BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Wednesday, 18 February 2015

አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ- ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር እንደማይግባቡ ተናገሩ።

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባ ዱላ-ገመዳ ከኦሮሚያ ክልል  ፕሬዚዳንት- ከአቶ ሙክታር ከድር ጋር እንደማይግባቡ የተናገሩት፤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር አባላት በቃኘው ጥልቅ ግምገማ ላይ ነው
አፈ-ጉባኤው በግምገማው”የኦሮምያ አባላትን በተለየ ትህትና ታሰተናግዳለህ፣የአፈ ጉባኤነቱን ቦታ በደስታ አልተቀበልከውም፣ በአዲስ አበባ አዲስ ማሰተር ፕላን ጋር ተያይዞ ተል እኮ የማስፈጸም ችግር አለብህ፣ ከማስተር ፕላኑ ጋር ተያይዞ ለተነሳው አመጽ መባባስ መንስኤ ነህ፡፡>> ተብለው  ነው የተወቀሱት።

አባ ዱላ  ለቀረበባቸው   ሂስ ምላሽ ሲሰጡ ፦”አመፅ የተባለውን አልቀበለውም፡፡ ዘረኝነት የተባለው ከሙክታር ጋር ስለማንግባባ ነው፤ እንዳውም አሁን አሁን ስልክ እየደወልኩ  በክልሉ ዙሪያ አሰተያየት መስጠት አቁሚያለሁ፡፡>> ብለዋል።
<<በእርግጥ እንደተባለው በአፈ ጉባኤነቱ ሹመት ቀደም ሲል ደስ አላለኝም ብዬ ነበር>> ያሉት አፈ-ጉባኤው፤<< አሁን ግን ደስተኛ ነኝ፡፡ ተሰማምቶኛል፡፡>>በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።
ከአሁኑ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር አንግባባም ያሉት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ፤ቀደም ሲል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት  ነበሩ።
አፈ-ጉባኤው በተመሳሳይ፤ከአቶ ሙክታር ከድር በፊት የክልሉ ፕሬዚዳንት ከነበሩትና በ ኦህዴድ ጓደኞቻቸው ተመርዘው ከተገደሉት  ከአቶ ዓለማየሁ አቶምሳም ጋርም ጠበኞች እንደነበሩ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment