ሰሞኑን በስዊድን በነበረን ቆይታ ከጎናችን ሆነው ሲንከባከቡን ከነበሩት መካከል አንዱ መርሶ ነው።
መርሶ፣ ከበርካታ ዓመታት የስዊድን ቆይታ በሁዋላ እ፣ኤ.አ በ2012 ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ወደ ኢትዮጵያ አቅንቶ ነበር። ቦሌን
እናትም
ለልጃቸው ከጠመቁለት ጠላ በትልቁ ብርጭቆ ከቀዱለት በሁዋላ ከናፈቃቸው ልጃቸው ጋር የሆድ የሆዳቸውን ሊያወሩ
አጠገቡ ተቀምጠው ዓይን ዐይኑን ማዬት ጀመሩ።
ያሳዝናል…
ወዲያውኑ በሩ ተንኳኳ፤ በሩ ሲከፈት ሦስት የደህንነት ሀይሎች ናቸው። ወደ ቤት በመግባት መርሶን ባ’ስቸኳይ ኢትዮጵያን ለቅቆ
ወዲያውኑ በሩ ተንኳኳ፤ በሩ ሲከፈት ሦስት የደህንነት ሀይሎች ናቸው። ወደ ቤት በመግባት መርሶን ባ’ስቸኳይ ኢትዮጵያን ለቅቆ
እንዲወጣ በመንገር ይዘውት ሄዱ። የተቀዳለትን ጠላ
ሳይቀምስ ኢትዮጵያ በደረሰ በሦስት ሰዓታት ውስጥ ወደመጣበት ወደ ስዊድን “ዲፖርት”ተደረገ።
“ምክንያቱ ምን ይመስልሀል?” ብዬ ጠይቄው ነበር። እሱም በውል ምክንያቱ ይህ ነው ብሎ ለመናገር እንደሚቸገር፣ ሆኖም በውጪ
ሀገራት በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በመሳተፉ
ምክንያት ሊሆን ይችላል ብሎ እንደሚገምት ነግሮኛል።
“ይህ ሀገር የኛ ነው፤ኢህአዴግን የምትቃወሙ ሁሉ በዚች ሀገር ላይ ምንም ድርሻ የላችሁም” ይመስላል ነገሩ።
No comments:
Post a Comment