ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍኖተ ነፃነት እንደዘገበው-በኢትዮጵያ የአዉሮፓ ሕብረት ልኡካን ቡድን መሪ አምባሳደር ቻንታል ሔበሬሽ፣ በአዉሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ እና የሕንድ ዉቂያኖስ አካባቢ ዴስክ ኦፌሴር ቪክቶሪያ ጋርሲያ ጉሌን እና ቶማስ ሁይገባርቴስ የተሰኙ ፣ የአዉሮፓ ሕብረት ሃላፊ ፣-ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ዉይይት አድርገዋል።
ከአንድ ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ ከጠ/ሚኒስተር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር እንደተነጋገሩ የገለጹት የአዉሮፓ ሕብረት ልዑካን፣ የአንድነት ፓርቲ የጠራዉ የሚሊዮኖች ድምጽ ሁለተኛ ዙር ንቅናቄ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።
ልዑካኑ አያይዘውም አንድነት ፓርቲ ፈቃደኛ ከሆነ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
አንድነት ፓርቲ በመወከል ከአዉሮፓ ሕብረት ጋር የተነጋገሩት ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ሃብታሙ አያሌው አንድነት አሁን እያደረገ ያለው “የሚሊዮነሞች ድምፅ ለነፃነት” የተሰኘው ንቅናቄ ከዚህ በፊት የተደረገ ተመሣሳይ እንቅስቃሴ ተከታይ ዘመቻ መሆኑን ለልዑካኑ አስረድተዋል።
ፓርቲዉ አዲስ አበባን ጨምሮ በ17 ከተሞች ፣ በፍትህ እና በመሬት ይዞታ ለውጥ ፣ ዙሪያ ከሕዝብ ጋር ዉይይቶችን ማድረጉን የጠቀሱት የአንድነት አመራሮች፤ በተጓዳኝ በተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን እንዳደረጉም አብራርተዋል።
አንድነት ፓርቲ ከዚህ በፊት ባደረጋቸዉ በርካታ ሰልፎች በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ አንዳችም ጉዳት አለመኖሩን የገለጹት የፓርቲው አመራሮች ፣ ወደፊት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችም ሰላማዊና ሕዝባዊ መስመራቸውን ጠበቁ እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል።
የአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች በበኩላቸው አንድነት ይዞት የተነሳዉ የመሬት ጥያቄ ተገቢ፣ ወቃታዊና ለኢትዮጵያ ጥቅም የሚያመጣ እንደሆነ መግለፃቸውን ፍኖተ ነፃነት አመልክቷል።
በመጨረሻም የህብረቱ ልዑካንበመጪው የ2010 ምርጫ ዙሪያ አንድነት ያለውን አቋም እንዲያስረዳቸው ላቀረቡት ጥያቄ አመራሮቹ “ በሰጡት ምላሽ ፓርቲያቸው አገር አቀፍ መዋቅሩን እያሰፋ እንደሆነም በመጥቀስ፤ ለምርጫ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን ነው። በሁሉም ክልሎች ለፌዴራልም ሆነ ለክልል ምክር ቤቶች ተወዳዳሪዎችን ከወዲሁ እያዘጋጀን ነው” ብለዋል።
No comments:
Post a Comment