BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Thursday, 20 February 2014

የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ድርጅት ለረዳት ፓይለቱ ጠበቃ አቆመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን ስዊዘርላንድ ላይ ያሳረፈው የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን ጉዳይ አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው። የአውሮፕላን ጠለፋው ጉዳይም ከኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጋር የተያያዘ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው እየተነገረ ይገኛል። ይህን ተከትሎ ረዳት ፓይለቱ የሰራው ሥራ የሚደነቅ ነው በሚል በርካቶች ውዳሴን እያቀረቡለት ሲሆን “ረዳት ፓይለቱ በእጁ እንዳለው የተለያየ ሃገር ቪዛ በማንኛውም ጊዚ ከሃገር መውጣት ይችል ነበር፤ ሆኖም ግን ሊያስተላልፈው የፈለገው መልዕክት ስላለ ነው አውሮፕላኑን የጠለፈው ስለዚህ ይህ ለኢትዮጵያውያን የተከፈለ መስዋእትነት ነው” በሚልም ሰኞ ዕለት ለፈጸመው ድርጊት አድናቆትን እያገኘ እንደሆነ ከሚደረጉ እንስቃሴዎች መረዳት ይቻላል። ዛሬ ቢቢኤን ራድዮ ጣቢያ እንዳደረሰን መረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ የፖለቲካኛ እስረኞች አንድነት ድርጅት ለሃይለመድህን ጠበቃ ማቆማቸውን ይገልጻል። 

No comments:

Post a Comment