By Minilik Salsawi
ባለፈው ሳምንት በወያኔ ከታፈኑት የኦብነግ አባላት ጋር በተያያዘ ሁለት የኬንያ የፖሊስ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ዋሉ::በኬንያ መንግስት ለሰላም ድርድር በሚል የተጋበዙት የኦብነግ አመራሮች እስካሁን የት እንዳሉ አይታወቅም:: ምንሊክ ሳልሳዊ በናይሮቢ ኧፐር ሂል በሚገኘው አረቢያን ኮዚን ታዋቂ ሬስቶራንት ደጃፍ ላይ ባለፈው ሳምንት በደህንነት ሃይሎች ከታፈኑት ለድርድር ወደ ኬንያ የመጡት የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ኦብነግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ሁለት የኬንያ ከፍተኛ የፖለኢስ መኮንኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኬንያ ጋዜጦች ዘገቡ:: አንድ ከፍተኛ ኢንስፔክተር እና ሌላ ኮንስታብል ለኢትዮጵያ የደህንነት እና ስለላ ቡድን በመላላክ እና በመስራት እንዲሁም በመሰለል የሚል የክህደት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል::.............
የፖሊስ መኮንኖቹ ዛሬ ሰኞ ተይዘው ወዲያው ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው የተነበበላቸው ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘም የሰዎቹን መታፈን ተከትሎ ሌላ ወንጀሎችን እንደሰሩ የሚገልጽ መረጃዎች እና ማስረጃዎች እንደተገኙባቸው ታውቋል:: ለሶስተኛ ዙር ድርድር ወደ ናይሮቢ ለመጡት የኦብነግ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ለአቶ ሱሉብ አህመድ እና ለአቶ አሊ ሁሴን በጥር 26 2014 መታፈን እጃቸው እንዳለበት እና በዚህ የስለላ ተግባር ላይ እንደተሳተፉ እና ከሬስትራንቱ ደጃፍ አፍነው አሳልፈው እንደሰጡም የሚያረጋግጥ ማስረጃ ተገኝቶባቸዋል:: እነዚህ የፖለኢስ መኮንኖች ከአዲስ አበባ ለመጡ የስለላ ሰራተኞች ታፋኞቹን አሳልፈው የሰጡ እና የታፈኑት አመራሮችን የት እንዳሉ እንደማይታውቅ ተረጋግጧል::
የኦብነግ አመራሮች ከጽ/ቤታቸው እንደተናገሩት አባሎቻቸውን ለማፈን የኢትዮጵያ እና የኬንያ የጸጥታ ሰራተኞች እንደተንቀሳቀሱ እና በምሽትም አሳልፈው እንደሰጧቸው ተናግረዋል::ወደ ሬስቶራንቱ ምሳ ከጋበዟቸው በኋላ በሶስት መኪና ሲከታተሏቸው እንደነበረ እና ከሶስቱ አንደኛው መኪና ጥቁር ቶዮታ ፕራዶ በተከታዩ ቀን በፖሊስ ጣቢያው በቱርቢ ፖሊስ ጣቢያ እንደነበር ሁለቱ ግን ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ አመራሮቹ በማስረጃነት ተናግረዋል::በኬንያ መንግስት ለሰላም ድርድር በሚል የተጋበዙት የኦብነግ አመራሮች እስካሁን የት እንዳሉ የማይታወቅ አክለው ገልጸዋል::
በኬንያ መንግስት በኩል ከ2012 ጀምሮ የኢትዮጵያን መንግስት እና ኦብነግን ለማደራደር ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የተጀመረ እንደነበር አንዳንድ ወገኖች ይገልጻሉ ::ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የኦብነግ አባል ከናይሮቢ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም እንደዚህ አይነት ክስተቶች በተደጋጋሚ እየተከሰቱ ነው ያሉት የኦብነግ አመራሮች የኬንያ መንግስት ይህንን ጉዳይ ሊያጣራ እና እርምጃ ሊወስድ ለደህንነታችንም ዋስትና ሊሰጠን ይገባል ብለዋል:: ኦብነግ የኢትዮጵያ ሶማሊዎችን ይዞ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የሚዋጋ ድርጅት ነው:: #minilikSalsawi
No comments:
Post a Comment