
ከተማዋ መረጋጋት ቢታይባትም፣ ተመሳሳይ ችግር ሊከሰት ይችላል የሚል ፍርሃት መኖሩን ለማወቅ ተችሎአል። መጋቢት5 እና 6 ቀን 2006 ዓም በሁለተኛ ደረጃ እና በመሰናዶ ትምህርት ቤቶች መካከል ጎሳን ማእከል ያደረገ ብጥብጥ ተከስቶ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ የብዙ ነጋዴዎች ህንጻዎችም መስታውቶቻቸው ተሰባብሯል። ሃሙስ መጋቢት 6 በዋለው የከተማው ታላቅ ገበያ ላይ በተፈጠረ ሁከት በሚሊዮን የሚቆጠር ሀብት መውደሙን ነዋሪዎች ይናገራሉ። አንዲት ነዋሪ በጽኑ ቆስላ ህክምና ተደርጎላት መመለሱዋን እና በግጭቱ የሞተ ሰው አለመኖሩን ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋሉ 12 ሰዎች አለመፈታታቸውም ታውቋል።
No comments:
Post a Comment