የታሪክ ምሁሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከመቀመጫቸው በመነሳት ታሪካዊ እና አስደማሚ ንግግር አድርገዋል፡፡
“እዚህ ፍርድ ቤት የተገኘነው ፍርድ ቤቱ ፍትህ ይሰጠናል ብለን አይደለም፡፡ በዚህ ፍርድ ቤት ላይ ቅንጣት ታክል አመኔታ የለንም፡፡ መከላከያ ምስክርም ሆነ ማስረጃ የምናቀርበው ለታሪክ ተመዝግቦ እንዲቀር እንጂ በዚህ ፍርድ ቤት ጉዳያችን ታይቶ ፍትህን እናገኛለን ብለን አይደለም፡፡ ትክክለኛ ፍርድ ቤት ቢሆን ህገ መንግስቱ ተጥሶ ኢቲቪ ላቀረበው ብይን ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሰጠ ነበር” በማለት ረዘም ያለ አስደማሚ እና የፍትህ ስርአቱ የላዠቀ መሆኑን በመረጃ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡..............
ችሎቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ንግግራቸውን በየተራ ቆመው ለፍርድ ቤቱ ሲያሰሙ ዳኞቹ ደንግጠው ንግግራቸውን ከማዳመጥ የዘለለ መሃል መሃል ላይ ለማስቆም ከመሞከር በዘለለ ሌላ ምንም ሊያደርጉ አልተቻላቸውም፡፡
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የኢቲቪ ጉዳይ እኔ አይመለከተኝም በማለት የመሃል ዳኛው ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡
እነዚህን መሰል ጀግና ወኪሎች በመምረጣችን
እድለኞች ነን!!!
እድለኞች ነን!!!
No comments:
Post a Comment