
የከተማው ከንቲባዎች ቶሎ ቶሎ መቀያየር በክልሉ ያለውን የባለስልጣናት ሙሰኝነት ያሳያል ያሉት ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የከተማው አስተዳደር ፅ/ቤት ሰራተኛ፤ ከ1ሺ በላይ ግለሰቦች ካርታ ይዘው መሬት ሳይረከቡ መቆየታቸው ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የዛሬ ዓመት ከመሬት ሽያጭ ሙስና ጋር በተያያዘ በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ ተመስርቶባቸው ከአንድ ዓመት በላይ በእስር የቆዩ የቀድሞ የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ሽመልስ ሀሰኖን ጨምሮ ከአስራ አምስት በላይ የፊንፊኔ ዙሪያ የአስተዳደር ሠራተኞችና መሃንዲሶች በነፃ መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡
በቅርቡ በተካሄደው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ለዘጠኝ ሰዓታት ያህል የተገመገሙት የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ሃይሌም ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ አቶ መስፍን ለአራት ዓመታት የመሩትን ድርጅት በምትካቸው ወክለው እንዲወጡ በተወሰነው መሰረት በኦሮምያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በአስተዳደር ሃላፊነት ሲሰሩ የቆዩትንና በህግ የማስተርስ ምሩቅ የሆኑትን አቶ ተመስገን ባይሳን ወክለው እንደወጡ ተጠቁሟል፡፡
http://addisadmassnews.com/
No comments:
Post a Comment