BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Monday, 24 February 2014

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ለቀቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣  2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የግብፅ  ጊዜያዊ መንግሰት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀዜም ቤብላዊ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውንና ካቢኒያቸው መበተኑን ይፋ አደረጉ።
ድንገት የሆነውን  ዜና  ይፋ  ባደረጉበት መግለጫቸው ላይ ቤብላዊ  አገራቸው በግብፅ ጥቃቶች እየበረከቱ መምጣታቸውን አንስተው፥ በየትኛውም  የዓለም  ክፍል የሚገኝ መንግስት  ግን  በዚህ አጭር  ጊዜ  ውስጥ  የህዝብን  ጥያቄ ሙሉ በሙሉ መመለስ አይችልም ብለዋል።
ካቢኒያቸው ባለፉት ስድስት  ወራት ከባድ ሀላፊነቶችን  ተሸክሞ ማለፉንም  ተናግረዋል።
ቤብላዊ የእሳቸውና  የካቢኒያቸውን የስልጣን መልቀቂያ  ለሽግግር  መንግስቱ ፕሬዚዳንት አድሊ ማንሱር አቅርበዋል።
የመንግስቱ  የዜና  አውታር  አል አህራም  እንደዘገበው ጠቅላይ  ሚኒስትሩ በሌላ  እስከሚተኩ በስልጣን  እንዲቆዩ  በመንግስት  ተጠይቀዋል።

No comments:

Post a Comment