BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 4 February 2014

ኢትዮጵያን ለማዳን ወቅቱ አሁን ነው!!! የተከበሩ አቶ ልዑል ቀስቅስ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ሊቀመንበር



1528716_385228011613166_627076728_n
አቶ ልዑል ቀስቅስ አስታጥቄ በጎንደር ከተማ ተወልደው የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጎንደር ከተማ ውስጥ በሚገኘው ፃድቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአፄ ፋሲለደስ መለስተኛ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል፡፡
ከዚያም የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት በመቀላቀል ሁርሶ መኮንኖች ማሰልጠኛ በመግባት የሁለት አመት ወታደራዊ አካዳሚ ትምህርታቸውን ጨርሰው በመቶ አለቅነት ማዕረግ ተመርቀዋል፡፡
በመቀጠልም ኤርትራ ውስጥ በነበረው 2ኛው አብዮታዊ ሰራዊት ተመድበው በሻለቃ አዛዥነት እንዲሁም በዘርያድረስ 27ኛ መካናይዝድ ብርጌድ አመራር በመሆን በርካታ እልህ አስጨራሽ ውጊያዎችን አድርገዋል፡፡ ለሀገራቸው ከፍተኛ መስወዓትነት ከፍለዋል፡፡.........

ከዚህ በተጨማሪ በህግ ትምህርት በዲፕሎም ተመርቀዋል በማዕከላዊ እስታስቲክስ መስርያ ቤት ተቀጥረው ለ11 ዓመት ሰርተዋል፡፡ ከዚያም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል በማለት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላም እና ዴሞክራሲ ለማምጣት በተቋቋሙት የሰላም ታጋይ ድርጅቶች ውስጥ በመግባት ቅንጅትን ቅንጅት ካደረጉት ግንባር ቀደም የሀገራችን ውድ ልጆች መካከል አንዱ ሆኑ ፡፡ በቡዙዎች የሀገራችን ሕዝቦች ዘንድ ታላቅ ተስፋን ሰጥቶ በነበረው ሆኖም በወያኔ ቡድን በተጨናገፈው የ1997 ዓ.ምረቱ ሀገራዊ ምርጫ በጎንደር ከተማ ቅንጅትን በመወከል ተወዳድረውና ሰፊ የህዝብ ድጋፍ አግኝተው የኢትዮጵያ የፓርላማ አባል በመሆን ለተወሰነ ጊዜ አማራጭ ሲጠፋ ገብተው ለተወሰነ ጊዜ እንደቆዩ ፓርላማው የወያኔ ፓርላማ እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደማይወክል ተረድተው እና የተገነዘቡትንም ችግር ለሪፖርተር ጋዜጣ መግለጫ ሰጥተው ፓርላማውን ትተው በረሀ ገቡ፡፡
አንባገነኖችን በትጥቅ ትግል ካልሆነ በስተቀር በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አምነው ስልጣናቸውን ለህዝብ እንደማያስረክቡ ያረጋገጡት አቶ ልዕል በወቅቱ ኤርትራ ውስጥ ይገኝ የነበረውን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተቀላቀሉ፡፡ ለ10 ወራትም የትጥቅ ትግል ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
ወደውጭ በመውጣት በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በማቀናጀት እና በማደራጀት ቢሰሩ ይበልጥ ውጤታማ ሊሆኑ እና ለድርጅቱም ከፍተኛ ጥቅም መሆኑን የተገነዘበው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ወደ ውጭ እንዲወጡ አደረገ፡፡ ላለፉት 3 ዓመታትም በውጭ ሀገር የግንባሩ ተወካይና የአለም አቀፍ ኮሚቴው ሊቀመንበር በመሆን የሚጠበቅባቸውን ከፍተኛ ተግባር በብቃት እየተወጡ ቆይተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ
ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ (EPPFG) ሊቀመንበር ናቸው፡፡
በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና በድርጅቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ ማብራሪያ በመስጠት ከድርጅቱ መጽሔት ጋር አጨር ቆይታ አድርገዋል፡፡ መልካም ንባብ
ጎህ፡- የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ከሁለት ዓመት በፊት የደርጅቱን ፕሮግራም እና ህገ ደንቡን በማሻሻል እንዲሁም ከ6
ዓመት በፊት ተመስርቶ ወያኔን ያንቀጠቀጠውን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ዘብ ጋር በመዋሀድ በአንድ መጠሪያ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በሚል ትግሉን በማካሔድ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የተደረገበት ምክን ት ምንድነው ከሚለው ብንጀምርስ?
አቶ ልዑል፡- ድርጅቱ ከበፊቱ ሥያሜው የተለየ ብዙም ነገር የለውም፡፡ ሆኖም ለፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ መጠናከር ሲባል እንዲሁም አጠቃላይ ለድርጅቱ አደጋ የሆኑ ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል ሲባል የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ (EPPFG) የሚል ስያሜ የውህደት ሥያሜ ተሰጥቶታል፡፡
በአጠቃላይ የውጭና የአገር ውስጥ የድርጅቱን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ሲባል ይህም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች ቀደም ብለው እንዲወያዩበት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም የሁሉንም አባላት ድጋፍ አግኝቶ ከፍተኛ አመራሩ ባደረገው የመጨረሻ ሥብሰባ ውሳኔ ተሰቶበት ፀድቋል፡፡
ጎህ፡-በአሁኑ ሰዓት የድርጅቱ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?
አቶ ልዑል፡- ከላይ እንደጠቀስኩት ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት ጠንካራ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ በአገር ውስጥ በሁሉም የሀገራችን ክልሎች በየስፍራው በመግባት ለውጥ ፈላጊውን ህብረተሰብ እያገዘና እያሳተፈ በህዕቡና በግልፅ እየተንቀሳቀሰ አምባገነኖችን እየታገለ ይገኛል፡፡ የድርጅት አባላትንና ደጋፊዎችን ለማሥፋት በተደረገው የተጠናከረ እንቅስቃሴ በአሁኑ ወቅት የአገር ውስጥ አባላትና ደጋፊዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ ሲሆን
ይህም ድርጅቱ ምን ያህል ለህዝብ ጠቃሚ አጀንዳ ያለው መሆኑ ህብረተሰቡ መረዳቱን ያመላክታል፡፡ በውጭ አገርም ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በውጭ አገር የሚኖረው ዲያስፖራ ያገሩ ጉዳይ ይመለከተዋል፡፡ ተገቢም ነው፡፡ ሆኖም በጋራ ሆኖ ትግሉን ለማካሄድ ጠንካራ ድርጅት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም የኛ ድርጅት ለውጥ ፈላጊውን በውጭ አገር የሚገኝ የኢትዮጵያ ህዝብ በማሰባሰብ ድጅታዊ ድጋፍ የመሥጠት ሚናውን እየተወጣ ነው የሚገኛው፡፡ ለዚህም በየጊዜው እየጨመረ የመጣው አባላት ቁጥር አንድ ማሳያ ነው፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ድርጅት መሆኑን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖረው ህዝብ ይበልጥ የተገነዘበበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
ጎህ፡- ወያኔን ከሚታገሉ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ያላችሁ ግንኙነትስ ምን ይመስላል?
አቶ ልዑል፡- አላማችንና አጀንዳችን አንድ ነው፡፡ ይህም አምባገነኑን የወያኔ ቡድን ማሥወገድ ነው፡፡ እናም በጋራ እየተወያየን እየሰራን እንገኛለን፡፡ በያለንበት የፖለቲካ ድርጅት ለህዝብ የሚጠቅም ሥራ እያከናወንን እንገኛለን፡፡ ትግሉን ፊሬአማ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን አንዳንድ ጠጠር እንዲወረውር እንጠይቃለን፡፡ „ወይ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ“የሚለው የህዝባችን ወቅታዊ መፈክር ትክክል መሆኑን ተረድተን ከመጠላለፍና ከመዘላለፍ እንዲሁም ጎራ ለይቶ
ከመፋለም ይልቅ እየተነጋገሩ የወያኔን ሥርዓት ግባ ከመሬት ለማፍጠን አማራጭ የሌለው ጥያቄ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ እንድንሰራ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ያለብንን ክፍተቶች ለመድፈን እና አብሮ ለመስራት በተለይ በአመራር ደረጃ ላይ ያለን እየተገናኘን እየተወያየን እንገኛለን፡፡ በተለይ በአሁን ሰዓት በቅርብ በተመሰረተውና በውስጡ በርካታ ድርጅቶችን ባቀፈው ሸንጎ ጋር በጋራ ለመሥራት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ እንገኛለን፡፡ ባለፈው መጋቢት 1/2013
ፍራንክፈርት ውስጥ በተካሄደው ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ ሸንጎ የበኩሉን የድጋፍ መልዕክት መላኩ በሀገራችን ጉዳይ በመተሳሰብና በጋራ ለመሥራት ያለውን መልካም ጅምር የሚያመላክት ነው፡፡ በአቶ ጥአሁን ገላው የሚመራው ድርጅት ጋርም በጋራ እየሰራን እንገኛለን፡፡
ጎህ፡- በአሁኑ ሰዓት ያለውን የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እንዴት ይመለከቱታል?
