“ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል።” ጄኔራል ሳሞራ የኑስ
ከሳምንታት በፊት ራሱን የአማራ ክልል ብሎ በሚጠራው የክልል አምባገነን ጁንታ አስተዳዳሪ ነኝ የሚለው የብኣዴን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አለምነህ መኮንን በድርጅቱ የውይይት መድረክ ላይ የአማራውን ህዝብ ለሃጫም እና ልጋጋም እንዲሁም መርዝ ብሎ መሳደቡን ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ የውጪ እና የውስጥ ተቃውሞ በየአቅጣጫው እየተነሱ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል::
ሰሞኑን በብአዴን አመራሮች እና በካድሬዎቻቸው መካከል ግለሰቡን የተመለከተ አለመግባባት መከሰቱን እና ጥያቄዎች ከአባላቱ በስፋት እየመጡ መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ጠቅሰው የአዲስ አበባ እና አከባቢው የድርጅቱ ካድሬዎች ግለሰቡ እና ሁኔታው እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል እስከማለት ደርሰዋል:: ይህንን ለመናገር የፈለገው ለምንድን ነው ተልእኮውስ ምንድነው? በሌላው ብሄር ላይ ይህ ነገር ቢነገር የድርጅታችን እርምጃ ምን ይሆን ነበር? ግለሰቡ በህግ ሊጠየቅ ይገባል::
የሚሉ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተጠየቁ ቢሆንም አመራሮቹ እስካሁን መልስ ከመስጠት ይልቅ ኢዲሞክራሲይዊ በሆነ መንገድ አለመግባባቶችን ከመፍታት ይልቅ በማስፋት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ጸረ-… እያሉ ጠያቄዎችን በመወንጀል እና ዋናውን ክትትላቸው ያደረጉት ድምጹን ቀድቶ ማን አውጣው የሚለውን የማይመለስ ጥያቄ ይዘው አደና ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል::
ከድርጅቱ አንዳንድ ካድሬዎች እንደሚሰማው የድምጹን ቅጂ ያወጡት የሕወሓት ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ እና ሕወሓትን በጥርጣሬ የሚይስቡ እንዲሁም ግንቦት ሰባት ናችሁ ብለው እርምጃ ሊወስዱባቸው የሚፈልጉትን የብኣዴን ካድሬዎች ለመዋጥ የተደረገ ሴራ ነው::በድርጅታችን ውስጥ የማይበጁትን አንጠባጥቦ የራሱን ለመሰግሰግ ያሰረው ሕወሓት መንገድ አገኘ ቢሉም በለላ ወገን ደግሞ በድርጅቱ የተማረሩ እና የለውጥ ፍላጎት ያላቸው የብአደን አመራሮች አሹልከው ያወጡት እንደሆነ ይነገራል።ካድሬዎቹ ክፉና ደጉን እንድንለይ ላደረገን ኢሳት ቴሌቭዥን ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ ተደምጠዋል:: በአመራሮቹ እና በካድሬዎቹ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በዚሁ ከቀጠለ አቶ አለምነህ የድርጅት ስራ ብቻ እንዲሰሩ ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት እና በክልሉ ላይ የተሰጣቸውን ስልጣን ለስም ብቻ እንዲቀመጥ የሚደረግ እንደሚሆን እና ቀስ በቀስ ከድርጅቱ ገፍቶ በማስወጣት አምባሳደር አድርጎ መሾም የሚሉ አስተያየቶች ከድርጅቱ አከባቢ ተደምጠዋል::
=============================================
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የብሄር ተዋፅኦን እና የመኮንኖች ቅነሳን በተመለከተ ከፍተኛ የሆነ ክርክር መነሳቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል:: እንደምንጮቹ ከሆነ በዚህ ሰሞን በተካሄዱ ተከታታይ ምስጢራዊ ስብሰባዎች ላይ የመከላከያ ሰራዊቱ በአንድ ብሄር በተሰበሰቡ ጄኔራሎች የተሞላ ነው: የመኮንኖች ቅነሳ ለምን አስፈለገ? ለምንስ አማራው እና ኦሮሞው ላይ አተኮረ ?ሰራዊቱ እና ቤተሰቡ በኑሮ ውድነት እየዋተተ ነው ከፍተኛ መኮንኖች በሙስና ተዘፍቀዋል ህገመንግስቱ አልተተገበረም የሚሉ የህዝብ አቤቱታዎች ተበራክተዋል … የሚሉ በሰራዊቱ ውስጥ ተጠንቷል ተብለው በቀረቡ ጥያቄዎች ዙሪያ ክርክር እና ውይይት የተደረጉ ቢሆንም በሕወሓት ጄኔራሎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንዲሁም ሞራልም ያልጠበቁ ስድቦች ካለውጤት እንደተበተኑ ምንጭኦቹ ገልጸዋል::
የአንድ ብሄር የበላይነት የምትሉት ለሕወሓት ያላችሁን ጥላቻ ለመግለጽ ነው ያሉት ጄኔራል ሳሞራ ጥያቄውን የፓርቲ ስብሰባ እስኪመስል ድረስ ጮኽውበታል::በትግል የከፈልነው መስዋትነት ውጤት እንጂ ከጎዳና ላይ መጥተን ማእረግ አልተሰጠንም::ከየብሄሩ አስፈላጊ ያልነውን ሊሰራልን የሚችለውን ጄኔራል እያደረግን እየሾምን ነው:: ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል። ሲሉ በመከላለያ ኢንዱስትሪ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ጠና ላይ ተሳልቀውባቸዋል::
የሰራዊቱ መኮንኖችን ቅነሳ በተመለከተ የማይታጠፍ እቅድ ስለሆነ ተግብርዊ ይሆናል ያሉት ሳሞራ ብሄር ለይተን ያደረግነው ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና የመከላከያ ሰራዊቱ ተጠንቶ የሚወሰድ ኢርምጃ ነው ብለዋል::ለሰራዊቱ የምናደርገው ድጎማ የለም::ያልተመቸው ካለ ሰራዊቱን መሰናበት ይሽላል ሲሉ በቁጣ የመለሱ ሲሆን ሙስና የሚባለው ማስረጃ ያለው ሄዶ ሊከስ ይሽላል ከዚህ ውጭእ ስም ማጥፋት ነው ሲሉ ተደምጠዋል :;ህገመንግስቱን እና መንግስታዊ ስርኣትን በተመለከተ መልካም አስተዳደር እና ልማት ስለሰፈነ ቢዚህ ልይ ምተኮር ስፈላጊ አይደለም ብለዋል:: ከሰራዊቱ አባልት መሃል ገብተን ያስጠናነው ጥያቄ ነው እየተወይየንበት ያሉትን ሰነድ በተመለከተ ማንም የጦር መኮንን አስተያየት ያልሰጠበት እና ያልጠየቀ ሲሆን ሁሉም በዝምታ በማዳመጥ ሳይወያይ መስማማት አለመስማማቱን ሳይገልጽ የተነገረውን እንደ መመሪያ ተቀብሎት መውጣቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::
No comments:
Post a Comment