንደነበር ተጠቆመ፡፡ ከታሰረ ሁለት ወር በሁዋላ ክስ በተመሰረተበት በመላኩ ፈንታ ላይ ከቀረቡት ክሶች መሀከል የሰው ሚስት አፋትቶ አማግጦዋል በሚል የቀረበበትን ክስ ከፍተኛ የብአዴን  ካድሬዎች ሞራልን የሚነካ ...ስነ ምግባርን 
ያልተከተለ…ምክንያታዊ ያልሆነ….ከጀርባው ተልዕኮ ያለው….ክስ በመሆኑ እርማት ሊደረግ ይገባል በሚል ጥያቄ ያነሱ ቢሆንም ነባር እና በእድሜ የገፉት የህወሀት ባለስልጣናት ግን  ይህን ማለት ሙስናን እንዋጋለን ብለን ቃል የገባነውን እንደመሻር የሚቆጠር በመሆኑ ጥያቄው ተገቢ ያልሆነ ከመሆኑም በላይ አንዳንዶቻችሁ በጥቅም የተሳሰራችሁ መሆናችሁን ደርሰንበታል በማለት የማስደንገጫ ምላሽ እንደሰጧቸው ከደረሰን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ጥቆማ ለመረዳት ተችሎዋል፡፡ 

         መለስ ከሞተ በሁዋላ የሕወሀት ሰዎች እርስ በርስ ተከፋፍለው እየተፋለሙ በነበረበት ወቅት ብአዴን አንሰራርቶ ለጥቂት ግዜ የበላይነቱን ለመያዝ እየተንፈራገጠ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ኢህአዴግ 9ኛ ጉባኤውን በባህርዳር ላይ ባደረገበትም ወቅት የብአዴኖች ሰዎች ልብ አግኝግተው አንዳንድ ጉዳዮችን ያለ ፍርሀት ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል።  

         የግብርና ሚኒስትሩ የብአዴኑ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ተፈራ ደርበው ግብርናን አስመልክቶ በአሁኑ ሰዓት የግብርና ፖሊሲ ብለን እየተንቀሳቀስንበት ያለው መንገድ ከአርሶ አደሩ ጋር ያልተመጣጠነና ተገቢ ያልሆነ ከመሆኑም በላይ የቀረጽነው ስትራቴጂ የተሳሰተ ነው በማለት በይፋ የወያኔን ግብርና መሪ ፖሊሲ እያብጠለጠለ በጉባኤው ላይ መናገሩ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ የኤርትራ ተወላጁና የመለሰ ቀኝ እጅ የሆነው  በረከት ስምኦንን ጨምሮ የወያኔ ባለስልጣኖች አባይ ጸሀዬ …አባይ ወልዱና ሌሎቹም ተረባርበው ተፈራ ደርበው ባቀረበው አስተያየት ላይ ውርጅብኝ ያዘነቡበት ከመሆኑም በተጨማሪ የቀረጽነውና በስራ ላይ እየተረጎምነው ያለው የግብርና መሪ ፖሊሲ የአስፈጻሚው ችግር እና የአርሶ አደሩ ስንፍና ነው በማለት መሳደባቸው ይታወሳል፡፡   
  
          የፍትህ ሚኒስትሩ ብርሀን ኃይሉም በበኩሉ የተደራጁ ክሶች በአግባቡ እንዳይወሰኑና እንዳይታዩ በአንዳንድ የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት ትዕዛዝ እንዲዘጉና እንዲዳፈኑ በመደረጉ ስራ መስራት አልቻልንም በማለት በጉባኤው ላይ በይፋ መናገሩም ይታወቃል፡፡

በሳውዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ላለው ጥቃት 

ተጠያቂው ወያኔ ብቻ ነው


ወያኔ በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ዓም ጀምሮ በአገራችንና በወገኖቻችን ላይ ከፈጸማቸው በርካታ ወንጀሎች አንዱ በህጋዊ መንገድ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን ለባርነት ወደ አረብ አገራት በመላክ የአገራችንን መልካም ዝናና የህዝባችንን ክብር ያዋረደበት ተግባር ነው::
በወያኔ ንግድ ድርጅቶች ዋና ተዋናይነት ተመልምለው ለባርነት ሥራ የሚላኩትን ዜጎች በገፍ ስትቀበል የኖረቺው ሳውድ አረቢያ የሥራ ፍቃድ ያለቀባቸውን ከአገሯ ለማባረር ሰሞኑን በወሰደቺው የማዋከብ እርምጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን እየተደበደቡና ጎዳና ላይ እየተጎተቱ እሥር ቤት ታጉረዋል፤ ገንዘባቸውን ተዘርፈዋል፤ ከፖሊስ የሚደርስባቸውን ድብደባና እንግልት ለመቋቋም የሞከሩት በግፍ ተገድለው አስከሬናቸው ጎዳና ላይ ተጥሎሏል:: በርካታ ወጣት እህቶቻችን ደግሞ በአምስትና ስድስት የአረብ ጎረምሳ ወሲብ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ለአካልና መንፈስ ጉዳት ተዳርገዋል::
ይህ ሁሉ ሲሆን በአባይ ግድብ ግንባታ ሥም ገንዘብ ለመሰብሰብ ቦንድ ግዙ እያለ የሳውዲ ነዋሪ ሲጨቀጭቅ የኖረው በሳውዲ የወያኔ ኤምባሲም ሆነ አዲስ አበባ የሚገኙ ቅምጥል አለቆቹ ጥቃቱን ለማስቆም ድምጻቸውን ለማሰማት አለመፈለጋቸው ብቻ ሳይሆን ጥቃቱን ያደረሰውን የሳውዲ መንግሥት እርምጃ እውቅና የሚሰጥ መግለጫ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲህ መሰጠቱ እጅግ የሚያሳዝንና ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በመላው አረብ አገር በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው የባርነት ስቃይ በፋሺስት ጣሊያን ዘመን በወገኖቻችን ላይ ከተፈጸመው የከፋና በተለይ በሴት እህቶቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ እንደ አገርና እንደ ህዝብ የገባንበት ውድቀትና ውርደት ማሳያ ነው ብሎ ያምናል::
ስለዚህ ይህንን ውርደት ማስቆም የምንችለው ለዚህ ሁሉ መከራና ውርደት የዳረገንን የወያኔንሥርዓት ታግለን በማስወገድ በምትኩ ለአገሩና ለህዝቡ ፍቅር ያለው፤ በያንዳንዱ ዜጋ ላይ የሚደርሰው መከራና ስቃይ የሚቆረቁረው፤ አገር ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጥሮ ለባርነት ሥራ ወደ ውጪ የተላኩትን የሚሰበስብ መንግሥት ማቋቋም ስንችል መሆኑ ታውቆ ወያኔን ለማስወገድ የተጀመረውን ትግል በተለይ ወጣቱ የህብረተሰባችን ክፍል በነቂስ እንዲቀላቀል የተቀረውም ህዝባችን አቅም የፈቀደውን ሁሉ እንዲያደርግ ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል::
በመጨረሻም ምንም እንኳ በተለያዩ አረብ አገሮች በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ላለው መከራና ስቃይ ዋና ተጠያቂው ዜጎችን በህጋዊ መንገድ ለባርነት ከላከ ቦኋላ ጥቃት ሲፈጸምባቸው መከላከል ሳይፈልግ ዝም ብሎ እየተመለከተ ያለው የወያኔ አገዛዝ መሆኑ ባያጠያይቅም፣ የሳውዲ አረቢያም ሆነ ሌሎች አገሮች ተቆርቋሪ በለላቸው ዜጎቻችን ላይ የሚፈጽሙትን ወንጀል በአሰቸኳይ እንዲያቆሙና ተጠያቂዎቹንም ለህግ እንዲያቀርቡ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄን አቅም የፈቀደውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሁሉ ወያኔን ከማስወገድ ትግል ጋር አጣምሮ እንደሚገፋ ይገልጻል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄን የህዝብ ግንኙነት
November 12, 2013

ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን


በንቅናቄዓችን ፀሐፊ እና በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራር አባላት ላይ የተቃጣው ረዥም ጊዜ የወሰደ የግድያ ሴራ መክሸፉ አስደስቶናል። ይህ ሴራ የወያኔ የስለላና የግድያ ኃላፊዎች በሆኑት ጌታቸው አሰፋ እና ጸጋየ በርሄ የቅርብ ክትትል የተመራ፤ የአሻንጉሊቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እውቅናና ይሁንታ የተሰጠው፤ ወያኔ ከፍ ያለ ተስፋ የጣለበት ሴራ ነበር።
“ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም” የተሰኘው ይህ በወያኔ የመጨረሻ ከፍተኛው አመራር የተመራው ሴራ ስለወያኔ ውስጣዊ አደረጃጀት ጠቃሚ መረጃዎችን ሰጥቶናል። ከዚህም በተጨማሪ የወያኔ ሹማምንት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት፤ ከአመት በኋላ ስለሚደረገው ምርጫ ውጤት፤ ለሰላዮቻቸው ስለሚሰጡት ጉርሻ መጠን፤ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ተስፋ ከጣሉበት ቅጥረኛ ነብሰ ገዳያቸው ጋር ካደረጉት የስልክ ንግግሮች ማድመጥ ይቻላል። ይህ ለበርካታ ጥናቶች በግብዓትነት ሊውል የሚችለውን በድምሩ ከስምንት ሰዓታት በላይ የሚፈጀው የስልክ ንግግር ቅጂ በሕዝባዊ ኃይሉ የመረጃ ክፍል አማካይነት ለሕዝብ በኢንተርኔት በነፃ ተለቋል። በአጋጣሚውም የወያኔ ገበና ተጋልጧል።
በአንፃሩ ደግሞ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተደራጀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቢሆንም ምን ያህል ወያኔን እንቅልፍ እንደነሳ ተጨባጭ ማስረጃ ሆኗል። ይህ ለነፃነት ታጋዮች ከፍተኛ የስነልቦና ብርታት የሚሰጥ ነገር ሆኖ ተገኝቷል።
በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተቃጣበትን ጥቃት ከማክሸፍ በተጨማሪ የወያኔን ገበና ማጋለጥ በመቻሉ የመጀመሪያው ሁነኛ ድል ተቀዳጅቷል።
ግንቦት 7 : የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” አፕሬሽንን ላከሸፉ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት ይገልፃል። ለወደፊቱም ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊደርሱ የሚችሉ መሆኑን በመገንዘብ የመከላከል ብሎም የማጥቃት ኃይሉን እንዲያጠናክር ይመክራል።
የንቅናቀዓችን እና የሕዝባዊ ኃይሉ አመራርና አባላት ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ ናቸው። “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ትግላችን ይገታ ነበር ማለት አይደለም። ትግላችን መስዋዕትነትን የሚጠይቅ መሆኑን እናውቃለን። ጓዶች ሲወድቁ ሌሎች ሺዎች አርማቸውን አንስተው ትግሉን ይቀጥላሉ።
ትግሉ የሚጠይቀንን መስዋትነት ከፍለን ወያኔን ከሥልጣን አስወግደን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት የሆነባት ኢትዮጵያ እንደምትኖረን እርግጠኞች ነኝ።

ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን።
ድል ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
November 12, 2013

Monday, 11 November 2013

ጅል መንግስት የጅል ህዝብ ውጤት ነው ! (አሌክስ አብረሃም)

የሳዑዲ ህዝብ እንዴት አብሮን ይቆይ ይሆን ??? እንተያያለና !!! ብድር በምድር !!!
ሰሞኑን በሳውዲ ህዝብና መንግስት እየተፈፀመ ያለውን ያልሰለጠነ እና ኋላ ቀር ድርጊት በርካቶች እያወገዙት ቢሆንም አንዳንዶች ግን እርምጃው ልክ ነው የሚል አስተያየት ሲሰጡ እየሰማን ነው …. የሚገርመው ደግሞ እነዚህ አስተያየት ሰጭወች ኢትዮጲያዊያን መሆናቸው ነው !
የአስተያየት ሰጭወቹ መከራከሪያ ቃል በቃል ኢትዮጲያዊያን (አበሾች) ሳውዲን አቆሽሸዋታል ሌብነት ሽርሙጥና መጠጥ መቸርቸር በአበሾች ተስፋፍቷል ይባስ ብሎም አበሻ የቤት ሰራተኞች አሰሪወቻቸውን በግፍ እየገደሉ ነው የሚል ‹‹በደፈናው›› ሃሳብ ያቀርባሉ ! ቀጥለውም የሳውዲ መንግስት ሰባት ወር ታግሶ ህጋዊ እንዲሆኑ ለምኗል አስታሟል (እንደውም ትእግስቱ በዝቷል) አይነት ሃሳብ ይመርቁበታል ፡፡
እናም ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ዜጎች ቢጉላሉ ቢታሰሩ ቢንገላቱና ቢገደሉ ጭምር የሳውዲ መንግስት ተጠያቂ አይደልም በማለት ጭፍን ፍርዳቸውን ያሳርጋሉ !
እናተ የባእድ ከበሮ የምትደልቁ ከንቱወች !
Ethiopians are detained in Riyadh's Manfuhah neighbourhood
Saudi police in Riyadh clash with migrant workers 
BBC
November 11, 2013
At least two people have been killed and scores wounded as Saudi police clashed with protesting foreign workers in a district of the capital, Riyadh.
A police statement said hundreds of people were arrested in the Manfuhah neighbourhood.
Later on Sunday, thousands of mostly African workers gathered in the capital to prepare for repatriation.
Last week police rounded up thousands of migrant workers after an amnesty linked to new employment rules expired.
Yemenis return
One of the two people killed was a Saudi while the other was unidentified, police said. About 70 others were injured and there were some 560 arrests, officials added.
However, Ethiopian Foreign Affairs Minister Tedros Adhanom said he had information that three Ethiopian citizens had been killed, one last Tuesday and two in the latest clashes.
He said Addis Ababa had formally complained to Riyadh.
"This is unacceptable. We call on the Saudi government to investigate this issue seriously. We are also happy to take our citizens, who should be treated with dignity while they are there," he said.
Police said they intervened on Saturday after foreign workers in the Manfuhah district rioted, attacking Saudi and other foreign residents with rocks and knives.
Vigilante Saudi residents in Manfuhah reportedly joined the fighting and even detained some Ethiopians.
Manfuhah is home to many migrants, mostly from east Africa.
On Sunday, witnesses said police surrounded the district while units from the National Guard and special forces were sent in.
Hundreds of African migrants reportedly surrendered to police.
A long line of buses took the migrants to temporary housing along the airport road in Riyadh.
Last Monday, the authorities began rounding up thousands of illegal foreign workers following the expiry of a seven-month amnesty for them to formalise their status.
Nearly a million Bangladeshis, Indians, Filipinos, Nepalis, Pakistanis and Yemenis are estimated to have left the country in the past three months.

Foreign workers wait for a taxi as they leave the Manfuhah neighbourhood of Riyadh. 10 Nov 2013 Hundreds of foreign workers were leaving the Manfuhah district on Sunday
More than 30,000 Yemenis have reportedly crossed to their home country in the past 10 days alone.

Four million other migrants obtained work permits before last Sunday's deadline.
Saudi Arabia has the Arab world's largest economy, but authorities are trying to reduce the 12% unemployment rate among native Saudis.
An estimated nine million migrant workers are in Saudi Arabia - more than half the workforce - filling manual, clerical, and service jobs.



Source   http://www.oromoliberationfront.org/sbo.html
Afaan Oromoo fi Afaan Amaaraa

PLEASE HEAR IT????
Nov 10, 2013
Nov 6, 2013
Nov 3, 2013
Oct 30, 2013
Oct 27, 2013
Oct 23, 2013
DO YOU KNOW

                                                                               OLF Major Policies



On Peaceful Resolution of Conflicts in Ethiopia

The root cause of political problems in Ethiopia is national oppression by the Ethiopian empire state and refusal by the state to respect the rights of oppressed peoples to self-determination. The current Ethiopian regime has recognized in its constitution the right of self-determination with serious limitations imposed on the exercise of the right. The aspiration of the people to regain the fundamental freedom, which was snatched from them by brutal conquest, is supported by the principle enshrined in the UNO Charter and related international instruments. The Oromo and other oppressed peoples are endowed with the right to decide the form of sovereignty they want, whether on their own or in a union with others on the basis of freely expressed consent of all concerned parties. To bring genuine peace and stability imperial domination must be brought to an end. To realize this objective readiness by all concerned parties is necessary to solve the political problem peacefully. Policy of shelving political problems must cease. OLF is ready to go an extra mile in search of peaceful resolution of the political crisis in Ethiopia. The OLF is ready to contribute towards any meaningful peace effort, as it did in the past, to reach at a comprehensive settlement to bring peace to all peoples of the empire.

On Armed Struggle

The protracted armed resistance under the leadership of the Front is an act of self-defense exercised by the Oromo people against successive Ethiopian governments, including the current one, who forcibly deny their right to self-determination. The OLF armed resistance targets the government's coercive machinery, not innocent civilians. The OLF has an unswerving anti terrorism stand and opposes terrorism as means of struggle to achieve the right of the Oromo people. The Organization considers terrorism as act of desperation. Therefore, anti terrorism remains a core policy of the organization.

HAVE YOU NOTICED THIS BEFORE???
Oromia Speaks

Article from Oromia Speaks Vol. 10 Issue 1



EPRDF Replaces Public Enterprises with Political Party Businesses



The Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Front (EPRDF) dominating Ethiopia, has been fully engaged in privatizing public enterprises, organized by the previous regime of the Military- Socialist Government of Ethiopia, since it snatched power by force in 1991. The Privatization Program and building of a free market economy was initiated by international donors, spearheaded by the IMF, as a major conditionality to mobilize foreign financial resource for the development of Ethiopia. The aim of a Privatization Program is to restrict the government’s role in economic production and distribution so as to create a level playing field for the private sector and development of a competitive market economy.

However, what the EPRDF government is doing is a mockery of the principles and hoodwinking the international donors and democratic states. Parallel to the privatization of the Ethiopian public enterprises, the EPRDF is busy building its Economic Empire with the instrumentality of political patronage to inherit the lion’s share of the previous socialist government as a major actor in the Ethiopian economic activity. The EPRDF under the hegemonial leadership of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) is engaged in agriculture, mining, industry, trade, construction, transport, finance, and service activities to be an elephant economic entity in Ethiopia so as to be able to strangulate private sector economic development as well as progress of democratic political process.

The EPRDF/TPLF establishes and controls its economic conglomerates through the Para-NGOs, organized for specific purposes over its political life. Among the TPLF economic agencies, the Relief Society of Tigray (REST) was created in 1978 and presented to the international donors as NGO, independent of and separate from the TPLF. Whereas in reality it is a TPLF-auxiliary, secretly headed by a TPLF-Central Committee member. The main task of REST was to tap the resources of the international NGO- community, which was reluctant to deal directly with an armed guerrilla movement for relief and development in TPLF controlled parts of Tigray. The input of external donors through REST into TPLF-held areas of Tigray was considerable and had several and crucial benefits for the TPLF. Due to the international donor support, REST not only could provide much needed relief to the war and drought affected civilian population of Tigray but also could build up its own financial assets in an impressive manner. The extent of this build up, as well as its material property, particularly a huge transport fleet, was carefully hidden from the donors .

When Tigray was liberated from the control of the government in Addis Ababa in 1988, the TPLF was faced with the challenges of developing Tigray. To cope with this challenge, the Tigray Development association (TDA) was created to mobilize resources from educated, wealthy, and pro-TPLF members of the Tigray Diaspora particularly in Europe and North America. Though it was assumed to be independent of the TPLF structurally, members of its Board of Directors are top TPLF political leaders.

After the end of the war, both REST and TDA, experienced a rapid organizational growth. REST formalized and further expanded its organizational structure and presence on the ground in Tigray whereas TDA consolidated and expanded its branches within Tigray and established new ones among the Tigray Diaspora in other parts of Ethiopia. Both organizations also tremendously increased their financial resources; REST mainly through immensely increased funding by international NGO and governmental aid-organizations; TDA mainly through an intensification of fund-raising campaigns backed up by the political power of the TPLF.

Finally, in 1995 the TPLF set up the Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFFORT). Legally, EFFORT is a non-governmental public charity in the form of a foundation. But it seems to be even more strictly controlled by TPLF than REST and TDA. The large majority of its Board of Directors members (7-8) are directly representing the TPLF.

Parallel to the post-war consolidation and expansion of the Para-NGOs, the TPLF begun to set-up legally private companies with high-ranking TPLF-members, and possibly some trusted private Tigrians close to the TPLF-leadership, fronting as shareholders.

“A Preliminary Survey of Ethiopian Non-governmental Business” shows that investment by the TPLF companies in the Ethiopian Economy runs into billions of dollars. For instance, some of the companies have started operations with staggering authorized initial investment capital as indicated below:

Mesebo Building Materials Manufacturing SC 240.00 million Br.
Almeda Textiles Manufacturing SC 180.00 million Br.
Sur Construction 100.00 million Br.
Trans-Ethiopia SC 100.00 million Br.
Dashen Brewery SC 60.00 million Br.
Wegagen Bank SC 60.00 million Br.
Dedebit Credit and Savings Institution SC 60.00 million Br.
Addis Pharmaceutical Production SC 53.00 million Br.
Sheba Tanery Factory SC 40.00 million Br.
Africa Insurance SC 30.00 million; Br.
Zeleke Agricultural Manufacturing SC 27.00 million Br.
Hiwot Agricultural Mechanization SC 25.00 million Br.
Meskerem Investment SC 20.00 million Br.
Beruh Chemical SC 20.00 million Br.
Tesfa Livestock Development SC 20.00 million Br.
Mega-net Corporation SC 10.00 million Br.
Express Transit Service SC 10.00 million Br.
Guna Trading House SC 10.00 million Br.

Nearly, all the companies mentioned above are located in Tigray except few, to create job opportunities for the people of Tigray, control supply and develop Tigray unevenly, while letting the other states deteriorate.
Moreover, trade enterprises have monopolized fertilizer trades in Ethiopia to control the huge majority of the farming population through the fertilizer credit system and denial of opportunity of purchase if a farmer is not loyal to the TPLF politically and cast ballots, if there is election. Companies engaged in coffee trade displace small traders and suppress suppliers’ prices at will. Dedebit Credit and Savings Institution SC also extends credit to poor peasants. To get the credit, primarily, a farmer should vote for the TPLF. Similar mechanisms of credit-cum-vote are being established in Oromia, Amhara, and the Southern Nations Nationalities and Peoples States for the same objectives. It is to suppress free and fair elections and ensure the invincibility of the TPLF/EPRDF.

Generally, the private sector in Ethiopia cannot compete with the government supported financially heavy party enterprises. It is an indirect socialist economic control, vote trading if there is democracy. If this state of economic operation is continued unabated, the TPLF/EPRDF will be the single dominant economic actor in Ethiopia by systematically killing all the private initiatives. It is to accomplish this grand design that the TPLF/EPRDF formulated a Revolutionary Democracy Development Strategy. Revolutionary Democracy is a precursor of socialism not a market economy.
If a free market economy is to flourish in Ethiopia, all the TPLF/EPRDF economic enterprises should be sold to the private sector and the party desists from engaging in economic activities. The IMF and the World Bank fully understand that the TPLF/EPRDF is moving towards a state controlled economy. The experts and the management don’t have the heart to tell them to change the course. The TPLF leadership knows how to deceive these two international organizations. The President of the World Bank had asked Prime Minister Meles Zenawi, at their discussion in Addis Ababa, to privatize these party enterprises. But Meles told him that the property doesn’t belong to the government of Ethiopia but captured from the enemy in fighting and it should remain the exclusive asset of the TPLF. It is amazing as to why the World Bank President did not insist that there should not be two governments in one country. If Meles resisted why didn’t he withhold assistance? It should be answered. The European Union also had reported against these unfair party economic swindling practices. Yet they are continuing to finance the EPRDF. Donors should insist on transparency to create level playing fields for economic actors and political operators.
OROMIA SPEAKS

ሰበር ዜና ሪያድ በወያኔው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የሚመራ የሎኡካን ቡድን ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ገባ ።

ሰበር ዜና ሪያድ በኢትዮጵያው ውጭጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የሚመራ የሎኡካን ቡድን ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ገባ ። ይህንንም ተከትሎ በህዝቡላይ ይተፈጸመውን ግፍ እና በደል ለማጣራት ከህዝቡ ጋር በኢትዮጵያ ሰአት አቋጣጠ ከቀኑ በአስር ሰአት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳርሻ ስብሰባ እንደሚደረግ ከኤንባሲው የደርሱን ሚስጥራዊ ምንጮች ገልጸዋል ። ይህን ተከትሎ ህዝብን ለሞት እና ለስቃይ ያበቁት አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን እና የጥቂት ዲፕሎማቶች የፈጸሙት ጥፋት በህዝብ እንዳይጋለጥ፡ ህዝቡ ከባለስልጣናቱ ጋር እንዳይገናኝ፡ኤንባሲው ስብሰባውን በሚስጥር ለታማኞቹ ማስተላለፉን የሪያድ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ



ቋንቋ ማንነትን እንደማይገልጽ በብርቅዬ ኢትዮጵያዊት አርቲስት EPRDF እና ጀሌዎቹ ቢገባቸው .............

“ፍቅርን እንደወረደ እሰብካለሁ” አርቲስት ሃኒሻ ሰለሞን

የባላገሩ አይዶል ባለቤት አብርሃም ወልዴ በክህደት ተከሰሰ

hanishaለማዘንም ለመደሰትም የቀረበች ናት። ስለዘርና ስለቋንቋ ያላት እምነት የሚለካው በፍቅርና በፍቅር ብቻ እንደሆነ ደጋግማ ትናገራለች። ቋንቋም ሆነ ዘር የማንነት መለኪያ እንዳልሆነ አጥብቃ ትከራከራለች። ፍቅርን እንደወረደ ከመስበክና ወገኖቿን የመርዳት ዓላማዋን ከማሳካት የሚበልጥባት ጉዳይ እንደሌለ አበክራ ትናገራለች። ገና ጀማሪ ብትሆንም ሙዚቃዎቿ ተወደውላታል የሚሉ እየበረከቱ ነው። እኔ ዘር የለኝም በሚል የሰፋ ሃሳብ ያለው ሙዚቃ ተቀኝታለች። ኢትዮጵያ የፍቅር ምድር እንድትሆን አብዝታ እንደምትሰራ ቃል በመግባት ከጎልጉል ጋር ቃለ ምልልስ አደረገችው አርቲስት ሃኒሻ ሰለሞን የምትኖረው ሎንዶን ነው። እንደሚከተለው ቀርቧል።hanisha7
በቃለ ምልልሱ ሃኒሻ ላይ በደል ፈጽሟል የተባለው የባላገሩ አይዶል ባለቤት አብርሃም ወልዴ ለቀረበበት ውንጀላ ምላሽ መስጠት ከፈለገ ዝግጅት ክፍላችን በደስታ እንደሚያስተናግደው ከወዲሁ ለመግለጽ ይወዳል። በተመሳሳይ በደል የደረሰባቸው አርቲስቶች እንዳሉ መረጃዎች ስላሉ ተበዳዮችም ሃሳባቸውን ቢሰጡ እናበረታታለን።
ጎልጉል፦ ከቋንቋ እንጀምር?
ሃኒሻ፦ ከስርአቱ እንጂ ከቋንቋ ጋር የሚደረግ ጸብ ለእኔ ግልጽ አይደለም። አይገባኝም። ቋንቋ መግባቢያ እንጂ የዘር መለኪያ ሚዛን አይደለም። አንድ ቋንቋ ግን አለኝ። እሱም ፍቅር ነው። ቋንቋዬ ፍቅር ነው ብዬ የዘፈንኩትም ለዚህ ነው። በጥንቃቄ ከታሰበ ከፍቅር በላይ ምንም ቋንቋ የለም። ፍቅርን፣ እንደወረደ እሰብካለሁ።
ጎልጉል፦ ስለ ብሔር ምን ትያለሽ?

“በሳዑዲ ኢትዮጵያዊ ህገ ወጥ ስደተኞች ሳንጃና ቆንጨራ መታጠቃቸውን አረጋግጠናል” አምባሳደሩ

(አምባሳደሩ በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ስም በሚያንቀሳቅሱት የአሰሪ እና ስራተኛ ኤጄንሲ ለሞቱት 3 ሴቶች ተጠያቂ ናቸው)
eth saudi
ኖቬበር 4 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የምህረት አዋጅ የግዜ ገደብ መጠናቀቅ አስመልክቶ ለተለያዩ የልማት ማህበር አባላት ኤምባሲው አርብ ኖቬምበር 1 2013 በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበር የሚገልጹ ምንጮች ስብሰባው በኢትዮጵያውያን ቆጨራ እና ሳንጃ መታጠቅ ዙሪያ ኤምባሲው ማህብረሰቡን ለመነጋጋር አጀንዳ ይዞ መቅረቡ ስብሰባው በጣም አሳፋሪ እና ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ለመወንጀል ሆን ተብሎ የታቀደ ከስም ማጥፋት ዘመቻ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ገልጸዋል።
በተለይ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን በወቅቱ ለተሰባስቢው ስለአጀንዳው ሲገልጹ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ አያሌ በባህር የመጡ ኢትዮጵያውያን በተለምዶ «ባህር ሃይል እየተባሉ የሚታወቁ» መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ጠቀሰው እነዚህ ህገወጦች የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያወጣውን ህግ ተከትሎ የሚወሰድባቸውን እርምጃ ለመከላከል ሳንጃ መታጠቃቸውን ኤምባሲው በመረጃ አረጋገጦል ብለው መናገራቸው በአብዛኛው ተሰብሳቢ ዘንድ ተቃውሞን ቀስቅሷባቸዋል። አምባሳደሩ በዚህ ዙሪያ ሰላማዊ ወገኖቻችንን በመወንጀል የሃገራችንን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት በኤምባሲ ደረጃ አጀንዳ ተይዞ ስብሰባ መጠራቱ ያበሳጫቸው ተሰብሳቢዎች የአምባሳደሩን ጤናማነት እስከ መጠራጠር መድረሳቸውን ምንጮቻን አክለው ገልጸዋል። ድጋፍ እናገኛለን ብለው የጠሯቸው ታማኝ የልማት ማህበራቱ ስራ አመራር የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ያቀረቡት ክስ ከምን ጭብጥ ተነስተው እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጦቸው ስብሰባው ላይ ወጥረው ይዘዋቸው እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች ስብሰባው ገና ከመነሻው በተሳታፊው ከፍተኛ ተቃውሞ አለመግባባቶች ተፈጥረው እንደነበር ይገልጻሉ፡፡
mohammed hassenአንዳንድ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን አባባል ያንገበገባቸው አስተያየት ሰጪ የቀረበው አንጀዳ ስህተት መሆኑንን ገልጸው ሴት እህቶቻችን ጉልበታቸውን ያፈሰሱበትን የወር ደሞዛቸውን ተነጥቀው ተደብድበው እና ተደፍረው በየጎዳናው ወድቀው የፍትህ ያለህ እያልን ጣረሞት እያሰማን ባለንበት የስደት አለም እኛው አጥፊ እኛው ገዳይ አረመኔ እና ጨካኝ ተብለን በተለያዩ ሚዲያዎች ስማችን ሲጠፋ እና የሃገራችን በጎ ገጽታ በማጉደፍ በባእዳን ጥላቻ የተቃጣብንን የስም ማጥፋት ዘመቻ አምባሳደሩ እንደ አንድ ሃገር መሪ ተወካይ መጋፈጥ ሲገባቸው የዝሆን ጆሮ ይስጥኝ ብለው ከርመው ዛሬ በድፍረት እኛ ፊት ቆመው እኛኑ ለመወንጀል መቃጣታቸው በጣም ያሳዝናል ብለዋል።
በሌላ በኩል አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ሲናገሩ አምባሳደር መሃመድ ሃሰንን ከእንግዲህ እንደማያውቋቸው ገልጸው ስለኢትዮጵያውያን ለመናገር የሞራል ብቃት የሌላቸው ከሳቸው ይልቅ በዲፕሎማት ደረጃ አንቱ የሚባሉ እንደነ አቶ መስፍን እና መሰል ዲሲፒሊን ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የመንግስት ተወካዮች ስለኮሚኒቲው ችግር ህዝቡን ማወያየት እንደሚገባቸው በአጽኖት ጥቀስ በኤምባሲው ዝርክርክ አሰራር የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የተሳናቸው ወገኖቻችን ላይ ለሚደረሰው ማንኛውም አደጋ አምባሳደሩ ሃላፊነትን መውሰድ እንደሚገባቸው በሰጡት አስተያየት ከተሰብሳቢው በተደረገላቸው የድጋፍ ጭብጨባ በወቅቱ የስብሰባ አዳራሹን ድባባ ለውጦታል።

በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉት 24 ተከሳሾች ክስ መሰማት ጀመረ

በገብረዋህድ ቤት በርካታ መሣሪያዎች ተገኝተዋል
Melaku-Fenta-Gebrewahid-Woldegiorgis
የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት እና ግብረ አበር ባለሀብቶች ላይ የመሰረተውን ክስ በፍርድ ቤት ማሰማት ጀምሯል። የኮሚሽኑ ዐቃቤ ህግ በተለይም በአንደኛው ተከሳሽ በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ መዝገብ ቁጥር 14356 ስር ባለው 11ኛ ክስ ውስጥ ተከሳሹ በትዳር ያለችን ሴት አስኮብልለዋል የሚል ክስ መስርቶባቸዋል።
ትናንት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክሱ ሲነበብ፤ 1ኛው ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታ የስራ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ለስራ ጉዳይ የመጣችን ሴት፤ ትዳሯን ፈታና በትዳር ውስጥ ያፈራቻቸውን ሦስት ልጆች በትና አብራቸው እንድትሆን አድርገዋል ሲል ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ከሷቸዋል።
ወ/ሮ መቅደስ ለማ የተባሉት እኚሁ ሴት የቀድሞ ባለቤታቸውን ንብረት የሆነውን ሳንክቸሪ ኢንተርናሽናል ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር በ2001 ዓ.ም የስራ ግብር ለመክፈል ወደገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሲሄዱ 144 ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸውና በዚህም ምክንያት አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለአንድ አመት ከ4 ወር መጉላላታቸውን ለማስረዳትና መፍትሄ ለማግኘት ወ/ሮ መቅደስ ለማ የአቤቱታ ደብዳቤ ይዘው ወደተከሳሹ ዘንድ በቀረቡበት ወቅት የፍቅር ግንኙነት መጀመራቸውን በክስ መዝገቡ ያትታል።
melakuበዚህም መሠረት ተከሳሽ የነበረውን ስልጣን መከታ በማድረግ ባለጉዳዩዋ ቀደም ሲል ከከፈሉት ብር ውስጥ አንድ መቶ ሺህ ብር ተመላሽ እንዲሆን አድርጓል፤ በትዳር ውስጥ ያለችን ሴትም አማግጧል ሲል የሙስና ክስ መስርቷል።
ዐቃቤ ህግ በዚህ ክስ ዝርዝር ውስጥ በተጨማሪነትም ተከሳሽ በጋብቻ ውስጥ ያለችን ሴት በመንግስት ተሽከርካሪና ነዳጅ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ክብረ በዓል ላይ እንድትገኝ ከማድረጉም በላይ ቀኑ በውል ባልታወቀበት ዕለትም፤ በጋብቻ ውስጥ የነበረችው መቅደስ ለማን በግል ሾፌሩ አማካኝነት ወደ ባህርዳር ከተማ እንድትሄድ በማድረግ ሰመርላንድ ሆቴል ለአንድ ሳምንት አብረው እያደሩ እና በሾፌሩ አማካኝነት ከተማ ውስጥ ተዝናንታለች ሲል፤ የተፈፀመው ወንጀል መንግስትና ህዝብ የጣለበትን አደራ ያለአግባብ የመጠቀም ሙስና ሰርቷል ይላል። (በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉትን 24 ተከሳሾች የክስ ሙሉውን ጭብጥ እነሆ)

ወያኔና አሸባሪነት ምንና ምን ናቸው ???


