BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!
Wednesday, 5 February 2014
የወያኔን ከፋፍለህ ግዛ የፍጅት ፖለቲካ ለማደባየት ጠንካራ የሆነ ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል !
እኛ ኢትዮጵያውያን የዚያ ብሔር ወይም የዚያ ጎሣ አባል ሆነን የተፈጠርነው የሆነ ቅጽ ሞልተን ወይም ዕጣ ተጣጥለን አይደለም፡፡ ተፈጥሮ ነው፡፡ በባለጠበንጆቹ ወያኔዎች የተነጠቅነውን መብትና ግዴታን በማስከበር፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የምንችለው ግን እንደ ብሔር ወይም ብሔረሰብ አባል ብቻ ታስረንና ጠበን ሳይሆን፣ እንደ አንድ አገርና ሕዝብ በጋራ ስንቆምና እጅ ለእጅ ስንያያዝ ነው፡፡...............
ኢትዮጵያዊነት እንዳያብብ የሃገር መልካም ታሪክ እንዳይወራ ጠንክረው የሚሰሩት ወያኔዎችን የማሳፈር እቅዳቸውን የማደባየት ግዴታው የኛ የኢትዮጵያውያን ነው:: የዓለም፣ የአኅጉራዊና የአገራዊ ፈተናው እየከበደ በሄደ ቁጥር የኢትዮጵያዊነት መለኪያና የጥንካሬው ማረ
ጋገጫ እየጨመረና እየከበደም መጥቷል፡፡ እስካሁን ድረስ ያለው ኢትዮጵያዊነታችን ጠንካራ አይደለም ወይ? የሚል ጥያቄ ሊነሳና አነጋጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ በግልጽ እንነጋገር ከተባለ ግን ኢትዮጵያዊነታችን ደካማ ነው አንልም እንጂ፣ ካለው የኢትዮጵያዊነት ስሜት በላይ እጥፍ ድርብ ጠንካራ የሆነ ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል ብለን ግን በድፍረትና በእምነት እንናገራለን፡፡
አንድነት እና ጥንካሬ በዜጎች መሃል እንዳይሰርጽ በወያኔ የሚሰራውን ደባ የማክሸፍ ሃገራዊ ግዴታ አለብን:: ኢትዮጵያዊ ሚናችንን በአግባቡ ለመወጣት እንኳ ጠንካራ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል፡፡ ይህ ጠንካራ ኢትየጵያዊነት ነው ሚና እንድንጫወት ዋስትና የሚሆነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የዚያ ብሔር ወይም የዚያ ጎሣ አባል ሆነን የተፈጠርነው የሆነ ቅጽ ሞልተን ወይም ዕጣ ተጣጥለን አይደለም፡፡ ተፈጥሮ ነው፡፡ ይህ እንዳለ ተቀብለን የብሔራችንን ባህልና ቋንቋ እናከብራለን፤ እናሳድጋለን፤ ይህንን ማድረግ ማንንም አይጐዳም፡፡ ሁላችንን ግን ይጠቅማል፡፡ ይህን እያከናወንን ግን ከድህነት በመላቀቅ፣ በመበልፀግ፣ ሰላምና መረጋጋትን እውን በማድረግ፣ መብትና ግዴታን በማስከበር፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የምንችለው ግን እንደ ብሔር ወይም ብሔረሰብ አባል ብቻ ታስረንና ጠበን ሳይሆን፣ እንደ አንድ አገርና ሕዝብ በጋራ ስንቆምና እጅ ለእጅ ስንያያዝ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ መንገድ ወይም አማራጭ የለም፡፡
#
Miniliksalsawi
No comments:
Post a Comment
Newer Post
Older Post
Home
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment