BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 10 February 2015

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማስፈታት ወደ ኢትዮጵያ ሊሄድ የነበረው የእንግሊዝ ፓርላማ ቡድን ጉዞውን ሰረዘ

የካቲት ፪(ሁለት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ዘ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው የፓርላማ ብድኑ የጉዞ እቅዱን የሰረዘው ፤ አቶ አንዳርጋቸውን ማነጋገር እንደማይችሉ በኢትዮጵያ መንግስት ስለተነገራቸው ነው።
እንግሊዝ -ለኢትዮጵያ እርዳታ ከሚሰጡ ለጋሽ ሀገራት አንዷና ዋነኛው ስትሆን ፤ የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ ለኢትዮጵያ በሚሰጠው ድጋፍ ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በፓርላማው ውስጥ ተከታታይ ጥያቄዎች እየቀረቡ ነው።

ጄሬሚኮርቢን በተባሉት የእንግሊዝ ፓርላማ አባል የሚመራው የፓርላማ ቡድን  ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት አቶ አንዳርጋቸውጽጌን ለማስፈታት እንዳቀደ ከአንድ ወር በፊት በለንደን በሰጠው መግለጫ ማሳወቁ ይታወሳል።
ይሁንና የፓርላማ ቡድኑ አባላት በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ከአቶ ብርሃኑ ከበደ ጋር ሲነጋገሩ ፤ ወደ ኢትዮጵያ ቢያቀኑም አቶ አንዳርጋቸውን መጎብኘት እንደማይችሉ ስለተነገራቸው ጉዟችውን መሰረዘቸውን ሚስተር ኮርቢን ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤ የነጻነት ታጋዩ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ  60ኛ ዓመት ፤ በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በድምቀት እየተከበረነው።

No comments:

Post a Comment