BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Monday, 3 February 2014

ወገን ሳይኖር፣ አጋር ሳይኖር፣ በዙሪያ ደግ - አሳቢ ሳይኖር፤ ሹመት የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው! ጣጣው የማያልቅ ችግር ለትውልድ ይተርፋል፡፡


Horror: Rwandans view bodies during the country's horrific genocide in 1994




ጣጣው የማያልቅ ችግር ለትውልድ ይተርፋል፡፡ በትምህርት ከሀ እስከ ፐ መጓዝ የማይናቅ መሆኑ ባይካድም፤ ውጣ - ውረዱ፣ መከራው ሰቆቃው አይጣል ነው፡፡ ችግርን ከምንጩ መንቀል ብልህነት ነው። ከፊደልም ከህይወትም መማር ሙሉ ያደርገናል፡፡ ለለውጥ ዝግጁ የምንሆነው አንድም ዕውቀታችን ወደ ጥበብ ሲበስል፤ አንድም ለአዲስ ነገር አዕምሮአችን ክፍት ሲሆን፤እንዲሁም ከስህተታችን ለመማር እንችል ዘንድ ግትርነትን ስናስወግድ ነው፡፡
በሀገራችን የታሪክ ሂደት፤ ትግል፣ ድርድር፣ ዕርቅና ስምምነት፣ ጠቅልሎ ገብቶ ከመንግሥት ጋር መሥራት፣ መጣላትና መክዳት አዘውትረው የታዩ ክስተቶች ናቸው፡፡

በተለይ መከዳዳት እጅግ ተደጋግሞ የታየ ነው፡፡..............
“ወዳጅን አንዴ መክዳት ይቻላል ሁለት ጊዜ ግን አይቻልም” ትግል ሲከር፣ ዘመን ሲከዳ፣ አቋም ሲሟሽሽ፣ ተስፋ ሲጠፋ፣ በተለይም ወኔ ሲከዳ፤ አሊያም አቋም ሲለወጥ፤ እናት - ክፍልን ትቶ ወደሌላ ሠፈር ይገባል፡፡ መደራደር፣ ዕርቅና መስማማት ከጦርነት እኩል ሜዳ ላይ ናቸው ይባላል፡፡ ጂኬ ቴስተርተን እንደሚለን “መደራደርና መስማማት ማለት ግማሽ ዳቦ ማግኘት ከምንም ይሻላል ነበር፡፡ አሁን ግን በዘመናዊ መንግሥታት ዘንድ ግማሽ ዳቦ ከሙሉ ዳቦ ይሻላል በሚል ተለውጧል”፡፡ ተደራድሮ አንድ ነገር ማግኘት ታላቅ ነገር ነው፡፡ ሆኖም መደራደርን እጅ ከመስጠትና ከክዳት ለይቶ ማየት ያሻል፡፡ ከማጐብደድ መለየት የስፈልጋል፡፡

ደራሲና ፀሐፌ - ተውኔት ፀጋዬ ገ/መድህን “በምኒልክ” ተውኔቱ ያለውን አለመርሳት ደግ ነው። “ሸዋም ያው ያባት ልምዱን፣ የባህል ግብሩን፣ በጐበና ሹመት ላይ አጉተመተመ፡፡ አጉረመረመ፡፡ ያኑ የሆድ ክፋት ቅርሱን፣ ምሱን፣ የምቀኛ ተውሳኩን፣ ውስጥ ውስጡን አቀረሸ፡፡ “ማናቸውን ንጉሥ እንበል?!” እያለ፤ ይሄ አዲሱ ጐበና፣ የልቼው ሳይሆን፣ ራሱን እንደንጉሥ ላስጠራ ባይ ተቆናኝ ሆኗል፤ መሾሙንስ ምኒልክ ሾመው፣ መሻሩንስ ማን ይሽርለት ይሆን? እያለ…”

ወገን ሳይኖር፣ አጋር ሳይኖር፣ በዙሪያ ደግ - አሳቢ ሳይኖር፤ ሹመት የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው! በእርግጥ አያሌ ከእናት ፓርቲያቸው የተለያዩ የጥንት የጧት ሰዎች እናውቃለን፡፡ ምናልባትም እነሱም የራሳቸው ምክንያት ይኖራቸው ይሆናል፡፡ ለአንድ የእንግሊዝ ፓርላማ ቀዳማዊት ኤልሣቤጥ አደረጉት የሚባል ንግግር ላይ “እንደኔ ከሆነ፤ ለምን መኖርን መውደድ እንዳለብኝ ወይም ለምን መሞትን መፍራት እንዳለብኝ አንዳችም ምክንያት የለኝም፡፡ የዚህችን ዐለም በቂ ልምድ አግኝቻለሁ፡፡ ዜጋ መሆንም፤ መሪ መሆንም ምን ማለት እንደሆነ አውቄያለሁ፡፡ መጥፎም ጥሩም ጐረቤት ኖሮኝ ያውቃል፡፡ ስለዚህ በራሴ ዕምነት መክዳት ጥሩ እንደሆን ተገንዝቤአለሁ፤ ብለዋል፡፡ ደግና ክፉ መለየት ያለበት ራሱ ባለቤቱ ነው።

የዱሮም ይሁን የአሁን ወዳጅ፣ ከጊዜ በኋላ፤ አቋም ለውጠው ሲገናኙ እንዴት እንደሚገናኙ፣  እንዴት እንደሚወያዩ፤ ግራ ሊገባቸው ይችላል፡፡ ሆድ ለሆድ ተግባብተው? ተቂያቂመው? ወይስ ይቅር ለእግዚሃር ተባብለው፤ ስለአገር ጉዳይ ተስማምተን እንሥራ ተባብለው?

በየትኛውም የሹመት ደረጃ ብንሆን፤ አገርን የሚጐዳ ከሆነ ሥልጣን በቃኝ ማለት መክዳት አይደለም የእንግሊዝ ተወላጁ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዴ ሀይለኛ ግምገማ ተደርጐ አይምሬ የሆነ ግልጽ ሂስ ሲካሄድባቸው፤ “እኔምኮ ዶሮ እስኪጮህ ነበር የምጠብቀው ሥልጣኔን ለመልቀቅ” አሉ፤ አሉ፡፡ የፖለቲካ ሥልጣንን፤ ተዋግተንም እናምጣው፣ በሰላማዊ ድርድር፤ አሊያም ደጅ ጠንተን፤ ዳገት ቁልቁለት የሌለበት፣ በወርቅ አልጋ፣ በእርግብ ላባ ላይ መተኛት ነው ብሎ ማሰብ፤ ቢያንስ የዋኅነት ነው። ምንሊክ ሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment