የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ መረጃ እንደሚያሳየው በክልሉ በሚካሄደው ትጥቅ የማስፈታት ሂደት በሰሜን ጎንደርና በምእራብ ጎጃም ዞኖች ብቻ 2 ሚሊዮን 13 ሺ 497 ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች ለክልሉ ሚሊሺያ ጽ/ቤት ገቢ ተደርጓል።
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ጉዳዩች መምሪያ ኃላፊው አቶ ደጀኔ ሽባባው በጽ/ቤቱ የ2ዐዐ7 በጀት ዓመት ግማሺ አመት ሪፖርት ላይ እንዳመለከቱት ደግሞ ጽ/ቤቱ የጦር መሣሪያዎችን ዝውውር ለመቆጣጠር እና ለመግታት ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች 17ዐ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን 3ሺ 635 ልዩ ልዩ ጥይቶችን እና 21 ቦንቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
በቅርቡ በቀበሌ 16 በአንድ ግለስብ ቤት 21 ክላሺንኮቭ ጠመንጃ መገኘቱንም ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የሚገኙ የካቢኔ አባላት ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ 8 ሺ 429 የወገብ ሺጉጥ ታጥቀው እንደሚገኙም የክልሉ ሚልሻ ጽ//ቤት መረጃ ያሣያል፡፡
በክልሉ ከ5 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ያላነሱ ጠመንጃዎች፣ ጥይቶችንና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ እንደሚገኝ ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች የጦር መሳሪያችሁን አስረክቡ እየተባሉ እንደሚታሰሩ፣ እንደሚገረፉና ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም እንደሚጣልባቸው ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment