BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Saturday, 22 February 2014

ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ በጠለፋ ሳይሆን በእገታ ይከሰሳል::ከጠበቃ እንዲገናኝ ተፈቅዶለታል ተላልፎ አይሰጥም።

ከስዊዝ የተሰሙ ዜናዎች እንደሚጠቁሙት ባለፈው ሰኞ የኢትዮጵያን አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 702 በጄኔቭ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ በአይሮፕላኑ ላይ እና በመገደኞች ላይ እገታ በመፈጸም እንደሚከሰስ እና ወደ ፍርድ ቤትም ጉዳዩ በቅርቡ እንደሚሄዽ ታውቋል::

የስዊዝ የህግ አካል እንዳለው ለሃይለመድህን አበራ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ የተመደበለት ሲሆን የፍርድ ሂደቱ በቅርቡ እንደሚጀመር እና የፍርድ ሂደቱ የሚጀመርበትን ቀን ግን በይፋ አልታወቀም:: የስዊዝ ባለስልጣናት በዚህ ዙሪያ ያለውን መረጃ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ሲሆኑ ምርመራ ላይ ስለሆነ ምርመራው እንደተጠናቀቀ የበለጠ ግንዛቤ እንደሚሰጡ እየተጠበቀ ነው::
 #Ethiopian702 #MinilikSalsawi#
http://www.zegabi.com/articles/?p=7494
Ethiopian Airlines Hijacker Co-Pilot to Stand Trial

No comments:

Post a Comment