በደሴ ከተማ የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ስፍራው የተጓዙት የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ አቶ አዕምሮ አወቀ ድብደባና ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
ዓርብ መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡15 ላይ በደሴ ከተማ በተለምዶ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕራት በልተው ሲወጡ ታርጋ የሌለውና መስታወቱ ጥቁር በሆነ ኮብራ መኪና አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ከውጪ ሁለት ሰዎች ገፍተው ወደ መኪናው እንዳስገቡአቸው ጨምረው አስረድተዋል፡፡ በመቀጠልም አፍና አፍንጫቸው ላይ ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ፈሳሽ ነገር ከነፉባቸው በኋላ መኪናው ተዘግተው ድብደባ ፈጸመውባቸዋል፡፡
እሳቸውም ድብደባውን ሲከላከሉና የመኪናውን መስታወት ለመስበር ሲታገሉ ደብዳቢዎቹ ከኪሳቸው ውስጥ 1735 ብር፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት መታወቂያ ወስደው ከመኪናው ገፍትረው እንደጣሏቸው ገልጸውልናል፡፡
ፍኖተ ነፃነት
No comments:
Post a Comment