BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Monday, 24 February 2014

የሰማያዊ ፓርቲ የድሬደዋ ስብሰባ ፎቶዎችን ይመልከቱ






የሰማያዊ ፓርቲ፣ ከመኢአድ እና አንድነት ጋር የባህር ዳሩን ሰልፍ እንዲቀላቀል ከአንዳንድ ደጋፊዎቹ ጥሪ የቀረበለት ቢሆንም፣ የድርጅቱ አመራሮች አብሮ ያለመስራት አክርሪ አቋማቸውን በመያዝ፣ ትኩረታቸውን ከምእራብ ኢትዮጵያ ወደ ምስራቅ አዙረዉ ነበር።
የባህር ዳር ሰልፍ በሚደረገብት ቀን «በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከድሬደዋ ሕዝብ ጋር ለመነጋገር» በሚል እሁድ የካቲት 16 ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሳምራ ሆቴል ስብሰባም አድርገዋል።
sem2
የፓርቲዉ አሰታባበሪዎች በከተማዋ የሰልፉን ፍላየር፣ ቅዳሜ የካቲት 15 ሲበትኑ የነበረ ሲሆን ፣ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ በሆነችዉ በድሬደዋ ከተማ፣ ስብሰባውን መካፈል ከነበረበት ህዝብ ጋር ሲነጻጸር፣ በሰማያዊ ስብሰባ የተገኘው ሕዝብ ብዙ ነበር ማለት እንደማይቻል የደረሰን ዜና ያመለክታል።

በሰማያዊ ስብሰባ ከተገኙ ጥቂት ኢትዮጵያዉያን መካከል ፣ አንዱ «የህግ የበላይነት በሌለበት ስርዓት ነው ያለነው፡፡ የብሄር ፖለቲካም እስካሁን አልጠቀመንም!›› ሲሉ ያለፉት የ20 አመታት የአገዛዙን የዘር ፖለቲካን አውግዘዋል። ከሃያ አመታት በፊት አክራሪ ኦነጎች እና በጀኔራል ጃራ ይመራ በነበረዉ፣ በእስላማዊ ኦርሞ ነጻ አውጭ ድርጅት ደጋፊዎች ፣ በከተማው በሚኖሩ «አማራ» የሚሏቸው ክርስቲያኖች ላይ በድረደዋ ከተማ ተነስተው በነበረ ጊዜ፣ ከተማው ለሶስት ቀናት መረበሿ፣ በዚያም ምክንያት ድሬዳዋ ልዩ አስተዳደር እንዲኖራት መደረጉም ይታወሳል።
“ኢህአዴግ በመሀከላችን ወዳጅ መስሎ ገብቶ ያጣላናል፤ እንታገላለን! ለነጻነታችን ለመታገል ሞትን አንፈራም!”” ሲሉ የተናገሩት ሌላ የድሬደዋ ነዋሪ ደግሞ የአብሮ መስራት ጥቅም በማስረዳት፣ መከፋፈል የሚጠቅመው ለኢሕአዴግ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።
ይህ የሰማያዊ የድሬደዋ ስብሰባ፣ በጥናት በዝግጅትና በፕላን የተደረገ ሳይሆን፣ በችኮላና በእሽቅድምድሞሽ «ስለአንድነት ብቻ ለምን ይወራል? እኛም ዜናው ዉስጥ መሆን አለብን» ከሚል ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ያናገራሉ።
«ሰማያዊ በጎንደር ለብቻው ሰልፍ ጠርቶ ነበር። በድሬደዋ ለብቻው ስብሰባ ጠራ። የተገኘዉ ሕዝብ ግን በባህር ዳር ከተገኘው ሕዝብ ጋር ሲነጻጸር በጣም ጥቂት ነዉ። ይህ ቆም ብለው እንዲያስቡ ሊያደርጋቸው ይገባል» ያሉት በዚህ ጉዳይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ሰማያዊ የሕዝብን ጥያቄ በማዳመጥ ከመኢአድ እና አንድነት ጋር አብሮ መስራት እንዲጀምር ያሳስባሉ። «የድሬደዋ ሕዝብ ይህ ያንስበታል። ሰማያዊ ከመኢአድ እና ከአንድነት ጋር ሆኖ ወደ ድረደዋ እንደገና መመለስ አለበት። ሕዝቡ የተዝረከረከ ሳይሆን የተደራጀ፣ አንድ የሆነ አመራር ነው የሚፈልገው» ሲሉ በባህር ዳር የታየው በድሬደዋም እንዲደገም ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።
የአንድነት አመራር አባላት ፣ የፖለቲካ ፕርግራም ልዩነቶች እንደሌሉ በመገልጽ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ፣ ካልሆኑም ደግሞ በጋራ ጉዳዮች (ሰልፎችን ማዘጋጀት፣ ከዲፕሎማቶችን ጋር መነጋገር …) አብሮ ለመስራት ፋልጎት እንዳላቸው በይፋ ማሳወቃቸው የሚታወቅ ነዉ።
በሰማያዊ ፓርቲ አመራርና ደጋፊዎች መካከል፣ «ከአንድነት ጋር አብረን መስራት አለብን» የሚሉ እየበዙ እንደሆነም አንዳንድ ፍንጮች ይጠቁማሉ። የሰማያዊ አመራር «ከአቋማችን ዝንፍ አንልም» በሚሉ የጥቂቶች አምባገነናዊነት መዳፍ ዉስጥ ካልወደቀ በስተቀር፣ ዲሞክራሲያዊ አሰራር ካላ፣ በስማያዊ ፓርቲ አንዳንድ በሳል አመራር አባላት እንዲሁም ለሕዝቡ ቅርብ በሆኑ ተራ አባላት ግፊት፣ ሰማያዊ አክራሪ አቋሙን ያለዝባል የሚልም ግምት አለ።
sem11
sem13
sem12
sem10
sem9
sem7
sem6
sem5
sem4

No comments:

Post a Comment