BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 28 February 2014

ጠባብ ብሄርተኞች እና አክራሪ ብሄርተኞች…

ሁለቱም አደገኛ ናቸው….ጠባብ ብሄርተኝነትም ሆነ አክራሪ ብሄርተኝነት በባህሪያቸው የተለያዩ ይሁኑ እንጂ ፍፃሚያቸው አንድ ነው…..ፍጅት!!! ጠባብ ብሄርተኞች ገዢዎችን ከህዝቡ መለየት ተስኗቸው ምንም የማያውቀውን ህዝብ ሊያፋጁ ዘወትር መርዝ ይረጫሉ፡፡…….አክራሪ ብሄርተኞች በበኩላቸው ደግሞ የራሳቸውን ባህል እና እምነት የራሴ ነው ብሎ ከማለት ይልቅ በሌላው ላይ በመጫን የእናንተም ነው ሊሉን ይቃጣቸዋል፡፡….በዚህም ፍጅትን እንደሚጋብዙ አያስተውሉም፡፡…….ኢትዮጲያ ሀገራችን ብዙ ባህል ብዙ ቋንቋ ያላት ሀገር ናት፡፡ ይሄ የትም የማይሄድ ሀቅ ነው፡፡ ነገስታቶች በታሪካችን ከተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች ተነስተዋል……ሁሉም ማለት በሚቻልበት ሁኔታ ግን በጉልበት ላይ የተመሰረተ አገዛዝ የነበራቸውና ህዝባቸውን ያስመረሩ ነበሩ(በጎ ስራዎች መስራታቸውም እንዳለ ሆኖ)…….አጼ ቴዎድሮስ(በጣም ብወደውም) ጨካኝ እና ጨፍጫፊ እንደነበር ታሪካዊ እውነታ ነው!!!…….አፄ ዩሀንስ መተማ ላይ አንገታቸውን የሰጡ ጀግናችን ቢሆኑም ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችን አካሂደዋል……..ሁለቱም እውነት ነው…….የየጁ ነገስታት ወሎንና አካባቢውን ሲገዙ ብዙ መልካም ነገሮችን ቢያደርጉም እነሱም ጨፍጭፈዋል…….ዘመናቸውም እኛ በ21ኛው ክ/ዘመን ቁጭ ብለን ጭፍጨፋን እንደምናወግዝበት ያለ አልነበረም…ይልቁን ጉልበት የሚወደስበት ነበር….በሌላም አለም እንዲሁ ነበር፡፡…….አፄ ምኒልክም በተለይ ኢትዮጲያን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማስተዋወቅ ያደረጉት ጥረት እና በአድዋ ላይ የፈፀሙት ጀግንነት ቢያስወድሳቸውም በግዛት ማስፋፋት ወቅት የወሰዱት ምህረት የለሽ እርምጃ መጥፎ ጠባሳ ነው፡፡……….ከሁሉም በላይ ግን ሊታወቅ የሚገባው ሀቅ አንድ ነው..እሱም ገዢዎች ዛሬ ድረስ በጉልበት እንጂ በህዝብ ይሁኝታ አልነገሱምና ህዝብን አይወክሉም….በነርሱ ጥፋት የሚጠየቅ ህዝብ የለም…….ጠባቦቹ ይሄን ነው ማስተዋል ያቃታቸው፡፡…………በኃይለስላሴ ዘመን በተለይም ብሄሮችን የጨቆነ ስርዓት እንደነበር ማንም የሚክደው አይደለም……ሹመትም በአብዛኛው የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች እጅ ያጠነጠነ ነበር…….ዛሬ እንደ ሞረሽ ወገኔ ያሉ አክራሪ ብሄርተኞች ንጉሳዊው ስርዓት እንዲመለስላቸው ያልማሉ….ይቃዣሉ፡፡ ይህ ግን መቼም አይሆንም፡፡ ራስን የአማራ ድርጅት ነኝ ብሎ በብሄር ደረጃ ዝቅ ካደረጉ በኋላ እኔ ስለሁሉም የኢትዮጲያ ህዝብ ያገባኛል እያሉ መቀባጠር የትም አያደርስም፡፡ እኔን የሚያሳስበኝ በዚህ በጠባቦችና በአክራሪዎች ግርግር መሀል የኢትዮጲያን አንድነት የማይሹ እና ጥፋቷን የሚመኙ ነገሩን እያራገቡ እንዳይከፋፍሉን ነው……..እንድ ጥያቄ በመመለስ ላብቃ……..ከእነ ሞረሽ ወገኔ ጀርባ ያለው ሀይል ማነው;;; ከነጃዋር ጀርባስ;;; ሊከፋፈሉን የሚፈልጉ የውጭ ሀይሎች ናቸው፡፡

ማርታ ተስፋዬ

No comments:

Post a Comment