የወያኔ ጉጅሌ ሰሞኑን የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ በእጅጉ ሊያስቅ የሚችል ቧልት ላይ ተጠምዷል። የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ሳይቀር ህብረተሰቡን በየተቋሙና በየመኖሪያው እየሰበሰበ ስለሽብርተኝነት ማብራሪያና ገለፃ በመስጠት ዜማ ላይ ተጠምዷል።
የወያኔ የሽብረተኝነት ገለፃ ዘመቻ ሚስጥር ደግሞ ብዙ ምርምር የሚሻ አይደለም። የሀገራችን ሰዎች ዶሮ ጭራ ልታወጣው የምትችል የሚሉት አይነት ሚስጥር ነው። አላማው ነጻነት አማረኝ፣ እምቢ ዘረኝነት እና ቢያንስ መሰረታዊ ሰበአዊ መብቴ ይገባኛል በማለት መብቱን እየጠየቀ የመጣው ህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ታይቶታል።
የማእበሉ የመጀመሪያ ንቅናቄዎች ከወዲያ ወዲህ መታየት ጀምረዋል። የገለፀው ሽርጉድ ዋና አላማ ይህ መብቱን የሚጠይቅና አጎንብሶ መኖር የሰለቸው ህዝብ ለመብቴ የማደርገውን ትግል ሽብርተኛ ያስብለኛል ብሎ እንዲፈራና ይበልጥ እንዲያጎነብስ መሆኑ ነው። ይህን ደግሞ ህዝቡ አውቆታል። ሰሞኑን በአለምያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለገለፃው ለመጡ ካድሬዎች የሰጧቸው አጸፋዊ ገለጻ ይህንኑ ያሳያል፡፡
ሽብርተኝነት አንድና በነጻነትና በዴሞክራሲ ለመኖር የሚመኝና የወሰነን ህዝብ ሰላም በመንሳት የፖለቲካ አላማዪን አሳካለሁ ብለው የሚያምኑ ቡድኖችና ድርጅቶች የፖለቲካ መሳሪያ ነው። የወያኔ መሪዎች የሽብርተኝነት ትርጉም አልገባቸው ከሆነ ሰብስብ ብለው መሰዋእት ፊት ቢቆሙ ሽብረተኝነትን አፍጥጦ ሊያዩት ይችላሉ፡፡ ሽብርተኛው ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው።
ህዝቡ ፊት በቆሙ ቁጥር ግን ህዝቡ ሽብርተኞችን ያያል። ሰለባውን ለማስተማር መሞከር ለእናት ምጥ የማስተማር ያህል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ሁሉንም የዲሞክራሲና የሰላም ጥያቄ ሁሉ በጉልበትና ባፈና የደፈጠጠ አሸባሪ ቁጥር አንድ ወያኔ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ከሽብር ጋር የመረረ ችግር ላለባቸው ሀገሮች ሎሌነት ገብቶ ሌሎች ሽብርተኞችን ወደሀገራችን የሚጎትተው ራሱ ወያኔ ነው።
ዛሬ በማንም የባእድ አሸባሪ በህዝባችን ላይ ለሚደርስ ጉዳት ዋናው ተጠያቂ ወያኔ የሚሆነውም ለዚህ ነው። ለምእራብያውያን ጸረ ሽብር አጋራችሁ ነኝ እያልኩ ራሴ በምገዛው ህዝብ ላይ የምፈጽመውን ሽብር እንዳለ ያዩልኛል፣ ፍርፋሬም አገኝበታለሁ በሚል ስሌት የተገባበት መሆኑንም የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ቁጥሩ ትንሽ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡- ነጻነት የናፈቀህ፣ አጎንብሶና በገዛ ሀገርህ ተዋርዶ መኖር የሰለቸህ፣ በወያኔ ተሰደህ በባእድ ሀገር የምትሰቃይ፣ የምትሞት የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ወያኔዎች ከግፍ አልፈው ሊቀልዱብህ፣ በቁምህ ሊገሉህ፣ ሊከፋፍሉህ አይገባም። ወያኔ የፈሪ አብራሪ ነው። አሻፈረኝ ሲሉት እንጂ ቢሸሹለት በቃኝ ብሎ አይመለስም፡፡
ግንቦት 7 ንቅናቄ እንደሁልግዜው ዛሬም ወገን ሆይ፡- የሀገርህን ህልውና ለመታደግ ተነሳ፣ ተቀላቀለን፤ የመከራችንን ቀን አጭር እንደርገው ዘንድ ጸሃይ ሳትገባብን፣ ሳይመሽብን ኑ ተቀላቀሉን የሚለውን ጥሪ ዛሬም አጠናክሮ ያቀርብልሃል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
G7 October 18

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ የአመራር አባላትላይ ታቅዶ የነበረ የመግደል ሙከራ ከሸፈ።

በጠቅላይ ሚንስትር ተብየው ሃይለማሪያም ደሳለኝ እውቅናና ትእዛዝ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ታጋዮች በሚገኙበት ቦታ ድረስ በመሄድ አመራሩን ለመግደል ሙከራ ቢደረግም ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል ከፍተኛ ክትትል ሙከራው መክሸፉን ሕዝባዊ ሃይሉ ገለጸ። ይህ ልዩ ትእዛዝ ጥቅምት 30 2006 ዓ/ም ተፈጻሚ እንዲሆን እቅድ የነበረ ቢሆንም ሕዝባዊ ሃይሉ ጥቅምት 27 2006 ዓ/ም ሊያከሽፈው ችሏል። ዝርዝሩን ከዚህ ላይ ያዳምጡ   mp3 )

በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል


በወያኔ ግፈኛ ስርአት መከራቸውን ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን።
በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን።
ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው።
በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው።
ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

G7 November 7

Friday, 8 November 2013

Egypt and Ethiopia Disagree on Probe of Nile Dam Impact

The 6,000-megawatt Grand Ethiopian Renaissance Dam, set to be Africa’s largest when its completed in 2017, has raised concern in Cairo that it will reduce the flow of the Nile, which provides almost all of Egypt’s water. Ethiopia’s government has said it won’t pause construction or scale down the country’s most important development project. Sudan backs the dam, which will bring “many blessings and benefits for us,” Information Minister Ahmed Bilal Osman said in June.

‘Basic’ Analysis

In a June report, a group of international experts said Ethiopia’s analysis of the dam’s downstream impact during filling and operation was “very basic, and not yet at a level of detail, sophistication and reliability that would befit a development of this magnitude, importance and with such regional impact.” This week’s meeting was to discuss ways of acting on the report’s recommendations.
Egypt wants scientists from neutral countries to be involved in assessing issues including the dam’s dimensions, how it will be filled and discharged and “what will happen if it collapses,” Abdel-Moteleb said. The international experts’ report said that Ethiopia hadn’t presented analysis of the consequences of a dam collapse, although officials informed them a study was being undertaken.
Ethiopia and Sudan don’t think a panel with neutral representatives is needed to hire and oversee consultants to conduct studies recommended by experts in June, Fekahmed Negash, head of the Ethiopian Water Ministry’s Boundary and Transboundary Rivers Affairs Directorate, said by phone from Addis Ababa today. “The countries can handle it,” he said.
Officials will meet in the Sudanese capital again on Dec. 8 to try and resolve the issue, Alemayehu said.
Ethiopia is the source of 86 percent of the water that flows into the Nile, the world’s longest river that runs 4,160 miles through 11 countries from Burundi in the south to Egypt, where it empties into the Mediterranean Sea.
To contact the reporters on this story: Ahmed Feteha in Khartoum at afeteha@bloomberg.net; William Davison in Addis Ababa at wdavison3@bloomberg.net
To contact the editor responsible for this story: Antony Sguazzin at asguazzin@bloomberg.net
NOV 7 semayawi party