
የቃል አቀባይ ቢሮው ባለፈው ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአባይ ላይ እየገነባች ያለችው ግድብ በ1902 በእንግሊዝ እና በአፄ ምኒልክ የተፈረመውን የሚጥስ ነው፣ አፄ ምኒልክ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ተብለው ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ከእንግሊዝ ጋር በተፈራረሙት ውል መሰረት ከእንግሊዝ እና ሱዳን ፈቃድ ውጪ ኢትዮጵያ በአባይ፣ በጣና ሀይቅ እና በሶባት ላይ ምንም አይነት ግንባታ እንደማታደርግ እና ለመንባት የሚሞክሩ ወገኖችንም እንደምትከለክል ተስማምታለች፤
ስለዚህ የአሁኑ ግንባታ ስምምነቱን ይጥሳል ብሏል፡፡ በአለም አቀፍ ህግ የውሀ ባለሙያ የሆኑት አቶ እምሩ ታምራት ጉዳዩን አስመልክተው ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በመጀመሪያ ደረጃ ግብፅ የ1902 ስምምነት አካል ስላልሆነች፤ ይህን ስምምነት በመከራከሪያ ማንሳት አትትችልም፤ ሌላው የስምምነቱ የአማርኛ ትርጓሜ “ኢትዮጵያ ውሃውን ሙሉ በሙሉ የሚደፍን ስራ አትሰራም ይላል እንጂ ጥቅም ላይ አታውል” ብላ አልተስማማችም፡፡
አዲስ አድማስ
No comments:
Post a Comment