BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Wednesday, 19 February 2014

77ኛው የኢትዮጵያ ሰማእታት ቀን ተከብሮ ዋለ

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን በጣሊያን ወራሪ ሃይል በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን በመላው አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየተዘከረ ነው።

በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰምአታት ሃውልት ጀግኖች አባት አርበኞች በተገኙበት በአሉ ተከብሯል።
የካቲት 12፣ 1929 ዓም አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ኢትዮጵያውያን ግራዚያኒን ለመግደል የጣሉትን ቦንብ ተከትሎ፣ የጣሊያን ወራሪ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ  ከ30 ሺ በላይ ኢትዮጵያውን መገደላቸው ይታወቃል።
በ5 አመቱ የጣሊያን ወረራ  ወቅት አእላፍ አእላፍ የኢትዮጵያ ጀግኖች ወረራውን በመቃወም ሲዋጉ በጀግንነት መውደቃቸው ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment