.png)
የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ያደመጠው ፍርድ ቤትም፤ ለፊታችን መጋቢት 21 ቀጠሮ በመስጠት የእለቱን ችሎት አጠናቋል፡፡
ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ ወር 2006 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ የተመሰረተባቸው ጥር 28 ቀን 2007 ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት እድል ያገኙት ግን በዛሬው ዕለት ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የጦማርያኑን ችሎት በመሀል ዳኝነት ሲያስችሉ የነበሩት አቶ ሸለመ በቀለ ተከሳሾቹ <<ይቀየሩልን>> ባሉት መሰረት ሐሙስ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ራሳቸውን በፈቃደኝነት እንዳገለሉ የተገለጸ ቢሆንም፤ በዛሬው ችሎት ላይ ግን ቀርበው እንደነበር -ፍርድ ቤት ተገኝተው ችሎቱን የተከታተሉት የተከሳሽ ጓደኞችና ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡
No comments:
Post a Comment