BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 28 November 2014

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለአዳር የሚቆይ ተቃውሞ በመስቀል አደባባይ ለማካሄድ የእውቅና ጥያቄ አቀረበ

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- ትብብሩ ህዳር 18 ለመስተዳድሩ ባስገባው የእውቅና ጥያቄ ፣ የተቃውሞ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ከህዳር 27 እስከ ህዳር 28፣ 2007 ዓም ለማካሄድ ማቀዱን ገልጿል።
የእውቅና ደብዳቤውን ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር፣ የከንባታ ህዝቦች ሊቀመንበርና የትብብብሩ ም/ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ፣ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የትብብሩ ፀኃፊ እና የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሲር በጋራ ማስገባታቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን” “ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”



“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡

Monday, 17 November 2014

እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ደብዳቤ መጻፏን ወያኔ አረጋገጠ


የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ለወያኔዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ደብዳቤ መጻፋቸውንና ወያኔም አቋሙን ግልጽ ማድረጓን የወያኔዉ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ተናገረ። ሬድዋን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባለፈዉ ማክሰኞ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዴቪድ ካሜሩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደብዳቤ መጻፋቸውን የተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ሰምቻለሁ ካለ በኋለ “ለምን ጻፉ ማለት አይቻልም፤ ጥያቄዉ መሆን ያለበት ምን መለሳችሁ ነው፤” በማለት የተለመደ የማጭበርበሪያ ቃላት ደርድሯል።

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ።


Imageኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ። በደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ አንጎላዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች መፍታት አለበት ብሏል።

ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ አንጎላዊ ጋዜጠኛ ነው። በሙያው በሃገሩ አንጎላ በርካታ ክስ እና እስር እንደገጠመው ይነገራል። ባለፈው ወር በደቡብ አፍሪካ ዊትስ በተካሄደው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ጥሰት በመፈጸም ከአፍሪካ ህብረት ህልም በተቃራኒ ቆማለች በማለት ተችቷል። ''የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በቀዳሚነት የመላ አፍሪካውያንን ህልም ይወክላል።

Sunday, 16 November 2014

በዝነኛው ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው) ዜና እረፍት የተነሳ ከ ኢሕአፓ የተሰጠ መግለጫ

እውቁ ገጣሚ፥ ታላቁ ደራሲና ግዙፉ የሀገራችን ቅርስ ለረጅም ዓመታት በስደት መከራውን ሲያይ
በቆየበት በስቶክሆልም (ስዊድን) ከተማ በዚህ ሰሞን አርፏል። ታዋቂዋንና አቻ የሌላትን በረከተ
መርገምንና በርካታ ሊሎች የግጥም መድበሎችንና ድርሰቶችን ያቀረበው ኃይሉ በቤተ ክህነት ትምህርት
የላቀ ዕውቀት የነበረው፤ የቅኔም አባት ሆኖ የቆየ ታላቅ የአገር ቅርስ ነበር ።
ኃይሉ ለዘመናዊው ትምህርት ወደ ዩኒቨርስቲ ከገባ ተጀምሮ በተራማጅ አስተሳሰብን ያንጸባርቅ በነበረው
የተማሪ እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ሆኖ ሲታገል ከሌሎች ስምንት ተማሪዎች ጋር ከዩኒቨርስቲ ተባሮ
እንደነበር ይታወቃል ። ገሞራው በአጼው ዘመን ሲታገል በተደጋጋሚ ለበርካታ ጊዜዎች ተይዞ ታስሮ
የነበረ ሲሆን ጨካኝ በሆኑ የጸጥታ ሰራተኞች ድብደባና ስቃይን ተቀብሏል ።

ተማሪዋ በተሳፈረችበት ታክሲ ታፍና ተወስዳ በደረሰባት አስገድዶ መድፈር ሕይወቷ አለፈ


ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል
በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቄራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አየር ጤና አካባቢ አንዲት የአሥረኛ ክፍል ተማሪ በተሳፈረችበት ታክሲ ታፍና ከተወሰደች በኋላ በደረሰባት አስገድዶ መደፈር ጉዳት ሕይወቷ ማለፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
ሟቿ ተማሪ ሃና ላላንጎ ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. አየር ጤና በተለምዶ ሳሚ ካፌ በሚባለው አካባቢ በአንድ ሚኒባስ ውስጥ ተሳፍራ ወደ ጦር ኃይሎች እየመጣች እንደነበር ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ ከትምህርት ቤት ወጥታ ወደ ቤተሰቦቿ በመጓዝ ላይ የነበረችው ሟች ተማሪ የተወሰነ ርቀት ከተጓዘች በኋላ መድረሷን ተናግራ ‹‹ወራጅ አለ›› ስትል፣ በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ አራት ወንዶችና ሾፌሩ ስለት በማውጣት አስፈራርተው እንዳገቷትም ተጠቁሟል፡፡

Tuesday, 11 November 2014

ፓርቲዎች ለሃይማኖት ተቋማት ጥሪ አቀረቡ

ጥቅምት (ሠላሳቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ››በሚል መርህ ትብብር  የመሰረቱት 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀደም ብለው ባሳወቁት የአንድ ወር መርሃ ግብር መሰረት የጀመሪያውን ጥሪ ለሃይማኖት ተቋማት አድርገዋል።
ፓርቲዎቹ አገራችንና ህዝቧ በተፈጥሮ ሚዛን መዛባት በሚከሰትበትም ጊዜ ሆነ በአገዛዝ ሥርዓቶች ምክንያት በችግር ውስጥ በሚወድቁበት ጊዜ የኃይማኖት  ተቋማትና ምዕመናን ሚና ከፍተኛ እንደነበር አውስተው፣ ዛሬ ላይ እነዚህ የሞራልና ሥነ-ምግባር እሴቶች እየተናዱ በመሄዳቸው ዜጎች ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ተጋልጠዋል፣ የአገር ፍቅር ስሜት በጥያቄ ውስጥ ወድቋል ብለዋል። 

Monday, 10 November 2014

አቶ በረከት ስምኦን የስልጣን መልቀቂያቸው ለጊዜው ይቆይ በሚል ውድቅ ተደርጓል::


-በውሳኔው የማይስማማ ከሆነ በሱና በቤተሰቡ በወዳጆቹ ስም የተመዘገበው ሃብት እንዲጣራ ተብሏል::
-ሳያገግሙ ስብሰባ እንዲመራ እና ሚዲያ ላይ እንዲቀርብ ታዟል::
የብአዲን/ኢሕአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡት የስልጣን መልቀቂያ ለጊዜው በሚል ውድቅ መደረጉን ሆኖም በቅርቡ መልስ ይሰጥበታል ሲሉ የሕወሓት ባለስልጣናት መመለሳቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::

Sunday, 9 November 2014

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ


የተሰጠ መግለጫ
ጥቅምት 25 ቀን 2007ዓ.ም
በስብሰባ ጋጋታ የተማረውን ሕብረተሰ የሸፈተ ልብ ምርኮኛ ማድረግ አይቻልም
በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ
በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያጋጠመውን ዙሪያ ገብ ችግር ፣ በመምህራን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል
ከዚህ አንፃር መምህራን የትምህርቱን ጥራት ለማስጠበቅና መብቶቻቸውን ለማስከበር ማድረግ ያለባቸውን
እንቅስቃሴና መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃ በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ መግለጫዎችን በማውጣት
በመላው ዓለም ላሉ ኢትዮጵያውያን ባጠቃላይና በተለይ ለጉዳዩ ባለቤቶች ለኢትዮያጵያ መምህራን ፣
ለተማሪዎችና ለወላጆች እንዲደርስ አድርጓል።

ኢትዮጵያ ፦ ለልጆቿ የተከለከለች ፍሬ


የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ
ጥቅምት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. የተላለፈ



ዕምቅና ተጨባጭ የሆነው የተፈጥሮ ሀብቷ ሞልቶ ተርፎ ፤ ዜጎቿን መመገብ ያልቻለች ምድር ሀገራችን ኢትዮጵያ
መሆኗ እስከ ዛሬ ደረስ ያልተገነዘበ ፍጡር ይኖራል ብለን አንገምትም ። እኛም ዛሬ ይህንን ለማውሳት የፈለግነው፤
ለድኅነታችን፤ ለችግራችንና ለረሀብ ጥማታችን ማስተዋወቂያ አዲስ ሰሌዳ ለመዘርጋት አይደለም ። ብሄራዊ ችግሮቻችንን
በአደባባይ ማውጣቱም ሀዘንን እንጅ፤ ደስታን ፤ ሀፍረትን እንጅ ኩራትን እንደማያመጣልን ደህና አድርገን እንገነዘባለን ።
ዘለዓለም ስለ ሀገራችን መከራና ችግር ብቻ እያወሳን ማነብነብ አንዳችም መፍትሄ እደማያስገኝ እንረዳለን ።
የሀገራችን ችግር መወገዱ ቀርቶ፣ እንዲያውም እየተባባሰ መሄዱ እስከቀጠለ ድረስ ግን፤ በቸልታ ልንመለከተው
አይገባንም። በመሆኑም፤ የችግሩን መሠረታዊ ምክንያቶችና ለችግሩም ተጠያቂዎች የሆኑትን ለይቶ በመፈረጅ
የሚወገዱበትን ዘዴ መፈለጉን እንቀጥልበታለን። በዕርግጥም፤ በችግሮቹ ነባር ምክንያቶች ላይ በማተኮር፤ የዘለቄታ
መፍትሄ ማግኘት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር መሆኑንም እናምንበታለን ።

Saturday, 8 November 2014

ኢህአዴግ በሚያካሂደው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ህዝቡ ቅሬታዎችን እያሰማ ነው

ጥቅምት  (ሃያ ሰባቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በየስብሰባዎቹ የተሳተፉ ምንጮች ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት በየመድረኩ የጋዜጠኞች መታሰር፣ የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት አለመከበር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መባባስ፣የሙስናና ብልሹ አሠራር መንሰራፋት፣ የህወሃት የበላይነት መኖር፣ የድህነት መንሰራፋትና የዋጋ ግሽበት አለመቀረፍ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ወከባና እስር መጠናከር በተደጋሚሚ የሚነሱና ኢህአዴግ በቂ ምላሽ ሊሰጥባቸው ያልቻለባቸው አበይት ጉዳዮች መሆናቸው ታውቆአል፡፡

የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ

ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስተባበርና በማቀራረብ እርቅ ለማስፈን እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የመግባባት፣ አንድነትና ሰላም (ሰላም) ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ፋንታሁን የታሰረው ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውረብለብና የማህበሩን አላማ የሚገልጹ፣ እንዲሁም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ችግር የሚላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የያዘ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በመበተን ማህበሩን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡

Thursday, 6 November 2014

https://plus.google.com/u/0/101056493753516422433/posts/aj2ikgfaVto

መንግሥት የተቃዋሚ መሪዎችን እያደነ ማሰሩን ቀጥሎአል

ጥቅምት  (ሃያ አቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የተቃዋሚ አመራሮችን በመያዝ እያሰረ ነው::  በትግራይ ክልል በምዕራባዊያን ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ዳንሻ ከተማ የአረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ዘነበ ሲሳይ ጥቅምት 25፣ 2007 ዓም ከቤታቸው ተነጥለው በመወሰድ ሲታሰሩ፣  በተመሳሳይ ቀን በሁመራ የአረና የቁጥጥር ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አማረ ተወልደ  ታስረዋል።
ከወራት በፊት የታሰሩትን አብራሃ ደስታንና አያሌው በየነን  ጨምሮ 7 የፓርቲው አመራሮች በእስር ላይ ናቸው።
በተመሳሳይ ቀን በአማራ ክልል ምዕ/ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ  የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን አበበ እና ሶስት የድርጅቱ አባላት ተይዘው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።  ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ ከ10 ያላነሱ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አንዱአለም አራጌ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ናትናኤል መኮንንና ሃብታሙ አያሌው  በእስር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

U.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist


U.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist
The United States is deeply concerned by the October 27 sentencing of Ethiopian journalist Temesgen Desalegn to three years in prison for “provocation and dissemination of inaccurate information.”

Temesgen Desalegn – an Ethiopian embodiment of courage

by Hindessa Abdul
In one of his articles Temesgen discusses how the struggle of the Ethiopian opposition and other activists were reduced from raising political and civil liberty issues to merely demanding the release of opposition figures or imprisoned journalists. Ironic as it may seem, now the 37 years old is in the later’s shoes and rest assured others certainly will not stop demanding his release.Temesgen Desalegn, publisher and editor
Temesgen Desalegn, publisher and editor of the now defunct Feteh and a couple of other newspapers, has been found guilty of articles that were published in his paper between July 2011 and March 2012.

እሥሩ ተጧጡፏል፣ አንድነት ምርጫ እንዳይወዳደር አገዛዙ ይፈልጋል

ግርማ ካሳ

ዜጎች መታሰራቸው እየቀጠለ ነው። በተለይም የአንድነት ፓርቲ አባላት (በጎንደር፣ በትግራይ፣ በመቱ፣ በአዲስ አበባ ፣ በወላይታ ….) ። ብዙዎች ከፍተኛ ደብደባ እየደረሰባቸው ነው። ሕወሃት ፣ በሕዝብ እንደተጠላ ስላወቀ የአንድነት ፓርቲ እንዲዳከም ወይም ከምርጫው ዉጭ እንዲወጣ እየሰራ ነው። አንድነት ሊያሸንፈው እንደሚችል ስላወቀ።
የድርጅቶች መተባበር አስፈላጊ በመሆኑ፣ አንድነት ከመኢአድ ጋር ተስማምቶ የቅድመ ዉህደት ስምምነት ፈርሞ ነበር። ሁሉም ነገር አልቆ ነበር። ሆኖም ምርጫ ቦርድ ወይንም አገዝዙ፣ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ዉህደቱን አስቁሞታል። ይኸው እስከአሁን ድረስ በአቶ አበባው ለሚመራው መኢአድ እውቅና አልሰጠም ብሎ መኢአዶችን ምርጫ ቦርድ እያጉላላቸው ነው።

መልዕክት ከቃሊቲና ከቂሊንጦ

ነገረ ኢትዮጵያ
የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ የዝግጅት ክፍል አባላት ወደ ቂሊንጦና ቃሊቲ እስር ቤቶች በማቅናት እስረኞችን ጠይቀዋል፡፡ እስረኞቹ ያስተላለፉትን መልዕክት ነገረ ኢትዮጵያ እንደሚከተለው ጠቅለል አድርጋ አቅርባዋለች፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አይቀርም›› እስክንድር ነጋ
በማህበራዊ ድረ-ገጽም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች መልካም ልደት ለተመኛችሁልኝ ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ የቡርኪናፋሶው አምባገነን መውደቁን በመስማቴ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ይህ ለእኔ ውድ የልደት ቀን ስጦታየ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ለውጥ የሚቀር አይደለም፡፡ የእኛ ችግር ከማንም የባሰ ነው፡፡ ቱኒዚያ ላይ የተጀመረው አብዮት ሰሜን አፍሪካ አንቀጥቅጧል፡፡ ኢትዮጵያ ከሰሜን አፍሪካ አገራት ይልቅ ለእነ ቦትስዋና ትቀርባለች፡፡ የቦትስዋና ጉዳይ ሌሎቹንም ማነቃነቁ የማይቀር ነው፡፡ ይህ ለውጡ ቅርብ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አይቀርም፡፡

Wednesday, 5 November 2014

የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር አስተባባሪ ታሰረ


ነገረ ኢትዮጵያ
• ‹‹ጎንደር ውስጥ ያለውን የህዝብ ጥያቄ ለማፈን የተደረገ ነው፡፡›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ

• ‹‹የፀረ ሽብር ህጉ የገዥው ፓርቲን ስልጣን ለመጠበቅ እየዋለ ነው፡፡›› አቶ ይድነቃቸው ከበደ


የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል እና የሰሜን ጎንደር የዞን ሰብሰቢ አቶ አግባው ሰጠኝ ጎንደር ከተማ ውስጥ ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በገዥው ፓርቲ ደህንነቶች መታሰሩን የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፖሊስና የደህንነት ኃይሎች አቶ አግባው ሰጠኝን ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመውሰድ ከ1 ሰዓት ተኩል በላይ ፍተሻ እና ብርበራ በማካሄድ ስፍራው ወደልታወቅ ቦታ እንደወሰዷቸው ጎንደር ውስጥ የሚገኙ የፓርቲ አመራርና አባላት ገልጸዋል፡፡

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ተከሳሾች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

• ‹‹እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ በሽብር ወንጀልም ተሳትፈዋል›› የተባሉ ሌሎች ተከሳሾ በሽብር ተከሰዋል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርት

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት አራቱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ አስሩ ተከሳሾች ዛሬ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የዋስትና ጉዳያቸውን ለማየት ለህዳር 2/2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ሀብታሙ አያሌው፣ የሽዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሺን ጨምሮ አስሩ ተከሳሾች ላይ የፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ከቀናት በፊት መመስረቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ የዋስትና ጉዳያቸውን አይቶ ብይን ይሰጣል ቢባልም የተከሳሽ ጠበቆች አጭር የጊዜ ቀጠሮ በጠየቁት መሰረት ለህዳር 2/2007 በአምስት ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Tuesday, 4 November 2014

በሰሜን ጎንደር ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የቅማንት ተወላጆች ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ በተጠራ የስራ ማቆም አድማ በዞኑ የሚገኙ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ የተዘጉ ሲሆን፣ መንግስት እስከ መስከረም 30 መልስ የማይሰጥ ከሆነ፣ ተቃውሞው ግብር ባለመክፈል እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በርካታ አስተባባሪዎች ተይዘው የታሰሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው እስከ መስከረም መጨረሻ መልስ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።