BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Thursday, 13 February 2014

በኢሳት ጋዜጠኞች ኮምፒዩተሮች ላይ የሚካሄደው ስለላ እንደቀጠለ ነው

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በጋዜጠኛ መሳይ መኮንንና የኢሳት የኮምፒዩተር ባለሙያ በሆነው ተቀማጭነቱ ቤልጂየም በሆነው የኢሳት ባልደረባ ላይ የተገኙ ባእድ የመሰላያ ሶፍትዌሮች ከጣሊያኑ ሃኪንግ ቲም የተላኩ መሆናቸውን ሲትዝን ላብን በመጥቀስ ታዋቂው ጋዜጣ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።

ጋዜጣው ባወጣው ሰፊ ዘገባ መረጃዎችን ከኮምፒዩተሮች ላይ ለመውሰድ የሚያስፈልገው ባእድ ሶፍትዌር የተላከው ከጣሊያን ኩባንያ ጋር ቢሆንም፣ ኩባንያው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግንኙነት ሳይኖረው እንደማይቀር ገልጿል።
የኢሳት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ነአምን ዘለቀ ድርጊቱን የሚፈጽመው የኢትዮጵያ መንግስት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ አቶ ዋሂድ በላይ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊቱን አለመፈጸሙን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ተቀማጭነታቸው ውጭ አገር የሆኑ ድርጅቶችን ለመሰለል እጅግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ቢያፈስም እስካሁን የረባ ውጤት አላስገኘለትም።

No comments:

Post a Comment