ከኖርዌ/ኦስሎ
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ሴቶች ክፍል በዛሬው እለት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8, 2014 ምክንያት በማድረግ ዝግጅቱን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።
ዝግጅቱ ከቀኑ 11፡00 በዲሞክራሲያዊ ለውጥ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተከናወነ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ሊቀመንበር አጭር ንግግር አድርገዋል። ሴቶቹም በኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች እህቶቻቸው ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና እና የሰብአዊ መብት እረገጣ በማጋለጥና በመቃወም ገንቢ ውይይት ያደረጉ ሲሆን የድርጅቱ የሴቶች ክፍል ሰብሳቢ የመግቢያ ንግግር እና ጣይቱ ቡጡልን የሚያስታውስ ግጥም አቅርበዋል በመቀጠል ምክትል ሰብሳቢዋ እንዲሁ አድዋን በተመለከት አጠር ያለ ግጥም እና አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ አጭር ገለፃ አቅርበዋል በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ግጥሞች እና ንግግሮች እንዲሁም አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ጭውውቶች ፤ የጥያቄና መልስ ጊዜም ነበር። በተጨማሪ የምሳና እና ሻይ ቡና ግብዣ አድርገዋል በዚህ ዝግጅት ላይ ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን በእንግድነት ታዳሚያችን ነበረች።

በሐገራችን ሴቶች በፖለቲካው ዘርፍ ያላቸው ሚና አነስተኛ ቢሆንም ይህንን ሁሉ ተጋፍጠው የራሳቸውን የፖለቲካ አቋም ለመግለፅ በሞከሩና ወደ ፖለቲካው መድረክ ብቅ በሚሉ ሴቶች እህቶቻችን ላይ ገዢው ፓርቲ እያደረሰ ያለውን ጫና ሁላችንም የምናውቀው ነው ለዚህም ምሳሌ የሚሆኑ እህቶቻችን እንደነ ርዮት አለሙና ብርቱካን ሚደቅሳ የመሳሰሉት በነፃነት የራሳቸውን አስተሳሰብ እንዳያራምዱ እየተኮረኮሙና በእስርቤት እየተወረወሩ በሃገራቸው ጉዳይ ላይ እንደማይመለከታቸው ተደርገው እየተቆጠሩ ይገኛሉ። በአንፃሩ ደግሞ ለወያኔ የወገኑ የፓርቲው ደጋፊ የሆኑ ምንም አይነት የትምህርት ደረጃና እውቀት ችሎታቸው ሳይመዘን አንዳች መስፈርት ሳይቀመጥላቸው የአንድ አካባቢ ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ወይም ከጫካ በመምጣታቸው በስልጣን ላይ ተቀምጠው ለፍተው የተማሩ ሴቶች እህቶቻችንን ዋጋ በማሳጣት በደመነብስ ሐገር ሲያስተዳድሩ ይታያል።
በጠቅላላው ገዢው ፓርቲ በዘር በየሚያራምደው ፖለቲካ ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ አብዛኛው ህዝባችን በገዛ ሐገሩ እንድ ሶስተኛ ዜጋ እየተቆጠረ ሐሳቡን በነፃ የመግለፅ እና የራሱን የፖለቲካ አቋም ማንፀባረቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ከደረስን በርካታ አመታት ተቆጥረዋል ዜጎች ሐሳባቸውን በነፃ በመግለፃቸው ብቻ ለእስር፤ ለግርፋት፤ ለእንግልት ብሎም ሐገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ተገደዋል። ይሄ አይነቱ የአምባገነኖች አካሄድና አመለካከት እስካልተቀየረ ድረስ ሴቶች ብቻ ሳንሆን ሁላችንም በሐገራችን ጉዳይ ላይ ያገባናል ብለን በጋራ መወሰን አንችልም። በሐገራችንም የህግ የበላይነት ሊረጋገጥ አይችልም በመሆኑም አምባገኑና ዘረኛው የወያኔ ቡድን ከስልጣን ተወግዶ ሁላችንም የምንመኘው ዲሞክራሲ በሃገራችን እንዲመጣ ሴቶችም ከፍተኛውን ሚና መጫወት አለብን በተለይ በውጭ የምንገኝ ሁሉ ባለንበት ሃገር ለህዝባችን ድምፅ ሆነን በመጮህ የወያኔን ሴራ በማጋለጥ አብረን መታገል ይኖርብናል ይሄ የኔ አመለካከት ነው በጋራ እንታገል።
ድል ለተጨቆኑ እና ፍትህ ላጡ የኢትዮጵያ ሴቶች
No comments:
Post a Comment