በማህበራዊ ድረገጾች በመጻፍ የሚታወቁት የዞን ዘጠኝ አባላት እሁድ እለት ችሎት ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም፣ ግብረአበሮቻቸውም አልተያዙም በሚል ሰበብ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የ15 ቀናት ጊዜ ተፈቅዶለታል።
አቤል ዋበላ፣ በፈቃዱ ሃይሉና ማህሌት ፋንታሁን የተባሉ ወጣት ጸሃፊዎች ለሀምሌ 7 ቀን 2006 ዓም ተቀጥረዋል። ችሎቱን ለመከታተል የሄደው ህዝብ ወደ ችሎት እንዳይገባ የተከለከለ ሲሆን ከጠበቃው ከአቶ አምሃ እና ከአጃቢ ፖሊሶች በስተቀር ቤተሰቦች እንኳ ችሎቱን እንዲከታተሉ አልተፈቀደላቸውም።
ፖሊሶች ህዝቡን ሲያንገላቱ፣ ፎቶ የሚያነሱትን ካሜራዎቻቸውን ሲቀሙ እንደነበር በችሎቱ የተገኙ ታዛቢዎች ገልጸዋል። መንግስት ዞን ዘጠኝ የተባሉ ወጣቶች በውች አገር ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋር በመሆን ህዝባዊ አመጽ ለማስነሳት ተነስተዋል በሚል እንዳሰራቸው ይታወቃል።
በፈቃዱ ሃይሉ የተባለው ወጣት ጸሃፊ ያላመነበትን ነገር በግድ እንዲፈርም እንደተደረገ ተናግሯል። በኢትዮጵያ ሃሳብን ከመግለጽ ጋር በተያያዘ ከ15 ያላነሱ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ታስረው ይገኛሉ።
No comments:
Post a Comment