ለሴቶች መብትና እኩልነት መከበር የሚንቀሳቀሱ ዜጎች በአለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ
ባልሆኑ ተቋማት አማካኝነት የዘንድሮውን አለም አቀፍ የሴቶችን ቀን የካቲት 29 ቀን 2006 ዓ.ም. (ማርች 8
ቀን) „ለሴቶች እኩልነትና ለሁሉም ብልፅግና“ በተሰኘ መርሃ ግብር የተለያዩ ሴት ነክ በሆኑ ርዕሶች ላይ
መግለጫዎችን በማውጣትና የተለያዩ ህዝባዊ ውይይቶችን በማዘጋጀት ካለፉት ቀናቶች ጀምሮ እያከበሩት ይገኛሉ።
በሀገራችንም ይህንን መርሃ ግብር ከተጨባጩ ሁኔታዎች ጋር በማዛመድ ለመብት መከበር የሚታገሉ እንደ
ኢሕአፓ የመሰሉ ሀገር ወዳድና እንዲሁም ለሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር የሚንቀሳቀሱ እንደ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ ድርጅቶች ይፋና ይፋዊ ባለሆነ ሁኔታ ባለፉት አመታት
እንዳደረጉት ሁሉ „በምን ሁኔታ ላይ እንገኛለን፤ የት ደርሰናል? ምንስ ይቀረናል? ወደፊትስ ምን ማድረግ
በምትማቅቀው ሀገራችን የኢትዮጵያ ሴቶች ስለሚገኙበት ሁኔታ በጥልቀት በመዳሰስም ለሚመለከታቸው በአለም
አቀፍ ደረጃ ጭምር ላሉ መንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት በማሳወቅ ከተጨቆኑና ከሚበደሉ ሴት
ዜጎቻችን ጎን እንዲቆሙና ለነፃነታቸው መጎናፀፍ የሚያደርጉትን ትግልም እንዲደግፉ ጥሪ በማቅረብም ቀኑን
ያስታውሱታል።
የሀገራችን ሴቶች ከወንዱ አቻዎቻቸው ባልተናነሰ በኢትዮጵያን ሕዝብ የትግል ታሪክ ውስጥ ደማቅና አኩሪ የትግል
ገድል ቢፈፅሙም የእኩልነት መብታቸው በሚፈለገውና አግባብነት ባለው ደረጃ ገና አልተከበረላቸውም።
የድካማቸውን ፍሬ እንዲቋደሱ መድረኩ አሁንም ድረስ አልተመቻቸላቸውም። ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ወጣት
ሴቶችና ልጆች ለወሲብ ግንኙነት በግዴታ መዳረጉ እንደቀጠለ ነው። የኑሮው አስከፊነት ያነሰ ይመስል በአገዛዙ
ሙሉ ትብብር ለዘመናዊ ባርነት ተዳርገው (በተለይም ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት) ግድያና የተለያዩ
እንግልቶችና በደሎች እየተፈፀመባቸው ይገኛሉ። በቅርቡ በሱዳን ሀገር አንዲት ኢትዮጵያዊ ወጣት በጋጠ ወጥ
ወንጀለኞች የአስገድዶ መድፈር ድርጊት ቢፈፀምባትም ፍትህ እንድታገኝ ሕጋዊ እርዳታ ከመስጠት ይልቅ
በሚያሳዝንና አሳፋሪ በሆነ ደረጃ የሱዳን ባለሥልጣናት የዝሙትነትና የሥነምግባር ጉድለት ዘለፋ አድርሰውባታል።
በሀገራችን ለጋ ሕጻን በሆኑ ሴቶች የሚካሄደው የግርዘት ድርጊት አሁንም የተስፋፋ ነው። ሴቶች ለእኩል ሥራ
እኩል ደሞዝ አይከፈላቸውም። በራሳቸው ላይ ሙሉ የሥልጣን ባለቤትነት የላቸውም። ራሳቸውን በራሳቸው
ለማስተዳደር የሚያስችላቸው እንደ ትምህርት፤ የጤንነትም ሆነ የሥራ እድል የማግኘት እድላቸው የጠበበ ነው።
ብዙሃኑ ሴቶች የገጠር ነዋሪ ናቸውና በሥርአቱም ሆነ በወንድ ማናህሎኝነት የሚደርስባቸው ችግርና በደል የከፋና
የመረረ በመሆኑ ለዘመናዊ ባርነት ተዳርገዋል። የጠለፋ ድርጊት ከሚፈጽሙባቸው ወንጀለኞች ጋር ያለ ፍላጎትና
ፍቃዳቸው የጋብቻ ፍጥምጥም እንዲያደርጉ ስለሚገደዱም በደላቸው እጥፍ ድርብ ነው።
ታዲያ ይህ ሁሉ የመብት ረገጣ እየተስፋፋና እየተካሄደ ባለበት ሁኔታ የወያኔ አገዛዝ ሴቶች ነፃነታቸውንና
እኩልነታቸውን ተጎናፅፈዋል፤ ዴሞክራሲ በሂደት እየጎለበተ ነው በማለት የተፃፈበትን ወረቀት ያህል እንኳ ክብደት
የሌለውን ሕግ እያጣቀሰ የሚነዛው መጠነ ሰፊ ፕሮፓጋንዳ ውሃ የማይቋጥር ነው። የጥቃት እርምጃ ለማድረግ
በሚሰማራባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ ለምሳሌ በአማራ፤ በሶማሌና በኦሮሞ ሴቶች ላይ ሆን ተብሎ የዘረኝነትና
አድሏዊ ተግባራት እየፈፀመባቸው ይገኛል። ይህን የመሰለ ተግባር የባዕዳን ደጋፊዎችን አጀንዳ ለማስፈጸም
በተሰማራበት ጎረቤት ሶማሌ እንኳ ሳይቀር መፈፀሙ የተጋለጠ ነው።
http://www.ethiolion.com/Pdf/03072014Setoch.pdf
http://www.ethiolion.com/Pdf/03072014Setoch.pdf
No comments:
Post a Comment