BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Wednesday, 26 February 2014

ጠ/ሚ ኃ/ማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው *ኢቴቪና ፌዴራል ፖሊስም ይከሰሳሉ

በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቅርቡ ከተላለፈው ‘‘ጅሃዳዊ ሃራካት’’ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ የወንጀልና የፍትሃብሔር ክስ ሊመሰረት ነው። ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ባሻገር በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሬቴድ) እና በፌዴራል ፖሊስ ተመሳሳይ ክስ ይመሰረትባቸዋል።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናቱ እና የተጠቀሱት ተቋማት ላይ ክስ የሚመሰረተው ሰሞኑን ‘‘ጃሃዳዊ ሃራካት’’ በሚል በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ደርጅት የቀረበው ዘጋቢ ፊልም በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር ያሉትን ተጠርጣሪዎች መብት ሲጣስ መከላከል ባለመቻላቸው፣ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀማቸው፣ በሕዝብ ሐብት ያለአግባብ በመገልገላቸው፣ የተሰጣቸውን የሕዝብ አደራ ባለመወጣታቸውና በሃይማኖት ጣልቃ በመግባታቸው የወንጀልና የፍትሐብሔር ክስ ይመሰረትባቸዋል። ክሱን የሚመሰርቱት በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ባሉት ተጠርጣሪዎች ጠበቆች አማካኝነት ሲሆን ክሱም በሁለት ደረጃ ተከፍሎ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል።
ክሱን እያዘጋጁ ከሚገኙት ጠበቆች አንዱ የሆኑት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ክሱን በማስመልከት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በመንግስት ባለስልጣናት ላይ የሚመሰረተው ክስ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባል ብለዋል። በኢቲቪ ላይ የሚመሰረተው የፕሬስ ክስ ቀጥታ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የሚቀርብ ሲሆን ክሱም ከሞራል ጉዳት ጋር እንደሚያያዝ ጠበቃው አስታውቀዋል።....

No comments:

Post a Comment