የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአስመጭና ላኪ እንዲሁም በግንባታ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች እንደሚገልጹት፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ የአገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ በእጅጉ እየተጎዳ ነው። ምንም እንኳ መንግስት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዳላጋጠመ በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ በርካታ ነጋዴዎች ወደ ባንኮች ሲሄዱ፣ የሚፈልጉትን መጠን የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አይችሉም። ከባንኮቹ የሚሰጣቸው መልስ ምንዛሬ የለም የሚል መሆኑን አንዳንድ ነጋዴዎች እንደሚናገሩ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ገልጿል።
አንዳንዶች እንደሚገምቱት አገሪቱ ከውጭ ንግድ በእያመቱ እስከ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት በማቀድ ብትንቀሳቀስም፣ ማሳካት የቻለችው የዚህን ግማሽ ያክል ብቻ በመሆኑ፣ አሁን ለሚታየው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አስተዋጽኦ አድርጓል።
No comments:
Post a Comment