የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም በከንቲባ ድሪባ ኩማ ፊርማ ተጽፎ በወጣው ደብዳቤ አቶ ካሓሰ ወ/ማርያም ከየካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር በቢሮና በኃላፊ ደረጃ ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል።
“የተለያየ መ/ቤት ስያሜ እያወጡ እና ለህዝቡ ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተቋማትን እየፈጠሩና እያዋቀሩ ለስራ እንቅስቃሴ እየተባለ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የህዝብ ውስን ሃብት የሆነውን የመንግስት በጀት እየመደቡ ከተማዋን በሙት መንፈስ ለመምራት ጥረት እያደረጉ ” ነው በማለት የመስተዳድሩ ሰራተኞች ለኢሳት ተናግረዋል።
የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ጽ/ቤት ሱልልታ ውስጥ በጣም ዘመናዊ በሆነ ህንፃ ተገንብቷል። ህንጻው የሰልጣኖች ማደሪያ እና የመኖሪያ ቤትን አካቶ ይዟል።
No comments:
Post a Comment