አቶ ልዑል፡- የአሁኑ የወያኔ ሥራ አዲስ አይደለም፡፡ የቆየ ደብቅ አላማው ነው፡፡ እንደምንታዘበው ዘር በማጥፋትና የውጭ ሃይሎች ሎሌ በመሆን አገራችንን እያተራመሰ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ከአንድ ዓመት በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግፍ እናስታውሳለን፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በቤኒሻንጉል ጉምዝ አካባቢ የሚገኙ አማራዎች የአይናችሁ ቀለም አላማረኝም በሚል እያፈናቀለ ሜዳ ላይ እየጣላቸው ይገኛል፡፡ ይህም ድብቅ የቆየ የህዘብ
ጠላትነቱን ያሳየ ተግባር ነው፡፡ ሌላው በሃይማኖት ላይ የሚያካሄደው የሀገር ማጥፋት ዘመቻ ነው፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ዛሬ እየደረሰበት የሚገኘው ግፍና በደልም መግለፅ ከሚቻለው በላይ ነው፡፡ እንዲሁም በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ እየደረሰ ያለው ተግባር የወያኔን እኩይ ተግባር ያረጋገጠ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ወያኔ ሃይማኖታዊው ሥርዓት በማይፈቅደው መንገድ የራሱን ፖለቲካ ጳጳስ በመሾም ለ22 ዓመት ሃይመኖትን ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት ሲያተራምስ ቆይቷል፡፡ ዛሬም እንዲሁ ከዚህ ተግባሩ አልወጣም፡፡ የምዕመኑን ድምፅ በማፈን ፖለቲከኛ ጳጳስ ሾሟል፡፡ ይህም የሚያመለክተው ሀገር አፍራሽ ወሮበላ ቡድን መሆኑን ነው፡፡
ጎህ፡- አቶ ልዑል ይህ ሁሉ ተባለ፡፡ እንዲያው እስካሁን ባሳለፉት የትግል ጉዞና ተሞክሮ በመነሳት የወያኔን ቡድን እንዴት ይገልፁታል?
አቶ ልዑል፡- በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ ወያኔ በመሰረቱ አመሰራረቱ ሻዕብያ በትከሻው ተሸክሞ ከሳህል በረሃ ደደቢት አምጥቶት ያገባው የሻዕብያ ተላላኪ ቡድን ነው፡፡ ተላላኪነቱን ያመለከተውም እንደምታሥታውሱት ሻዕብያና ወያኔ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠሩ ሻዕብያ ለሰባት አመት ኢትዮጵያን እንዲዘርፍ የፈቀደለት ራሱ ወያኔ መሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል አንድ እግር የቡና ተክል የሌላት ክፍለ ሀገር የኢትዮጵያን ቡና በወያኔ ተባባሪነት በመዝረፍ ሜድ ኢን ኤርትራ እያለች ለውጭ ኤክስፖርት ታደርግ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡
ጎህ፡- ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ሶስት የባህር በሮች ነበሯት፡፡ በአሁን ሰዓት ከሶስቱም የባህር በሮች አንድ እንኳ የላትም ይህን ጉዳይ ድርጅታችሁ እንዴት ያየዋል? ወደፊትስ አገሪቱ የባህር በር እንዲኖራት ምን መደረግ አለበት ብሎ ያምናል?
አቶ ልዑል፡- አሁንም ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሶስት ወደቦች እንደነበራት ግልፅ ነው፡፡ ጅቡቲ፣ አሰብና ምፅዋ ሶስቱ የባህር በሮቻችን ነበሩ፡፡ የጅቡቲ ጉዳይ አፄ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን ለማሳደግ ከነበራቸው ከፍተኛ ዕራይ የተነሳ የተፈፀመ ጉዳይ ነው፡፡ የአሰብና የምፅዋ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ የኛ ድንበር ቀይባህር ነው፡፡ ኤርትራ በወያኔና ሻብያ ህገ ወጥ ፈቃድ ብቻ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ፍላጎት ሳይኖርበት የተፈፀመ ህገ ወጥ ሥራ ነው፡፡ ያም ቢሆን አሰብ በሰሜን ምስርቅ ኢትዮጵያ የሚገኝ የሀገራችን ክፍል ነው፡፡ እንጂ የኤርትራ አካል አይደለም፡፡ ይህንንም ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አሰብ የኢትዮጵያ ወደብ ነች፡፡ የሚያሻማ ጉዳይ አይደለም፡፡ ወደፊት በኢትዮጵያ ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ሲመሰረት ኢትዮጵያ ህጋዊ በሆነ መንገድ አሰብን የማስመለስ ህጋዊ መብት አላት፡፡ ምንም ይሁን ምን የሁለቱ ሀገር ህዝቦች ወንድማማቾች ናቸው የሚጣሉት ሁለቱ የወሮበላ ቡድኖች ናቸው፡፡
ጎህ፡- በመጨረሻም የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለዎት?
አቶ ልዑል፡- „ወይ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ“ የሚለው የህዝባችን ወቅታዊ መፈክር ትክክል መሆኑን ተረድተን ከመጠላለፍና ከመዘላለፍ እንዲሁም ጎራ ለይቶ ከመፋለም ይልቅ እየተነጋገሩ የወያኔን ሥርዓት ግባ ከመሬት ለማፍጠን አማራጭ የሌለው ጥያቄ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ እንድንሰራ ጥሪያችንን
እናስተላልፋለን፡፡
ጎህ፡- ለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን፡፡
አቶ ልዑል፡- እኔም አመሰግናለሁ፡
ከጎህ መፅሔት ኤፕሪል 2013 ዓ.ም አንደኛ አመት ቁጥር 2 የተወሰደ

No comments:

Post a Comment