ሰኔ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን መንግስት የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ማገቱን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች ቁጣቸውን እየገለጹ ነው።
አላማጣ አካባቢ የሚኖሩ አንድ አስተያየት ሰጪ ” የየመን መንግስት ያገተው አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። በዚህ የቁርጥ ቀን ልጅ ላይ አንድ ነገር ቢደረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆ ብሎ ይነሳል። የመን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አብራ ለመኖር ካሰበች አንዳርጋቸውን በአሽኳይ ትልቀቅ ” ብለዋል።
ሌላ ወጣት ደግሞ ” አቶ አንዳርጋቸው የታሰሩት ለኢትዮጵያ ህዝብ እስከሆነ ድረስ ፣ ማንኛውንም መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን” ስሜቱን ገልጿል።
” ትልቅ ትግል እያደረገ ያለ የነጻነት አባታችን ነው። የየመን መንግስት ነብር አየህ በሉት።” የሚሉት ሌላ አስተያየት ሰጪ አክለውም ” ይህ የአገር ኩራትና ተምሳሌት በየጫካው ሲዞር የኖረ ሰው እንደዚህ ሲሆን በጣም ያሳዝናል። እዚህ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ትንሽ ክፈተት ነው የሚጠብቀው፣ ዝግጁነው። በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው” ሲሉ አክለዋል
” አንዳርጋቸውን በማሰር የኢትዮጵያ ትግል የሚቆም ይመስላቸዋል ወይ?” በማለት አስተያየታቸውን በጥያቄ የጀመሩት አስተያየት ሰጪ ደግሞ ” ትግል አይቆምም፣ ወያኔዎች ከማን ጋር እየተጣሉ እንደሆነ ያውቁታል። ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው ሊያስቡ ይገባል። በእየአገሩ ችግር ሊፈጠርባቸው እንደሚችል ሊገባቸው ይችላል። የትም ተደብቀው አይቀሩም።” ሲል ተናግረዋል
አንድ ሴት አስተያየት ሰጪ ደግሞ ስሜቷ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱንና ኢሳት ዜናውን ተከታትሎ መልካሙን እንዲያሰማት ጠይቃለች።
በሌላ ዜና ደግሞ በየመን የጸጥታ ሃይሎች የታገቱትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማስፈታት አለማቀፍ ዘመቻ መጀመሩን ግብር ሃይሉ አስታውቋል።
“አንዳርጋቸው ጽጌ ይለቀቅ” የሚል ስያሜ ያለው ግብረሃይል ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ” የግብረ ሃይሉ አላማ የየመን መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አቶ አንዳርጋቸውን እንዲለቀው ግፊት ማድረግ ነው።”
ግብረሃይሉ በአለም ያሉ ኢትዮጵያውያን በአካባቢያቸው ወደሚገኙ ኢምባሲዎች ስልኮችን በመደወል፣ የኢሜል እና የፋክስ መልክቶችን በመላክ ትህትትና በተሞላበት ነገር ግን ቆራጥነትን በተላበሰ መልኩ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።
የአቶአንዳርጋቸውጽጌንለማስለቀቅየተቋቋመውዓለማቀፈግብረሀይልብዲፕሎማሲያዊመንገድእየተደረገያለውጥረትውጤታማይሆንዘንድበሁሉምሀገራትየሚኖሩኢትዮጵያውያንእስከመጪውአርብድረስበግብረሀይሉየተዘጋጀውንደብዳቤበአቅራቢያቸውወደሚገኙየየመንኤምባሲዎችተሰባስበውበመሄድእንዲሰጡካልቻሉበደብዳቤውጫፍላይየተቀመጡአድራሻዎችንተጠቅመውበፖስታወይምበፌስቡክአለያምበኢሜይልእንዲልኩአሳስቧል።ከዚህምባሻገርአቶአንዳርጋቸውእንዲልቀቁየሚጠይቀውንፒቲሺንበመፈረምየአቅማቸውንጠጠርአንዲወረውሩጠይቋል።ግብረሀይሉበጀመረውዲፕሎማሲያዊዘመቻእስከመጪውአርብድረስከየመንመንግስትአንድምላሽሊገኝይችላልየሚልተስፋእንዳለውጠቅሶ፤በመሆኑምበነገውእለትበሳንሆዜለስፖርትፌስቲቫልየተሰባሰቡኢትዮጵያውያንከሚያደርጉትሰልፍበስተቀርእስከመጪውአርብድረስበሌሎችሀገሮችሰልፎችእንዳይደረጉአሳስቧል።እስከአርብድረስበጎእናጥሩምላሽከተገኘየታሰቡትሰልፎችበሙሉሊቀሩይችላሉያለውግብረሀይሉ፤እስከመጪውአርብምላሽካልተገኘግንበመላውዓለምየሚኖሩኢትዮጵያውያንበመጪውማክሰኞበአንድቀንበየአካባቢያቸውበሚገኙየየመንኤምባሲዎችሰልፍለመውጣትዝግጅትእንዲያደርጉአሣስቧል።
የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ካውንስል ለኢሳት በላከው መግለጫ ደግሞ የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር በጽኑ አውግዞ ፣ የየመን መንግስት በአፋጣኝ እንዲለቀው ጠይቋል።
አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ እንዳይሰጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት እንዲነሳ ካውንስሉ ጥሪ አቅርቧል።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ እርሳቸውና ድርጅታቸው በአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ማዘናቸውን ገልጸው ፣ የየመን መንግስት በአስቸኳይ ይፈታው ዘንድ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ኦባንግ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችና ለጋሽ አገራት ጣልቃ እንዲገቡም ጠይቀዋል።
No comments:
Post a Comment