BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Sunday, 16 February 2014

አንድነት ፓርቲ ሁለተኛውን ዙር የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲጀመር ወሰነ


የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ሁለተኛውን የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚው ተግባራዊ እንዲደርግ ወሰነ፡፡
ብሔራዊ ምክር ቤቱ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2006 ባደረገው አስቸኳ ስብሰባ በሶስት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ከነዚህ ውሳኔዎች መካከል ሁለተኛው ዙር የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ ይገኝበታል፡፡ 
የፓርቲው ፕሬዝደንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሁለተኛው ዙር የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ በመሬት ባለቤትነትና አስተዳደር ጉዳይ ላይ ያተኮረ እንዲሆን መወሰኑን በመግለፅ ብሔራዊ ምክር ቤቱም ለዚሁ ውሳኔ ይሁንታው እንዲሰጥ በመጠየቅ፣ ህዝባዊ ከንቅናቄው ስለሚጠበቀው ውጤት ማብራሪ ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ስዩም፣ የማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊው አቶ አለነ ማዕፀንቱ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊው አቶ ሰለሞን ስዩም በሀገራችን ከመሬት ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ ስለፈጠራቸው ውስብስብ ችግሮች ጥልቅ ጥናታቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብና ጥናት ላይ ግብአት ከሰጠና ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ሁለተኛው የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ በመሬት ጉዳይ ላይ ተኮረ እንዲሆንና ይህንኑም ተግባራዊ እንዲያስደርግ ለፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኃላፊነት በመስጠት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

No comments:

Post a Comment