በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ተብሏል፡፡ ብዙ ተፅፏል፡፡ ብዙ ውይይት ተደርጓል፡፡ ብሄር ማለት ሀገር ማለት ነውና በኢትዮጲያ ውስጥ ብሄሮች አሉ የሚለውን ሀሳብ ጨምሮ ጎሳ የሚለው ቃል በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለመግለፅ አቅሙ የለውም እስከሚለው ሀሳብ ድረስ ብዙ ተብሏል፡፡ ርዕሰ ጉዳዩ ግን ብሄር እና ጎሳ የሚሉት ቃላት ላይ ተንጠልጥሎ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ቃሎቹን የተጠቀሙባቸው ሰዎች ቃሎቹን ሊያሸክሟቸው የፈለጉት ፅንሰ ሀሳብ ምንድነው የሚለውን በውል ማጤን ካልፈለግን የሰከነ ውይይት በማድረግ ፈንታ እንደ ጨበራ ተስካር ትርፉ መንጫጫት ብቻ ይሆናል፡፡ በኢትዮጲያ ውስጥ የብሄር ጥያቄ ጎልቶ መሰማት የጀመረው በ1950ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ከሜጫና ቱለማ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በወቅቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ(በቀዳማዊ ሀ/ስላሴ ዩኒቨርሲቲ) የተማሪዎች ማህበር አዘጋጅነት በብሄር መደራጀት አደጋው ምን ሊሆን ይችላል; በሚል ሀሳብ የሜጫና ቱለማ እንቅስቃሴ መሪዎች በተጋበዙበት ውይይት ይደረግ ነበር፡፡ የሜጫና ቱለማ እንቅስቃሴም ሆነ በተማሪ ማህበሩ የሚደረጉ ውይይቶች ግን በአፄው አምባገነናዊ እርምጃዎች ምክንያት እድሜ አልነበራቸውም፡፡ ቆይቶ ግን የተማሪው ማሀበር ሲጠናከር ይህ የብሄር ጥያቄ መልሶ የመወያያ አጀንዳ ሆነ፡፡ የተማሪው ማህበር ፕሬዝዳንት የነበረው ዋለልኝ መኮንንም የብሄር ጥያቄ የሚለውን ፅሁፉን ያቀረበው በዚህ ወቅት ነበር፡፡ አንዳንድ ጥራዝ ነጠቆች የብሄር ጥያቄን ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠረው ዋለልኝ መኮንን እንደሆነ አድርገው ለማቅረብ ይሞክራሉ....ለምሳሌ ያህል በፋክት መፅሄት ላይ
‹‹የዋለልኝ ልጆች›› በሚል ልጅ ልጅ የሚል ፅሁፍ ያስነበበን ልጅ ዳዊት ለዚህ ሁሉ የብሄር ፖለቲካ ጣጣ እና ጦስ የዳረገን ዋለልኝ ነው ሲል የሚያውቀውን ያህል ነግሮናል፡፡ ነገር ግን ከዋለልኝ በፊት የብሄር ጥያቄ በኢትዮጲያ ሰማይ ስር ሲነሳ ቆይቷል፡፡ የዋለልኝን ለየት የሚያደርገው በጊዜው በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ከነበረው የሶሻሊዝም ርዕዮተ-አለም አንፃር በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን የብሄር ጥያቄ ይፈታል የሚለውን ሀሳብ ርዕዮተ አለሙን አስደግፎ ማቅረቡ ብቻ ነው፡፡ ዋለልኝና ጓደኞቹ መሰረት አድርገው የተነሱት የስታሊን የብሄር ትርጓሜ እንደወረደ ይህን ይመስላል "an historically formed, stable community of people, united by community of language, of territory, of economic life, and of psychological make-up which expresses itself in community of cultre." ዋለልኝ ከላይ የቀረበው የስታሊን የብሄር ትርጓሜ በውቅቱ ከነበረው የኢትዮጲያ ሁኔታ ጋር ያዛመደበትን መንገድ ደግሞ ቀጥሎ ባለው የዋለልኝ ፅሁፍ ላይ እንመልከት፡-"What are the Ethiopian people composed of? I stress on the word peoples because sociologically speaking at this stage Ethiopia is not really one nation. It is made up of a dozen nationalities with their own languages, ways of dressing, history, social organization and territorial entity. And what else is a nation? It is not made of a people with a particular tongue, particular ways of dressing, particular history, particular social and economic organization? Then may I conclude that in Ethiopia there is the Oromo Nation, the Tigrai Nation, the Amhara Nation, the Gurage Nation, the Sidama Nation, the Wellamo [Wolayta] Nation, the Adere [Harari] Nation, and however much you may not like it the Somali Nation." በዚሁ ፅሀፉ ላይ ‹‹Start asserting your national identity and you are automatically a tribalist,›› በማለት በወቅቱ ስለ ብሄራዊ ማንነት አጥብቆ መናገር የነበረውን ፈተና ይጠቁመናል፡፡
ዋለልኝ ጨምሮ በወቅቱ ስለነበረው ስለኢትዮጲያዊ ብሄርተኛነት ስሜት ሲያብራራ
‹‹There is of course the fake Ethiopian Nationalism advanced by the ruling class and unwillingly accepted and even propagated by innocent fellow travellers. What is this fake Nationalism? Is it not simply Amhara and to a certain extent Amhara-Tigre supremacy? Ask anybody what Ethiopian culture is? Ask anybody what Ethiopian language is? Ask anybody what Ethiopian music is? Ask anybody what the "national dress" is? It is either Amhara or Amhara-Tigre!! To be a "genuine Ethiopian" one has to speak Amharic, to listen to Amharic music, to accept the Amhara-Tigre religion, Orthodox Christianity and to wear the Amhara-Tigre Shamma in international conferences. In some cases to be an "Ethiopian", you will even have to change your name. In short to be an Ethiopian, you will have to wear an Amhara mask (to use Fanon's expression).›› ይለናል፡፡
እንግዲያውስ ዋለልኝ በኢትዮጲያ ውስጥ ብዙ ብሄሮች አሉ ሲል ልክ የሆነው ምኑ ላይ ነው; የተሳሳተውስ; ኢትዮጲያዊ ብሄርተኝነት ሲባልስ እንዴት ነው የሚገለፀው???ኢትዮጲያዊ ብሄርተኛነት ከቋንቋ፣ ከባህል፣ እና ከማንነት አኳያ እንዴት ይገለፃል? ምንስ ነው? ለዋለልኝ ኢትዮጲያ የኦሮሞው የአማራው የትግሬው የጉራጌው ብሄር ስብስብ ናት......ከዚህ ውጪ የሆነች ኢትዮጲያ ወይም በአንድ ባህል እና ቋንቋ ልትወከል የምትችል ኢትዮጲያ ትኖር ይሆን? ካለችስ በየትኛው ቋንቋ ነው የምትወከለው? በየትኛው ባህል ነው የምትወከለው? የኢትዮጲያ ቋንቋ ምንድነው? የኢትዮጲያ ባህል ምንድነው??? የሶሻሊስት ርዕዮተ አለምን ሳንከተል ብሄር የሚለውን ፅነሰ ሀሳብ ብቻ መዋስስ እንዴት ይቻለነል???
ከላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልሶችችሁን በአእምሮአችሁ እያብላላችሁ ወደ ሌላኛው ፅንፍ ደግሞ ልውሰዳችሁ፡፡ ይህ ፅንፍ ኢትዮጲያዊ ብሄርተኛነትን ሲያቀነቅን በኢትዮጲያ ውስጥ የተለያዩ ጎጦች/ጎሳዎች እና ቋንቋዎች አሉ እንጂ የተለያዩ ብሄሮች የሉም ይላል፡፡ ኢትዮጲያዊ ብሄርተኛነት ከጥንት የነበረ በተለያዩ ወቅቶችና ጊዜያት ሲዳከም ሲጠናከር ኖሮን ዛሬ የደረሰ እንጂ አሁን በኛ ዘመን የተፈጠረ እንዳልሆነ ይሞግታል፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ይህን አመለካከት አጥብቆ በመደገፍ ይታወቃሉ፡፡ ኢትዮጲያ ከየት ወዴት በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ ለእርሳቸው ኢትዮጲያዊነት(ኢትዮጲያዊ ብሄርተኛነት) ምን ማለት እንደሆነ ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ
‹‹ኢትዮጲያ የሚለው መጠሪያ የፖለቲካ ስም እንጂ ከአንድ የተለየ ህብረተሰብ ወይም ቋንቋ ወይም ሀይማኖት ጋር የተቆራኘ አይደለም፡፡ ኢትዮጲያ ብዙ ቋንቋዎችን የሚነገሩ ፣ ብዙ ሀይማኖቶችን የሚከተሉ በተለያዩ የቆላና የደጋ መሬቶች ላይ የተለያየ የኑሮ መሰረት ያሉአቸው ህብረተሰቦች አገር ነች፡፡ እነዚህ ህብረተሰቦች.....እየተጋቡም እየተዋለዱም ብዙ ተዛምደዋል፡፡ የኢትዮጲያ ህብረተሰቦች ሲደባለቁና ሲዛመዱ ባህላቸውም እየተደባለቀና እየተዛመደ ሄዶ፡፡ የቤት አሰራርን ብንመለከት አብዛኛው ተመሳሳይ ነው፡፡ በምግብ በኩል እንጀራና ወጥ የማን ነው? ገንፎ የማን ነው? ቅንጨስ? ንፍሮስ? ቆጮስ? አንዳንድ ሰዎች እንዚህን የምግብ አይነቶች ለተለያዩ ህብረተሰቦች ለማደላደል እንደሚቃጣቸው ይገባኛል፡፡ ነገር ግን ቆም ብለው እንዲያስቡበትና እንዲወያዩበት ይጋበዛሉ፡፡ በልብስስ ብንሄድ እጀጠባብና ሱሪ፣ ኩታ፣ ጋቢ፣ ቡሉኮ የማን የማን ናቸው....›› በማለት አንድ የጠዛመደ እና ውሁድ ማንነት እንዳለን ይነግሩናል፡፡ ውሁዱ ማንነታችን የትኛው ነው? የትኛው አለባበስ? የትኛው ቋንቋ? የትኛው ባህል? ፕሮፌሰር መስፍን ከላይ ባነበብነው ፅሁፋቸው ላይ ጎሳ ወይም ብሄር ወይም ህዝቦች ላለማለት እጅግ በመጠንቀቅ ‹‹ህብረተሰቦች›› በሚል የተጠቀሙት ቃል ከታሪካዊውና ከነባራዊው የኢትዮጲያ ሁኔታ ጋር ይሄዳል ወይ???
ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች የምንመልሰቸው መልሶች እንደያዝነው ቅድመ-እሳቤ (pre-supposition) ይወሰናል.........እኔ ግን እውነታው በሁለቱ ፅንፎች መሀል የሆነ ቦታ ላይ ያለ ይመስለኛል!!!......................ማርታ ተስፋዬ
No comments:
Post a Comment