BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Saturday, 15 February 2014

በሚኒሶታ የሕወሓት በዓል በድብቅ ተከበረ

ለካቲት 11 በሚል የሕወሓት አፍቃሪና የሕወሓት ተጠቃሚ ብቻ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ብቻ የሚያከብሩት በዓል በሚኒሶታ በድብቅ ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎች ብቻ በተገኙበት መከበሩ ታወቀ። ባለፈው ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 8 ቀን 2014 በተበተነው የሚኒሶታው የኢትዮጵያ ትግራይ ኮምዩኒቲ ያዘጋጀው በዓል ፍላየር ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ አለመታየቱ ብዙዎች የሚኒሶታ ነዋሪዎችን እያነጋገረ ይገኛል ተብሏል።
በሚኒሶታ ባለፈው ፌብሩዋሪ 8 በተከበረው ለካቲት 11 በዓል የተበተነውፍላየር መግቢያ “ጥሪ ለተደረገላቸው ብቻ” የሚል ሲሆን ይህን የተመለከቱ ሰዎች ጉዳዩ ምንድን ነው? የሚል ጥያቄን እንዲያነሱ አስገድዷቸዋል።
በተለይም በሚኒያፖሊስ ነዋሪ የሆነ አስተያየት ሰጪ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጸው “እውነትም ትግራይ የምትባል ሃገር የመመስረት ሃሳባቸውን አሁን በትክክል አረጋግጠውልናል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። ከዚህ ቀደም ወደ ሱዳን ሲጓዙ በመኪና አደጋ የሞቱትን የትግራይ ተወላጅ አርቲስቶችን በተመለከተ በተመሳሳይ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የትግራይ ሕዝብን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ለመለየትና ሃዘኑም የትግራይ ብቻ ለማድረግ ተሞክሯል በሚል የሚተቹት እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች የሚያከናውኗቸውን ዝግጅቶች በድብቅ ሌላው ኢትዮጵያዊ እንዳይገኝ የሚያደርጉበት ሁኔታ እንዳልገባቸው አስታውቀዋል።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው “ከዚህ ቀደም ለአባይ ቦንድና በሌሎችም ጉዳዮች ሕወሓቶች የጠሯቸው ስብሰባዎች መሰናከላቸው የፈጠረባቸው ስጋት ነው ይህን በዓል በድብቅ እንዲያከብሩ ያደረጋቸው” ሲሉ ይናገራሉ።
በሚኒሶታ በድብቅ ለተከበረው የሕወሓት በዓል የተበተነው ፍላየር (ከኢትዮጵያ ባንዲራ ውጭ) የሚከተለው ነው ሲሉ ምንጮች አድርሰውናል፦

No comments:

Post a Comment