ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ባለቤት ለማድረግ ታስቦ በ1997 ዓ.ም የተጀመረወ የቤት ልማት ፕሮጀክት ከተጀመረ አስር አመት ያህል አስቆጥረቷል፡፡
ምንም እንኳ ይህ የቤት ልማት ፕሮጀክት በርካታ ቤት ፈላጊዎችን የቤት ባለቤት ማድረጉ የማይካድ ቢሆንም በጋራ የመኖሪያ ቤቶቹ እውን የተባሉት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እየተጠቀሙበት ነው? የሚለው ጥያቄ በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሃሳብ ሆኖ መቆየቱ በቤቶች ልማት እቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ላሉ ችግሮች እንደማሳያ አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡
የቤት ልማት ተጠቃሚ ለመሆን በ1997 ዓ.ም ተመዝግበው እና በእጣ እድለኞች ሆነው ቤት ካገኙ ነዋሪዎች ውስጥስ ምን ያህሉ በደረሳቸው ቤት እየኖሩ ይገኛሉ? በእነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥስ ምን አይነት የህብረተሰብ ክፍል እየኖረባቸው ይገኛል? የኮንዶሚኒየም ሳይቶች የአኗኗር ድባብ ምን ይመስላል ?የሚሉና ከእዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ምንም እንኳ በእነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች በቅርብ ሚያውቋቸው ቢሆንም ለማሳያነት ያህል የጎተራ ጎንዶሚኒየም ሳይትን ነጥዮ በማውጣት የታዘብኩትን ላካፍለቹ፡፡
የጎተራ ኮንዶሚንየም ሳይት ግንባታው አልቆ ለነዋሪዎች ከተላለፈ ከአምስት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን በ78 ብሎኮች ከ2500 በላይ አባወራዎች የሚኖሩበት ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶቹ በአሰስፋልት የተሰሩ እንዲሁም ለአይን በሚያማምሩ አረንጓዴ ተክሎች ያማረ ውብ የመኖሪያ ሳይት ነው፡፡
የመኖሪያ ሳይቱ ለተጠቃሚ ከተላለፈ ጀምሮ አበይት የሚባሉ ለውጦችን ማሳየት የቻለ፣ «ምንም የማይታጣበት» የመኖሪያ ሳይት ነው ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም፡፡ በአሁኑ ሰዓት የመኖሪያ ቤቱ የአነስተኛና የመከከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እየኖሩበት ነው ብሎ ለመናገር የሚከብዱ በርካታ እውነታዎ እና ድርጊቶችን በመኖሪያ ሳይቱ ማስተዋል ይቻልል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ የኮንዲምንየም ሳይቱ ካሉት 2500 አባወራዎች ውስጥ 92 በመቶ ወይም 2300 አባወራ የቤቱ ባለቤት ሳይሆን በኪራይ የሚኖር እና የገቢው መጠም ከፍተኛ ሊባል የሚችል ነው፡፡
በዚሁ ሳይት የቤት ኪራይ ዋጋ የተጋነነ እና ለደሞዝተኛ እና ለዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል ከመክበድ አልፎ የማይታሰብ የሚባል አይነት ነው፡፡ ከስቱዲዮ ስስከ ባለ ሶስት መኝታ ቤቶችን ለመከራየት ከ 3000 እስከ 6500 ብር የሚጠየቅ መሆኑ ከላይ ለጠቀስኩት ሃሳብ ማጠናከሪያ ነው ብዮ አስባለሁ፡፡
ምንም እንኳ የቤት ባለቤት ከሆኑት ግለሰቦች ውስጥ በየወሩ የሚከፈለውን የባንክ ብድር ለመክፈል አቅም የሌላቸው ሰዎች የሚኖሩ እና ይህንኑ ለመክፈል የመኖሪያ ቤታቸውን ያከራዩ ቢኖሩም የተጠቀሰው የማከራያ ዋጋ ግፋ ቢል በሁለት አመት ውስጥ የቤቱን ጠቅላላ ዋጋ መሸፈን የሚችል መሆኑን ስናስተውል ሌላ ጥያቄ መፍጠሩ አይቀርም፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ከፍል መኪና የመግዛት አቅሙ ምን ያህል እንደሆነ ማንም ሊገነዘበው የሚችል እወነታ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን በእዚህ የጋራ መኖሪያ ሰይት የሚኖሩ ነዋሪዎች መካከል ምን ያህሉ መኪና ባለቤት ስለመሆናቸው በሳይቱ የተቋቋመው የፓርኪንግ አገልግሎት ምስክር ነው፡፡
እዚህ ጋር ግን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መኪና ሊኖረው አይገባም ከሚል ሃሳብ ሳይሆን ከመኪኖቹ መብዛት እና በከተማችን ውድ የሚባሉ እንደነ v8 አይነት መኪኖችን እያሽከረከሩ በጋራ መኖሪያ ቤቶች መኖር የህብረተሰቡን ሃብት ከመሻማት አንጻር ሊታይ ይገባዋል ከሚል ሃሰብ የመነጨ ነው፡፡
በመኖሪያ ሳይቱ ከሚኖሩ ነዋሪዎች መካከል ባለሃብቶች፤ የውጭ ዜጎች፣ አርቲሰቶች፤ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ጨምሮ የመኖሪያ አፓርትመንታቸውንእና ቪላቸውን በማከራየት በሳይቱ የተከዩ የሚገኙበት ሲሆን በሳይቱ ከ 30 የሚበልጡ የመጠጥ ቤቶች ሌሊቱን ሲቀውጡት ማየት የተለመደ ነው፡፡
ከእነዚህ መጠት ቤቶች መካከል 24 ሰአት የሚሰሩትን ጨምሮ የጫት ማስቃሚያ ቤቶች እና አልጋ ቤቶች(አልቤርጎ) ለተጠቃሚዎቻቸው አገልግሎት የሚሰጡበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በየ ሌሊቱ ድብድብ እና አምባጓሮ ማየት የተለመደ ነው ፡፡
ዋናው ቁም ነገር የቤቱ መከራየት ሳይሆን የገንዘብ አቅማቸው ከፍተኛ የሆኑ ግለሰቦች የግል መኖሪያ ቤቶቻቸውን በማከራየት በእነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚኖሩበት ወቅት የቤት ኪራይን ከማስወደድ ባለፈ የኮንዶሚንየም ባለቤቶች በከተማው ውስጥ የሚገኙ የመኖሬ ቤቶችን መከራየታቸው የማይቀር ነው።
ይህ በሚሆንበት ወቅት ታዲያ የቤት ባለቤት ያልሆነው ደሞዝተኛ እና በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደረወው የህብረተሰብ ክፍል ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ ከፍተኛ እና በኑሮ ላይ የሚፈጥረው ጫና መታየት ያለበት ጉዳይ ነው።
ታዲያ መንግስት ለድሆች መኖሪያ ብሎ የገነባው ይህው የኮንዶኒንየም ሳይት የሃብታሞች እና የቅንጡዎች መፈንጫ ሲሆን ምነው ዝም ማለቱ?
በቢንያም ገ/ክርስቶስ
no clarity
ReplyDelete