የአዲስ አበባ ዞን ሊቀመንበርና ስራአስፈፃሚዎችን ለመምረጥ የ3 አስመራጭ ኮሚቴ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተደርጓል፤ በመቀጠልም ለሊቀመንበርነት 3 አባላት ተጠቁመዋል፡፡ በዚሁ መሰረት
አቶ ዳዊት ሰለሞን
አቶ ትግስቱ አወሉ
አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን ለዕጩ ሊቀመንበርነት ተጠቁመዋል፡፡
3ቱም ዕጩዎች እያንዳንዳቸው የ7 ደቂቃ የምረጡኝ ቅስቀሳ አድርገዋል፤ ለሊቀመንበርነት ጠንካራ ውድድር ከተደረገ በኋላ እና የድምፅ አሰጣጡ በምስጢር ከተካሄደ በኋላ በቆራጥ አመራራቸው በአንድነት አባላት ጀነራል በሚል መጠሪ ያገኙት አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን በሊቀመንበርነት ተመርጠዋል፡፡
በተጨማሪም በዚሁ እለት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚዎች ተመረጠዋል በዚሁ መሰረት
ነብዩ ባዘዘው ………. = 1ኛ
ዳዊት ሰሎሞን = 2ኛ
ታደለች አበራ = 3ኛ
እጥፍወርቅ በልስቲ = 4ኛ
ያሬድ አማረ = 5ኛ
ስንታየው ቸኮል = 5ኛ
እንግዳወርቅ ማሞ = 7ኛ
የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ በመሆን ቃለመሃላ ፈፅመዋል፡፡ በመጨረሻም አዲሱ የአዲስ አበባ ዞን ሊቀመንበር አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን ጉባኤውን በንግግር ዘግተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment