ዘጋቢ፦ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)
እናትና ህጻን ልጅዋን ገድሎ የተሰወረው ሰውዬ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በፈረንሳይ ፓሪስ ክተማ የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ነበር:: ሟች ወ/ሮ ክውን ገዳሙ ትባላለች:: ከቤትዋ ወደ ስራ ቦታ ሲመላለሱ ተጠርጣሪውን የዩታል:: በጎዳናው የተጎሳቆለውን ሰው(ጉዳዩ በህግ ስለተያዘ ስሙን እዚህ ላይ አንጠቅሰውም) ስለሚያሳዝናቸው ባለፉ ባገደሙ ቁጥር እጃቸውን ይዘረጉለት ነበር::
ከግዜ በኋላ ከክረምቱ ብርድ እንዲገላገል ሲሉ ይህንን የጎዳና ተዳዳሪ ለግዜው በቤታቸው አስጠጉት:: የአቅማቸውን እየረዱት አብረው ለወራት ኖሩ::
ባለፈው ሳምንት አንድ አስደንጋጭ ክስተት በቤተሰቡ ውስጥ ተፈጸመ:: በችግሩ ያስጠጉት ሰው ከተኙበት በጭካኔ ገድሏቸው አመለጠ::
ወ/ሮ ክውን ገዳሙ የሶስት ልጆች እናት ሲሆኑ በፈረንሳይ ፓሪስ ለረጅም ግዜ ኖረዋል:: የሶስት ልጆች እናትም ናቸው:: ያለአባት ከሚያሳድጓቸውን ሶስት ልጆች ውስጥ አንደኛዋና የሁሉም ታናሽ ከሆነችው ጋር ላይመለሱ ይህችን አለም ባለፈው ሳምንት ተሰናበቱ::
ገዳዩ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በጩቤ ሰነጣትቆ ነው እናትና ልጅን ለህልፈት የዳረገው- እንደ ፈረንሳይ የዜና ምንጭ:: ባጎረሱት እጅ ተነከሱ:: ደግ ባደረጉ ምላሹ ግድያ ሆነ: ለዚያውም አረመኔያዊ ግድያ::
ነብሰ ገዳዩ ለግዜው ተሰውሯል:: የፈረንሳይ ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመሆን ጉዳዩን በጥብቅ ይዞታል:: እኛም እየተከታተልን ጉዳዩ ምን እንደደረሰ እናቀርብላችኋላን::
No comments:
Post a Comment