BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Sunday, 16 February 2014

“በ ‘ጨቋኝ አማራ’ ስም የተጨቆነው ሕዝብ”

አዲስጉዳይ በቅጽ 8 ቁጥር 203 ቅዳሜ የካቲት 8፣ 2006 ዕትሙ፤
የብአዴን ከፍተኛ ባለሥልጣንና የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዓለምነው መኮንን በካድሬዎች ሥልጠና ላይ የሚመሩትን ሕዝብ የሚያናንቅ ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ የአማራ ሕዝብ ጉዳይ የመነጋገሪያ ርዕሰጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ የዐቢይጉዳይ አምዳችንም ይኽን ጉዳይ የተመለከተ “በ ‘ጨቋኝ አማራ’ ስም የተጨቆነው ሕዝብ” በሚል ርዕስ ዘገባ ተስተናግዶበታል፡፡
እስረኞች፤ ስለ የእስረኞች አያያዝና እስር ቤቶችን በተመለከተ ለአዲስጉዳይ ያካፈሉትን መረጃ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ረዳት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከሆኑት አቶ አዲሱ ጴጥሮስ ምላሾች ጋር በሃተታ አምድ ላይ ለንባብ በቅቷል፡፡
የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በቃለምልልስ ዓምዳችን ላይ “አማራው ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደተሰደበ ነው የሚሰማኝ” በማለት የባለሥልጣኑ ንግግር እንዳስከፋቸው የተናገሩ ሲሆን አቶ ዓለምነው ይቅርታ ጠይቀው ሥልጣናቸውን መልቀቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
ሰሞነኛ ዓምድ ላይ “ከፍርድ ቤቶች ፍትሕ አይገኝም” ብለህ ጽፈሃል ተብለው ስለታሰሩትና ትናንት አርብ የካቲት 7፣2006 በሁለት ዓመት ገደብ እንዲፈቱ ስለተወሰነባቸው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ አሥራት ጣሴ የሚዘግብ ጽሑፍ ተስተናግዷል፡፡
የኢትዮጵያ ጦር ዳግም ወደ ሱማሊያ መሠማራት አንደምታዎችን የተመለከተ ጽሑፍ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሠፍሯል፡፡
በቁጥር 201 ዕትም ጥበባት ዓምድ ላይ ማርቆስ የኔዓለም “እኛ እንጽፋለን እነሱ ይከብራሉ” ሲሉ መጽሐፍ አሳታሚዎች ደራሲዎች ላይ ስለሚያደርሱት ተጽዕኖ ላሰፈሩት አስተያየት ቃል ኪዳን ይበልጣል “ለደራሲያን የተሻለ ተጠቃሚነት” በሚል ርዕስ የራሳቸውን ዕይታና መፍትሔ ያሏቸውን ሃሳቦች አስቀምጠዋል፡፡
በሦስት ቀን ልዩነት የ1500 እና የ3000 ሜትር ውድድሮችን ሬከርድ በመስበር አዳዲስ የዓለም ሬከርዶችን ያስመዘገበችው አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በአንድ ጉዳይ አምድ ከእንዳለ ተሺ ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡
ኢብራሒም ሻፊ በስፖርት አምድ “የኢትዮጵያ እግር ኳስ፡ በፖለቲካ የሚነዳው ምስኪኑ ዘርፍ” በሚል ርዕስ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ስለ ሀገሪቱ እግር ኳስ ያላቸው ምልከታ የተሳሳተ እንደሆነ ይገልጻል፡፡
በየካቲት 12 በግራዚያ ስለተጨፈጨፉት ሰማዕታት “የየካቲት 12- ጥቋቁር ሰማዕታት!” በሚል ርዕስ በሰለሞን ተሰማ ጂ. ሰማዕታቱን የሚዘክር ጽሑፍ ቀርቧል፡፡ ከዓመታት ያላሰለሰ ጥረት በኋላ በቁጥጥር ስለዋለ ነፍስ ያጠፋ ወንጀለኛ “ከራቤል እስከ ጎሮ” የሚል እውነተኛ ታሪክ በወንጀል አምድ ተስተናግዷል፡፡ ዶክተር ብርሃኔ ረዳኤ ስለ ብጉርና ቡጉንጅ “ብቡ” በሚል ስለችግሮቹ ትንታኔ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ እትም ስለ ብጉር ጽፏል፡፡ በቀጣዩ ሳምንት በይደር ያቆየውን ስለቡጉንጅ ይጽፋል፡፡ ዳንኤል ክብረት “የዋርካው ዜጎች” በሚል ርዕስ ስለ ኢትዮጵያችን ወቅታዊ ሁኔታ ይገልጻል፡፡ ኤፍሬም እሸቴ የአሜሪካውያንን ሕይወት እያመሳቀለ ያለውን ከፍተኛ ቅዝቃዜና የበረዶ ክምርን አስታኮ “በረዶና ጨው፤ ክፉ ቀንና ጥጋብ” በሚል የራሱን ምልከታ አስቀምጧል፡፡ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር በኑሮ አምድ “የትዳር ቀን + የሴቶች ቀን” በሚል ርዕስ ኑሮ በሁለት ጎጆዎች ሥር ይህን ይመስላል ይለናል፡፡ አሌክስ አብርሃም “ከጥቁሩ መስተዋት ኋላ” የሚል የወግ ጽሑፉን አቅርቧል፡፡
በነጻ መድረክ አምድ “እውነት ኢህአዴግ ተምሮ አውቆ አስተውሎ ለመለወጥ ይችላል? ይፈልጋልስ?” በሚል ርዕስ የአቶ አሥራት ጣሴ አስተያየት ተስተናግዷል፡፡
መጽሔታችሁ አዲስጉዳይን እንድታነቡ እየጋበዝን መልካም የእረፍት ቀናትን እንመኛለን፡፡
ኞች አያያዝና እስር ቤቶችን በተመለከተ ለአዲስጉዳይ ያካፈሉትን መረጃ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ረዳት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከሆኑት አቶ አዲሱ ጴጥሮስ ምላሾች ጋር በሃተታ አምድ ላይ ለንባብ በቅቷል፡፡

No comments:

Post a Comment