ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም :-ግጭቱ የተከሰተው ባለፈው ሳምንት ሲሆን፣ ለግጭቱ መነሻ የሆነውም ኮንሶዎች ባጋጠማቸው የመሬት እጥረት ሳቢያ ወደ ቦዲዮች አካባቢ ሄደው በመስፈራቸው መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ይገልጻሉ።
በግጭቱ ከሁለቱም ወገኖች 4 ሰዎች ሲሞቱ፣ 3 ኮንሶዎች እና አንድ ፖሊስ ቆስለዋል። 72 ቤቶችም እንዲሁ ተቃጥለዋል።..........................
ከዚህ በፊት ሁለቱ ብሄረሰቦች በተደጋጋሚ ሲጋጩ ቆይተዋል። ቀደም ሲል መንግስት የኮንሶ ሰፋሪዎችን ወደ ቦዴ አካባቢ በመውሰድ ማስፈሩ በአካባቢው ለሚታየው ችግር መንስኤ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአሁኑ ጊዜ የፌደራል ፖሊስ ገብቶ አካባቢውን ተቆጣጥሮታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጅንካ መብራት ለረጅም ጊዜ በመቋረጡ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧል። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት በአራት ቀናት አንድ ጊዜ የሚመጣው መብራት፣ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ዳርጓቸዋል።
No comments:
Post a Comment