BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Saturday, 15 February 2014

የጠ/ሚ ሃ/ማርያም ደሳለኝ ቆይታ ከልማታውያን ጋዜጠኞች


ሁላችን እንደ ተከታተልነው 04/06/06 ዓ/ም ከሁለት ሰዓት ዜና በኃላ ጠ/ሚ ሃ/ማርያም ደሳለኝ እነዚህ ኣብዛኛዎቻቸው ልማታውያን ጋዜጠኞች ጠርተው የቼዝ ጭዋታ (chess play) በማካሄድ ሰዓታቸውን ኣሳልፈዋል፡፡ በዛ ጭዋታ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ኣብዛኛዎቻቸው ልማታውያን ስለነበሩ ሲያቀርብላቸው የነበሩ ጥያቄዎችም ልማታውያን ናቸው፡፡ ነገር ግን ኣንድ ሁለት የሚሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በተለይ ስለ መብራት ማቋረጥ፣ ወሃ እጥረት፣ የሞባይል ኔትወርክ ችግር፣ ስለነጋዴዎች ስጋት፣ ስለኢኮኖሚያዊ ሁኔታና ስለሚቀጥለው ምርጫ ዝግጅት — ወዘተ መጠየቃቸውና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ኣራባና ቆቦ የሆነ መልስ እንደ ተሰጣቸው ጆራችን ሰምተዋል፡፡

