BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 21 February 2014

ኢሕአዴግ ሕዝብን የሰደቡና ያዋረዱ የብአዴን አመራር አባል ጎን ቆመ !

አቡጊዳ
ኢሕአዴግ ሕዝብን የሰደቡና ያዋረዱ የብአዴን አመራር አባል አቶ አለምነህ መኮንንን ተጠያቂ በማድረግና ከሃላፊነታቸው ከማንሳት ይቅል፣ ከጎናቸው መቆሙን አረጋገጠ።
መኢአድ እና አንድነት ፣ በአማራዉ ክልል የሚኖረው ሕዝብ ላይ ከአንድ መሪ የማይጠበቅ አሳዛኝ፣ ንቀት አዘል አስተያየት የሰጡት አቶ አልምነዉ መኮንን ከሃላፊነታቸው እንዲነሱና ለፍርድ እንዲቀርቡ መጠየቁ ይታወቃል። ኢሕአዴግ ፓርቲዎቹ ያቀረቡትን ጥያቄ አናንቆ፣ ምንም ምልሽ ባለመስጠቱ፣ አንድነት እና መኢአድ ለየካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ በጋራ መጥራታቸዉን ይፋ አድርገዋል። ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳዉ የተጀመረ ሲሆን «ሕዝብን የሚንቁ የብአዴን መሪዎች የአመራር ብቃት የላቸውም» የሚሉ አባባሎች የያዙ ጽሁፎቸ ሲበተኑና በየቦታዉ ሲለጠፉ እንደነበረ ፍኖተ ነጻነት እና የአንድነት ሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ዘግቧል።
የባህር ዳሩ ሰልፍ ሞቅት እያየለ ሲመጣ፣ ኢሕአዴግ ነገሩ በጣም ስላሳሰበው፣ ሙሉ ሙሉ የሚቆጣጠረዉን ኢቲቪ በመጠቀም፣ አቶ አለምነው ማስተባበያ እንዲሰጡ ያደረገ ሲሆን፣ በባህር ዳርም ፣ አቶ አልምነው በኢቲቪ የተናገሩት አባባሎች ያቀፈ የማስተባበያ ወረቀት መበተን ጀምሯል።
ኢሕአዴግ አቶ አልመነዉ መኮንን በኢቲቪ ቀርበው ማስተባበያ እንዲሰጡ ማድረጉና አንድነት/መኢአድ እየበተኑ ያሉ ወረቀቶችን ለመመከት፣ የራሱ ወረቀቶችን ማሰራጨት መጀመሩ በተመለከተ አስተያየት የሰጡን አንድ የፖለቲካ ተንታኝ፣ «እኝህን ሰዉዬ ቀስ ብለው ያነሳሉ የሚል ግምት ነበረኝ። አሁን ግን በሙሉ ኃይል ከርሳቸው ጎን ለመቆም አገዛዙ የወሰነ ይመስላል። ይሄም ጉዳዩን በኦፌሴል ከግለሰብ ወደ ፓርቲ ከፍ አድርጎታል» ሲሉም አገዛዙ ሕዝብን ከሰደቡና ካዋረዱ አንድ ግለሰብ ጋር መቆሙን እንደመርጠ ያስረዳሉ።
ኢሕአዴግ በባህር ዳር በበተናቸው ወረቀቶች ፣ መኢአድ እና አንድነትን «ጸረ-ሰላም ኃይሎች» ፣ «የትምክህትና የኪራይ ሰብሳቢ ወኪሎች» በሚል የገለጻቸው ሲሆን፣ ለሕዝብ ይፋ የሆነውን የአቶ አልመነህ ሞኮንን ንግግር የያዘዉን ኦዲዮ ፋይል ደግሞ «ተቆራርጦ የተቀጠለ» በሚል ለመካድ የመሞከር ነገር ይታያል።
አቶ አልመነህ የተናገሩትን እና ኢቲቪ ቆርጦ ቀጥል ነው ያለውን ኦዲዮ ለመስማት እዚህ ይጫኑ !
ኢሕአዴግ በባህር ዳር የበተነዉን ወረቀት ይመልከቱ፣andm
====================================
- የአመራር ስም ማጥፋት፣ የቆርጦ ቀጥሎች ፖለቲካና የምርጫ ዋዜማ ነጠላ ዜማ ነው !
- የአማራ ሕዝብንና ትምክህትን ለያይተው መመልከት ባልቻሉ የጥፋት ፖለቲከኞች ሰፊው የአማራ ሕዝብ አይደናገርም!!
- ትምክህት የአማራ ሕዝብ ጠላት እንጂ ወዳጅ ሆኖ አያዉቅም ሊሆንም አይችልም!
- ቀጥል የጥፋት ፖለቲካ የብ አዴን ኢሕአዴግን አመራሮች ስም ማጥፋት የጸረ-ሰላም ኃይሎች የዘዉትር ተግባር ስለሆነ አዲስ ነገር አይደለም!!
- የአማራ ሕዝብ የተቀዳጃቸው የሰላም የዲሞክራሲና የልማት ጉዞ በትምህክህትና በኪራስይ ሰብሳቢ ወኪል ፓርቲዋ ፈጽሞ አይደናቀፍም !!
ብ፤አዴን የትምክህትና ኪራኡ ሰብሳቢነት አመለካከትን ሲዋጋ ኖሯል። የጸረ ትምክህትና ጸረ-ኪራስይ ሰብሳቢነት ትጉ ተጠናክሮ ይቀጥላል !
ከተማችን ባህር ዳር እያስመዘገበች የቆየችዉን ልማት በተለይ በዚህ አመት እየተካሄደ ያለዉን የተሟሟቀ የመሰረተ ልምትና የሥራ እድል ፈጠራ እንዲሁም የትልልቅ ኮንፈራንሶች ማእከል መሆኗ ያልተዋጠላቸው የጥፋት ፖለቲከኞች የሚነሱት ወሬ ከልማት ስራችን ሊያስተጓጉለን አይችልም !

No comments:

Post a Comment