1. የአድዋ ድል በአልን በተመለከተ ከአረና ፓርቲ ጋር በአድዋ ለማክበር ጥያቄው ለፓርቲው እንዲቀርብ ወሰነ፡፡ በአድስ አበባ ከትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ፣ መኢአድ፣ መድረክና ለሌሎች ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር ለማክበር ከወዲሁ የጋራ ኮሚቴ እንዲቋቋም እና ለፓርቲዎቹ በደብዳቤ ጥሪ እንዲያቀርብ ወሰነ፡፡
2. በመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ላይ በጠበቃ ተማም አባቡልጉ በኩል ፓርቲው የመሰረተው ክስ ለህዝብ ይፋ እንደረግ ወሰነ፡፡.........
3. የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ቁጥር ሁለት ፕሮጀክትን በመመርመር አፅድቆ ወደ ምክርቤቱ መራው፡፡
4. በብአዴን/ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር በአቶ ዓለምነው መኮንን ተፈጸመ የተባለውን ድርጊት ለመቃወም በባሕር ዳር ከተማ ህዝባዊ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ በተጨማሪም በነገው እለት ከጥር 27 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ የብአዴኑን ከፍተኛ አመራር ድርጊት በመቃወም ግለሰቡ በአስቸኳይ ከፓርቲና ከመንግስት ኃላፊነቱ እንዲነሳ፤ እንዲሁም ለፍርድ እንዲቀርብ ለመጠየቅ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያሉ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሳተፉበት “online” የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ስርዓቱ በይፋ እንዲጀመር የወሰነ ሲሆን ገፁ በፓርቲው ልሳን እና በሌሎች ማህበራዊ ገፆች ከማለዳ ጀምሮ ይተዋወቃል፡፡
No comments:
Post a Comment