ስለሚቀጥለው ምርጫ የተነሳ ጥያቄ ሲመልሱ
ተቋዋሚ ፓርቲዎች በሚቀጥለው ምርጫ ወደ ፓርላማ እንዲመለሱ ምን የታሰበ ነገር ኣለ? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ “የሚወዳደር ኣካል ራሱ ኣዘጋጅቶ መቆየት ኣለበት ካልሆነ በኢህኣዴግ ለተቋዋሚ ፓርቲዎች የሚሰጥ ትሩፋት ኣይኖርም” የሚል አስገራሚ መልስ ሰጥተዋል፡፡
ጥያቄው ግልፅና የማያሻማ ነበር፡፡ የጋዜጠኛዋ ጥያቄ ኣሁን ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ (በጣም ጦቦ) ወይ ደግሞ ኢህኣዴግ በራሱ ልክ የሰፋው የፖለቲካ ምህዳር ትንሽ ይሻሻል ወይም ቀዳዳ ይፈጠርለት ይሆን? እንዲሁም ተቋዋሚዎች በሄዱበት ሁሉ እየተከታተሉ ማዋከብና በፈጠራ ክስ ማሰርና ማስፈራራት ይቀንስ ይሆን ማለ~ ነው እንጂ በምርጫ ጊዜ በየትም ሃገር በገዢ ባርቲ ለተቋዋሚ ፓርቲዎች እንደ ዳቦ የሚከፋፈል ትሩፋት ወይ የፓርላማ ወንበር እንደሌለና ሊኖርም እንደማይችል ጠፍቶባት ኣይደለም ጥያቄው ያቀረበችላቸው፡፡
“የሚወዳደር ፓርቲ ራሱ ኣዘጋጅቶ መቆየት ኣለባት” ብሎዋል ጠ/ሚ ሃ/ማርያም፡፡ ጥሩ ኣባባል ነው፡፡ ነገር ግን በምን መልኩ መዘጋጀት እነደሚችሉ ቢነግ[ቸው ጥሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም፡
1/ ተቋዋሚ ፓርቲዎች ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ተጠቅመው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጡ በእርስዎና የእርስዎ ተከታዮች በተከለከሉበት ወቅት (ለምሳሌ ያኣንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ኣመራሮችና ኣባላት በክልሎችና በተለይ በኣዲስ ኣበባ ይህንን በመሞኮራቸው ስንቴ ታስረዋል ስንቴ ተደበድበዋል)፡
2/ ህዝብ በመሰብሰብ ኣላመቸውን ለማስተዋወቅ ፍቃድና መሰብሰብያ ኣዳራሽ ለጠየቁ ፓርቲዎች በእርስዎና በእርስዎ ተከታዮች ኣንዴ የሚጠብቅ የፖሊስ ሃይል የለንም በማለት ኣንዴ ደግሞ ስራችን እያስፈታችሁን ነው በሚል ተልካሻና ኣስገራሚ ምክንያት በሚከለከሉበትና በሚታሰሩበት ይባስ ብሎም 5 ኪሎ ስንዴና ኣንድ ሌትር ዘይት ከቀበሌ በሚሰጣቸው ኑሮዋቸው በሚገፉ በኣንድ ለ5 ኔትወርክ ያታቀፉ የቀበሌ ሴቶችና ምንም ያማያውቁ ከእድሜ በታች የሆኑ ልጆች ሰብስባችሁ እንሰዲሰድብዋቸውና እንዲደበድብዋቸው እያደረጋችሁ ባላችሁበት ጊዜ (ለምሳሌ የዓረና ፓርቲ አመራሮችና ኣባላት በታህሳስና በጥሪ ወር በሽሬ፣ በዓዲ ግራትና በሑመራ) ፈሪውን ህ.ወ.ሓ.ት/ኢህኣዴግ ያደረገውን ኣፈና፡
3/ በሃገራችን ፖለቲካ ላቅ ያለ እውቀት ያላቸውና ለፖለቲካዊ ለውጥ ቆራጥ ኣቋም ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በፈጠራ ክስ የፈረዳችሁባቸውና እያስፈራራችሁባቸው ባላችሁበት ጊዜ (ለምሳሌ በዚህ ሳምንት ያአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑ ኣቶ አስራት ጣሴና ወጣት ደራሲና ፖለቲከኛ ዳንኤል ተፈራ)፡
4/ የተቋዋሚ ፓርቲ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው በምክንያት እንዲባረሩና እንዲዋከቡ እያደረጋችሁ ባላችሁበት ጊዜ፡
5/ የሃገሪቱን መገናኛ ብዙሃን 24 ሰዓት በቁጥጥራችሁ ውስጥ ኣስገብታችሁ ለግለ ሰብና ለፓርቲዎች ስም ማጥፋት ዘመቻ በምታወልበት ሃገር፡
6/ ዜጎች የፈለጉትን ሃሳብ እንዳይገልፁና የፈለጉትን የፖለቲካ አቋም እንዳይኖራቸው በ1 ለ5 የስለላ ኔትወርክ ሰርታችሁ ነፃነቱ በነጠቃችሁት ህዝብ በአጠቃላይ መንግስት የመንግስት ስራ ትቶ የፓርቲ ስራ በሚሰራበትና መንግስት መንግስትነቱን ትቶ የተራ ሽፍታ ስራ በሚሰራበት ጊዜ እንዴት ኣድርገው ነው ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ራሳቸው ለውድድር መዘጋጀት የሚችሉት?
ሌላው ጠ/ሚ ደጋግመው ሲሉት የነበረ ጉዳይ ስለ ምርጫ ሂደት ነው፡፡ “ምርጫው ልክ እንደ ቅድሙ ሁሉ ነፃ፣ ፍትሓዊ፣ ዲሞክራስያዊና በህዝቡ ላይ ተአማኒነት ያለው እንዲሆን እንደ መንግስት በቂ ዝግጅት እናደርጋለን” የሚል ኣስገራሚ ኣባባል ነበር፡፡
መቼ ነው ኢህኣዴጎች ከረጆ ከመስረቅ (ከመቀየር)፣ የተቋዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎ ኣስፈራርቶ ከማባረር፣ ህዝብ በነፃነት እንዳይመርጥ ከማስፈራራትና ከመደለል እንዲሁም ከማደናገር ኣልፋችሁ ነፃ፣ ፍትሓዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሄዳችሁት? መቼ ነው በህዝብ ላይ ተኣማኒነት ያተረፈ ምርጫ ከንግግር ኣልፎ በተግባር የተደረገው?
በ1997 ዓ/ም ኣንፈልጋችሁም ብሎ ድምፁ ለነፈጋችሁ የኣዲስ ኣበባ ህዝብ ጥይት ያጎረሳችሁት ረስታችሁታል ማለት ነው? የወጋ ቢረሳ የተወጋ ኣይረሳምና ጠ/ሚ ሃ/ማርያም በኣጠቃላይ ኢህኣዴጎች የምትናገሩትና የምትሰሩት ፍፁም ስለማይገናኝ ይህ ኣይነት ቁማር በመጨረሻ ላይ ለናንተም ጠቃሚ ስላልደለ የኢትዮጵያ ህዝብ ህገ-መንግስታዊ መብቱ ተጠቅሞ የፈለገውን ሃሳብ በነፃነት እንዲያራምድ፣ እንዲሰበሰብና ኣቋሙ በሰላማዊ ሰልፍ እንዲገልፅ ብትፈቅዱለት ጥሩ ነው፡፡ ካልሆነ ህዝብ ኣፍነህ ለመግዛት መመኮር የቱንዝያ፣ የግብፅና የሊቭያ የቀድሞ ዲክታተር መሪዎች መጨረሻ ላይ እንዳላማረባቸው ከዚህ ይማረን እያላችሁ ስትከታተሉት የነበረ የትናንት ሓቅ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ትእግስተኛና ኣስተዋይ በመሆኑ እስካሁን ትእግስቱ ኣማጥጦ በመጠቀም የታገሰ ነው ያለው፡፡ ነገር ግን ትእግስት መጠን ኣለው፡፡ ስለዚ ትናንት ነገ ስለማይሆ ትእግስቱ ተማጥጦ እንዲያልቅ ባትገፋፉት ጥሩ ይመስለኛል፡፡
በሃይል ለመግዛት መሞከር የውድቀት ምልክት ነው!! Abiyu Getachew

No comments:

Post a Comment