በመሆኑም ፓርቲያችን የክልሉ መንግስት ትክክለኛው የቃጠሎ መንስኤ በአስቸኳይ ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ በማንኛውም ምክንያትኃላፊነታቸውን በብቃት ያልተወጡ የመንግስት ኃላፊዎች በግልፅ ለተጠያቂነት እንዲቀርቡ፤ የክልሉ ፖሊስ በህዝቡ ላይ የወሰደው የኃይል እርምጃ በገለልተኛአካል ተጣርቶ ይፋ እንዲደረግ፤ የክልሉ ፖሊስ በወሰደው የኃይል እርምጃ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ብዛትና የጉዳቱ መጠን በአስቸኳይ ለህዝብ ይፋእንዲደረግ ተገቢ ህክምና እና ካሳ እንዲከፈላቸው፤ ይህንን የፈጸሙ አካላትም ለፍርድ እንዲቀርቡ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡
በአንድነት ፓርቲ በኩል ይህንኑ በህዝብ ላይ የደረሰ ጉዳት ለማጣራትና ለመከታተል በስራ አስፈጻሚው አስቸኳይ ግብረ ኃይል ተቋቁሟል፡፡ ግብረ ኃይሉ ወደቦታው በማቅናት ጉዳዩን ካጣራ በኋላ የደረሰበትን መረጃ እና በፓርቲያችን የሚወስደውን ተጨማሪ አቋም በተመለከተ በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር
መጋቢት 4 ቀን 2006 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment