በማህበራዊ ሜዲያዎች በሚያነሳቸው ሀሳቦች ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘውና የአረና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል የሆነው አብርሃ ደስታ፣ በዛሬው ዕለት እነ አንዷለም አራጌን ርዕዮት አለሙን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ በሄደበት ጊዜ ለስድስት ሰዓት በዚያ እንደደረሰና እንግልት እንዳጋጠመው ገልጸ።
እስረኞች በወዳጅ ዘመድ ቤተ ሰብ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ሕግ መንግስቱ ላይ በገልጽ የተቀመጠም ቢሆን፣ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሃላፊውች በሕጉ መሰረት ጠያቂዎችን ማስተናገድ ስገባቸው፣ በታሰሩት ላይ የሚደርሰው ግፍ ሳያንስ በጠያቂዎችም ላይ እያደረሱት ያለው እንግልት ፣ ምን ያህል በአገሪቷ ሕግ እንደተናቀ የሚያሳይ ነዉ።
«የአረና ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አብርሃ ደስታ ዛሬ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ወደ ቃሊቲ በማምራት እነ አንዷለምና ርዕዮትን ለመጠየቅ ቢሄዱም የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ማንን ለመጠየቅ እንደመጡ ጠይቀዋቸው እነ አንዷለምን ለመጠየቅ እንደሚፈልጉ ገልጸውላቸው መታወቂያቸውን ተቀብለው ወደ ማረሚያ ቤቱ ኃላፊ አቀረቡዋቸው» ሲል የዘገበው የአንድነት ልሳን ፍኖት፣ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ከየት እንደመጡና ለምን እንደመጡ በትግርኛ ቋንቋ እንደጠየቋቸው፣ አቶ አብርሃም ከመቀሌ እንደመጡና እነአንዱአለምን ለመጠየቅ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን፣ ኃላፊውም በቁጣ «ከመቀሌ እዚህ ድረስ የአማራ አክራሪዎችን፣ ነፍጠኞችን ለማየት እንዴት ትመጣለህ ? አታፍርም ወይ ? ከእንግዲህ እዚህ ልትታሰር እንጂ ልትጠይቅ አትመጣም» በማለት ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው አስፈራርተዋቸው እስረኞቹን ሳይጠይቁ መውጣታቸውን ፍኖት ዘግቧል።
በዚህ ሁሉ ዉዝግብ ዊስጥ ለስድስት ሰዓታት የማረሚያ ቤት ሃላፊዎች አብርሃ ደሳት ካገቱት በኋላ ፣ እስረኞችን ሳይጠይቅ እንደተመለስም ለማረጋገጥ ችለናል።
አብርሃ ደሳት በቅርቡ በትግራይ ዉስጥ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበረዉ አንዱዋለም አራጌ በጣም ተወዳጅ ፖለቲከኛ መሆኑን መጻፉ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment